ክፍሎች መሰየሚያ
የ ተፈቀዱ ስሞች
ስሞች በ ሰንጠረዥ ውስጥ መያዝ ይችላሉ ፊደሎች: የ ቁጥር አሀዞች: እና አንዳንድ የ ተለዩ ባህሪዎች: ስሞች በ ፊደል መጀመር አለባቸው ወይንም ከ ስራቸው የ ተሰመረ ባህሪዎች
የ ተፈቀዱ የተለዩ ባህሪዎች:
-
ከ ስሩ ማስመሪያ(_)
-
ነጥብ (.) - የሚቻለው ከ ስም ጋር ነው: ነገር ግን እንደ መጀመሪያ ወይንም መጨረሻ ባህሪ አይደለም
-
ባዶ ( ) - የሚቻለው ከ ስም ጋር ነው: ነገር ግን እንደ መጀመሪያ ወይንም መጨረሻ ባህሪ አይደለም እና ለ ክፍል መጠንም አይደለም
ስሞች ተመሳሳይ መሆን የለባቸውም እንደ ክፍል ማመሳከሪያዎች: ለምሳሌ: ይህ ስም A1 ዋጋ የለውም ምክንያቱም A1 የ ክፍል ማመሳከሪያ ነው ከ ላይ በ ግራ ክፍል በኩል
ስሞች መጀመር የለባቸውም በ ፊደል R አስከትለው ቁጥር: ይመልከቱ የ አድራሻ ተግባር ለ በለጠ መረጃ
ስሞች ለ ክፍል መጠኖች ባዶ ማካተት የለባቸውም: ባዶ የሚፈቀደው በ ስሞች መካከል ነው ለ ነጠላ ክፍሎች: ወረቀቶች እና ሰነዶች
ክፍሎች እና መቀመሪያ መሰየሚያ
ጥሩው መንገድ ማመሳከሪያዎች ወደ ክፍሎች እና የ ክፍል መጠኖች ውስጥ መስራት በ መቀመሪያ ውስጥ የ መጠኖች ስሞች እንዲታይ ማድረግ ነው: ለምሳሌ: እርስዎ መሰየም ይችላሉ መጠን A1:B2 መጀመሪያ እርስዎ ከዛ በኋላ ይጻፉ በ መቀመሪያ ውስጥ እንደ የ "=ድምር(መጀመሪያ)". እርስዎ ረድፍ ወይንም አምድ ካስገቡ በኋላ ወይንም ካጠፉ በኋላ: LibreOffice በትክክል በ ስም የሚለዩትን መጠኖች ይፈጽማል: የ መጠኖች ስም ባዶ ቦታ መያዝ የለበትም
ለምሳሌ: በጣም ቀላል ነው ለማንበብ የ መቀመሪያ የ ሺያጭ ቀረጥ እርስዎ ከ ጻፉ "= መጠን * የ ቀረጥ_መጠን" ክዚህ ይልቅ ከ "= A5 * B12". ስለዚህ እርስዎ ይሰይማሉ ክፍል A5 "መጠን" እና ክፍል B12 "የ ቀረጥ_መጠን"
ይጠቀሙ የ ስሞች መግለጫ ንግግር ለ መግለጽ ስሞች በ መቀመሪያ ውስጥ ወይንም በ ከፊል መቀመሪያ ውስጥ እርስዎ አዘውትረው የሚጠቀሙበትን: የ መጠን ስሞችን ለ መወሰን
-
ይምረጡ ከፍል ወይንም የ ክፍሎች መጠን: እና ከዛ ይምረጡ ወረቀት - የ ተሰየሙ መጠኖች እና መግለጫዎች - መግለጫ የ ስሞች መግለጫ ንግግር ይታያል
-
ይጻፉ የ ተመረጠውን ቦታ ስም በ ስም ሜዳ ውስጥ: ይጫኑ መጨመሪያ አዲስ የ ተገለጸው ስም ይታያል ከ ታች በ ዝርዝር ውስጥ: ይጫኑ እሺ ንግግሩን ለ መዝጋት
እርስዎ መሰየም ይችላሉ የ ክፍል መጠኖች በዚህ ንግግር ውስጥ በማስገባት ስም በ ሜዳ ውስጥ እና ከዛ በ መምረጥ ተገቢውን ክፍሎች
እርስዎ ስም በ መቀመሪያ ውስጥ ከጻፉ: ከ ጥቂት ባህሪዎች ካስገቡ በኋላ ለ እርስዎ ጠቅላላ ስሙ ይታያል እንደ ጠቃሚ ምክር
-
ይጫኑ ማስገቢያውን ቁልፍ ስሙን ለ መቀበል ከ ጠቃሚ ምክር ውስጥ
-
ከ አንድ ስም በላይ በ ተመሳሳይ ፊደል የሚጀምር ከሆነ: እርስዎ ወደ ፊት መሸብላል ይችላሉ በ ስም ዝርዝር ውስጥ በ መጠቀም Ctrl + Tab ቁልፎች እና ወደ ኋላ በ መጠቀም Shift + Ctrl + Tab ቁልፎች