የ ቁጥር አቀራረብ ከ ዴሲማል ጋር
ያስገቡ ቁጥር ወደ ወረቀት ውስጥ: ለምሳሌ: 1234.5678. ይህ ቁጥር ይታያል በ ነባር ቁጥር አቀራረብ ውስጥ: ከ ሁለት ዴሲማል ቦታዎች ጋር: ይህ ለ እርስዎ ይታያል 1234.57 እርስዎ ማስገቢያውን ሲያረጋግጡ: በ ሰነዱ ላይ ብቻ የሚታየው ይጠጋጋል: በውስጥ: ቁጥሩ ሁሉንም አራቱን የ ዴሲማል ቦታዎች ከ ዴሲማል ነጥቦች በኋላ እንደያዘ ይቆያል
ቁጥሮች በ ዴሲማል ለማቅረብ:
-
መጠቆሚያውን በ ቁጥሩ ላይ ያድርጉ እና ይምረጡ አቀራረብ - ክፍሎች የ ክፍሎች አቀራረብ ንግግር ለ ማስጀመር
-
በ ቁጥሮች tab ውስጥ ለ እርስዎ ምርጫ ይታያል በ ቅድሚያ የተገለጸ ቁጥር አቀራረብ: ከ ታች በ ቀኝ በኩል በ ንግግር ውስጥ ለ እርስዎ ይታያል ቅድመ እይታ ቁጥሩ ምን እንደሚመስል የ ተወሰነ አቀራረብ ቢጠቀሙ
እርስዎ ከ ፈለጉ ማሻሻል የሚታየውን የ ቁጥር ዴሲማል ቦታ: ቀላሉ መንገድ መጠቀም ነው የ ቁጥር አቀራረብ: የ ዴሲማል ቦታ መጨመሪያ ወይንም የ ቁጥር አቀራረብ: የ ዴሲማል ቦታ ማጥፊያ ምልክቶችን ከ አቀራረብ መደርደሪያ ላይ