ጽሁፍ ወደ አምዶች
ጽሁፍ መክፈቻ በ አምድ ንግግር ውስጥ: እርስዎ የ ተመረጡትን ክፍሎች ይዞታዎች ማስፋት እና ማሰናዳት የሚችሉበት ወደ በርካታ ክፍሎች ውስጥ
የ ክፍል ይዞታዎችን ለማስፋት ወደ በርካታ ክፍሎች ውስጥ
እርስዎ ማስፋት ይችላሉ ክፍሎች በ ኮማ የ ተለያዩ ዋጋዎች የያዙ (CSV) ወደ በርካታ ክፍሎች በ ተመሳሳይ ረድፍ ውስጥ
ለምሳሌ: ክፍል A1 የያዘው በ ኮማ የተለያዩ ዋጋዎች 1,2,3,4, እና ክፍል A2 የያዘው ጽሁፍ ነው A,B,C,D.
-
እርስዎ ማስፋት የሚፈልጉትን ክፍል ወይንም ክፍሎች ይምረጡ
-
ይምረጡ ዳታ - ጽሁፍ ወደ አምዶች
ለ እርስዎ ይታያል ጽሁፍ ወደ አምዶች ንግግር
-
ይምረጡ የ መለያያ ምርጫ: የ ቅድመ እይታ ማሳያ የሚያሳየው የ አሁኑ ክፍል ይዞታዎች ይቀየራሉ ወደ በርካታ ክፍሎች
እርስዎ መምረጥ ይችላሉ የ ተወሰነ ስፋት እና ከዛ ይጫኑ በ ማስመሪያ ላይ በ ቅድመ እይታ ውስጥ የ ክፍል መለያያ ቦታዎች ለማሰናዳት
እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ወይንም መለያያ ባህሪዎች ማስገባት ለ መግለጽ የ መጨረሻ ነጥቦችን ቦታዎች: የ መለያያ ባህሪዎች ይወገዳሉ ከ ክፍል ይዞታዎች ውጤት ውስጥ
ከ ምሳሌ ውስጥ: እርስዎ ይምረጡ ኮማ እንደ ምልክት ባህሪ: ክፍል A1 እና A2 ይሰፋሉ ወደ አራት አምዶች እያንዳንዱ A1 የያዘው 1, B1 የያዘው 2, ወዘተ