እንደ ሁኔታው አቀራረብ መፈጸሚያ
ዝርዝር ትእዛዝ ይጠቀሙ አቀራረብ - እንደ ሁኔታው አቀራረብ ንግግሩ ሁኔታዎችን በ ክፍል መወሰን ያስችሎታል: ሁኔታው መሟላት አለበት ለ ተመረጠው ክፍል የ ተወሰነ አቀራረብ እንዲኖረው
እንደ ሁኔታው አቀራረብ ለመፈጸም: በራሱ ማስሊያ ማስቻል አለብዎት: ይምረጡ ዳታ - ማስሊያ - በራሱ ማስሊያ (ለ እርስዎ ይታይዎታል የ ምልክት ማድረጊያ ከ ትእዛዝ አጠገብ በራሱ ማስሊያ ሲያስችሉ)
በ እንደ ሁኔታው አቀራረብ: እርስዎ ይችላሉ ለምሳሌ: ጠቅላላ ማድመቅ ከ መካከለኛ ዋጋ በላይ የሚያልፉትን ከ ሁሉም ጠቅላላ ውስጥ: ጠቅላላ ከ ተቀየረ: አቀራረቡም በ ተመሳሳይ አይነት ይቀየራል: ምንም ሌላ ዘዴ በ እጅ ሳይጨመር
ሁኔታውን ለ መግለጽ
-
ይምረጡ ክፍሎች እርስዎ የሚፈልጉትን እንደ ሁኔታው ዘዴ ለ መፈጸም
-
ይምረጡ አቀራረብ - እንደ ሁኔታው አቀራረብ
-
ያስገቡ ሁኔታ(ዎች) ወደ ንግግር ሳጥን ውስጥ: ንግግሩ ተገልጿል በ ዝርዝር በ LibreOffice እርዳታ ውስጥ እና ምስሌዎች ከ ታች በኩል ተሰጥቷል
ለምሳሌ የ እንደ ሁኔታው አቀራረብ: ማድመቂያ ጠቅላላዎችን ከ ላይ/ከ ስር መከከለኛ ዋጋ
ደረጃ1: የ ቁጥር ዋጋዎች ማመንጫ
እርስዎ የ ተወሰኑ ዋጋዎች በ እርስዎ ሰንጠረዥ ውስጥ ማጉላት ከ ፈለጉ: ለምሳሌ: ሰንጠረዥ በሚገለበጥ ጊዜ: እርስዎ ሁሉንም ዋጋዎች ማሳየት ይችላሉ: ከ መካከለኛ በ ላይ የሆነውን በ አረንጓዴ ቀለም እና ሁሉንም ከ መካከለኛ በ ታች የሆነውን በ ቀይ ቀለም ማሳየት ይችላሉ: ይህ የሚቻለው በ እንደ ሁኔታው አቀራረብ ነው
-
በ መጀመሪያ: በ ሰንጠረዥ ውስጥ ይጻፉ ጥቂት የ ተለያዩ ዋጋዎች: ለ እርስዎ ሙከራ እርስዎ መፍጠር ይችላሉ በደፈናው ቁጥሮች:
በ አንዱ ክፍል ውስጥ ያስገቡ መቀመሪያ =በነሲብ(), እና እርስዎ ያገኛሉ የ ነሲብ ቁጥር በ 0 እና 1. መካከል: እርስዎ ኢንቲጀር ከ ፈለጉ በ 0 እና 50, መካከል: ያስገቡ መቀመሪያ =ኢንቲጀር(በነሲብ()*50).
-
መቀመሪያ ኮፒ ማድረጊያ ለ መፍጠር ረድፍ በነሲብ ቁጥሮች: ይጫኑ ከ ታች በ ቀኝ ጠርዝ በኩል የ ተመረጠውን ክፍል: እና ይጎትቱ ወደ ቀኝ የሚፈለገው ክፍል እስከሚመረጥ ድረስ
-
በ ተመሳሳይ መንገድ ከ ላይ እንደ ተገለጸው: ይጎትቱ ወደ ታች የ ሩቅ ቀኝ ክፍል ጠርዝ ለ መፍጠር ተጨማሪ ረድፎች በ ደፈናው ቁጥር
ደረጃ 2: የ ክፍል ዘዴዎች ይግለጹ
የሚቀጥለው ደረጃ የ ክፍል ዘዴ ለ መፈጸም ነው: ለ ሁሉም ዋጋዎች ለሚወክሉት የ ላይኛውን-መካከለኛ መገልበጫ: እና ከ እነዚህ አንዱ ከ መካከለኛ በታች የሆነውን: እርግጠኛ ይሁኑ የ ዘዴዎች መስኮት እንደሚታይ ከ መቀጠልዎት በፊት
-
ይጫኑ በ ባዶ ክፍል ላይ እና ይምረጡ ትእዛዝ ክፍሎች አቀራረብ በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ
-
ከ ክፍሎች አቀራረብ ንግግር ውስጥ ከ መደብ tab, ውስጥ ይምረጡ የ መደብ ቀለም እና ይጫኑ እሺ
-
ከ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ: ይጫኑ የ አዲስ ዘዴ ከ ምርጫ ምልክት ውስጥ: የ አዲሱን ዘዴ ስም ያስገቡ: ለዚህ ምሳሌ: የ ዘዴውን ስም "ከ ላይ" ይበሉት
-
ሁለተኛ ዘዴ ለ መግለጽ: ይጫኑ እንደገና በ ባዶ ክፍል ላይ እና ይቀጥሉ ከ ላይ እንደ ተጠቀሰው: የ ተለየ የ መደብ ቀለም ይመድቡ ለ ክፍል እና ስም ይመድቡ (ለዚህ ምስሌ: "ከ ታች በኩል")
ደረጃ 3: መከከለኛ ማስሊያ
በዚህ ምሳሌ ውስጥ: የምናሰላው መከከለኛ ነው በ ደፈናው ዋጋዎችን: ውጤቱ በ ክፍሉ ላይ ይቀመጣል:
-
መጠቆሚያውን በ ባዶ ክፍል ላይ ያድርጉ: ለምሳሌ: J14, እና ይምረጡ ማስገቢያ - ተግባር
-
ይምረጡ የ መከከለኛ ተግባር: የ አይጥ መጠቆሚያውን ይጠቀሙ ለ መምረጥ የ እርስዎን በደፈናው ቁጥሮች: ለ እርስዎ የማይታየዎት ከሆነ ጠቅላላ መጠኑ: ምክንያቱም የ ተግባር አዋቂ የሚከልለው ከሆነ: እርስዎ ማሳነስ ይችላሉ ንግግሩን ለጊዜው በ መጠቀም በ ምልክት
-
የ ተግባር አዋቂን ይዝጉ በ
ደረጃ 4: የ ክፍል ዘዴዎች መፈጸሚያ
አሁን እርስዎ መፈጸም ይችላሉ እንደ ሁኔታው አቀራረብ ወደ ወረቀት ውስጥ:
-
ሁሉንም ክፍሎች በ ነሲብ ቁጥሮች
-
ይምረጡ አቀራረብ - እንደ ሁኔታው አቀራረብ ትእዛዝ ለ መክፈት ተመሳሳይ ንግግር
-
እርስዎ ሁኔታውን እንደሚከተለው ይግለጽ: የ ክፍል ዋጋ የሚያንስ ከሆነ ከ J14: አቀራረብ ከ ክፍል ዘዴ "በ ታች": እና የ ክፍል ዋጋ የሚበልጥ ከሆነ ወይንም እኩል ከ J14: አቀራረብ ከ ክፍል ዘዴ "በ ላይ".
ደረጃ 5: የ ክፍል ዘዴ ኮፒ ማድረጊያ
እንደ ሁኔታው አቀራረብ ለ መፈጸም ወደ ሌሎች ክፍሎች በኋላ:
-
ይጫኑ አንዱን ክፍል ለ እንደ ሁኔታው አቀራረብ የ ተመደበውን
-
ክፍል ኮፒ ማድረጊያ ወደ ቁራጭ ሰሌዳ ውስጥ
-
ይምረጡ ተመሳሳይ አቀራረብ የሚቀበሉትን ክፍሎች
-
ይምረጡ ማረሚያ - የተለየ መለጠፊያ የ ተለየ መለጠፊያ ንግግር ይታያል
-
ከ ምርጫ ቦታ: ምልክት ያድርጉ የ አቀራረብ ሳጥን ውስጥ ብቻ: ሁሉም ሌሎች ሳጥኖች ምልክቱ መጥፋት አለበት: ይጫኑ እሺ