ዝርዝሮች
የሚቀጥሉት ዝርዝር ትእዛዞች ለ ሰንጠረዥ ዝግጁ ናቸው
እርስዎ መስራት የሚፈልጉትን ሰነድ የያዘ መስኮት መመረጥ አለበት ዝርዝር ትእዛዙን ለ መጠቀም: በ ተመሳሳይ: እርስዎ እቃ መምረጥ አለብዎት በ ሰነዱ ውስጥ ዝርዝር ትእዛዙን ለ መጠቀም ከ እቃው ጋር የ ተዛመደውን
ዝርዝር አገባብ sensitive ነው: ይህ ማለት እነዚህ ዝርዝር እቃዎች ዝግጁ የሚሆኑት አሁን ለሚሰሩት ስራ አስፈላጊ ሲሆኑ ነው: መጠቆሚያው በ ጽሁፍ አካባቢ ካለ: እነዚህ ሁሉም ዝርዝር እቃዎች ዝግጁ ይሆናሉ ጽሁፉን ለማረም: እርስዎ ንድፍ ከ መረጡ በ ሰነድ ውስጥ: ለ እርስዎ የ ንድፍ ማረሚያ ዘዴ ይታያል
ማስገቢያ
የ ማስገቢያ ዝርዝር የ ያዛቸው ትእዛዞች አዲስ አካሎችን ለማስገባት ነው: እንደ ክፍሎች: ረድፎች: ወረቀቶች እና የ ክፍል ስሞች ወደ አሁኑ ወረቀት ውስጥ
ዳታ
ይጠቀሙ የ ዳታ ዝርዝር ትእዛዞችን በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ ያሉ ዳታዎችን ለማረም: መጠኖች ለ መግለጽ ይችላሉ: ዳታውን ማጣራት እና መለየት: ውጤቶችን ማስላት: ዳታዎችን ማቀድ እና የ ፒቮት ሰንጠረዥ መፍጠር ይችላሉ
መሳሪያዎች
የ መሳሪያዎች ዝርዝር የ ያዛቸው ትእዛዞች ፊደሎችን ለማረም ፡ ማመሳከሪያ ወረቀቶችን ፈልጎ ለማግኘት: ስህተቶችን ፈልጎ ለማግኘት እና እቅዶችን ለ መግለጽ ነው