ማረሚያ

ይህ ዝርዝር የያዘው ትእዛዝ የ አሁኑን ሰነድ ይዞታዎች ማረሚያ ነው

መተው

መጨረሻ የሰሩትን ወይንም መጨረሻ ጽፈው ያስገቡትን መገልበጫ: እርስዎ ይምረጡ መገልበጥ የሚፈልጉትን: ይጫኑ ቀስቱ ላይ በ መተው ምልክት በ መደበኛ መደርደሪያ ላይ

እንደገና መስሪያ

መጨረሻ የ ሰሩትን መገልበጫ መተው ትእዛዝ: ለ መምረጥ የ መተው ደረጃን እርስዎ መገልበጥ የሚፈልጉትን: ይጫኑ ቀስቱ ላይ የ እንደገና መስሪያ ምልክት አጠገብ ያለውን በ መደበኛ እቃ መደርደሪያ ላይ

መድገሚያ

የ መጨረሻውን ትእዛዝ መድገሚያ: ይህ ትእዛዝ ዝግጁ የሚሆነው ለ መጻፊያ እና ለ ሰንጠረዥ ነው

መቁረጫ

ማስወገጃ እና ኮፒ ማድረጊያ የተመረጠውን ወደ ቁራጭ ሰሌዳ

ኮፒ

የተመረጠውን ወደ ቁራጭ ሰሌዳ ኮፒ ማድረጊያ

መለጠፊያ

መጠቆሚያው ባለበት ቦታ የ ቁራጭ ሰሌዳ ይዞታ ማስገቢያ: እና የ ተመረጠውን ጽሁፍ ወይንም እቃዎች መቀየሪያ

የተለያ መለጠፊያ

መጠቆሚያው ባለበት ቦታ የ ቁራጭ ሰሌዳ ይዞታ ማስገቢያ ወደ አሁኑ ፋይል አቀራረብ እርስዎ በሚወስኑት

ሁሉንም መምረጫ

የ አሁኑን ፋይል ጠቅላላ ይዞታ ክፈፍ: ወይንም የ ጽሁፍ እቃ መምረጫ

የ መምረጫ ዘዴ

ይምረጡ የ መምረጫ ዘዴ ከ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ: መደበኛ መምረጫ ዘዴ: ወይንም መምረጫ ዘዴ መከልከያ

ጽሁፍ ይምረጡ

እርስዎ ማስቻል ይችላሉ የ መጠቆሚያ መምረጫ ለ ንባብ-ብቻ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ወይንም በ እርዳታ ውስጥ: ይምረጡ ማረሚያ - ጽሁፍ መምረጫ ወይንም መክፈቻ የ አገባብ ዝርዝር ለ ንባብ-ብቻ ጽሁፍ ሰነድ እና ይምረጡ ጽሁፍ መምረጫ የ ተመረጠው መጠቆሚያ ብልጭ ድርግም አይልም

በ ቀጥታ መጠቆሚያ ዘዴ

ተጠቃሚውን በ መጀመሪያው: መሀከል ወይንም በ መጨረሻው ቦታ ላይ መጫን እና ማንኛውንም የ ጽሁፍ ገጽ ላይ መጻፍ ያስችለዋል

መፈለጊያ

መቀያየሪያ የሚታየውን የ መፈለጊያ እቃ መደርደሪያ ለ ጽሁፍ መቃኛ ወይንም ሰነዶችን በ አካል መፈለጊያ

መፈለጊያ & መቀየሪያ

መፈለጊያ ወይንም መቀየሪያ ጽሁፍ ወይንም አቀራረብ በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ

መሄጃ ወደ ገጽ

መክፈቻ የ መቃኛ መስኮት ላይ የ ገጽ ቁጥር ማሽከርከሪያ ቁልፍ: እና እርስዎ የ ገጽ ቁጥር ማስገባት ይችላሉ

ለውጦች መከታተያ

በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ለውጦችን ለ መከታተል ዝግጁ የሆኑ ትእዛዞች ዝርዝር

Hyperlink

እርስዎን hyperlinks መፍጠር እና ማረም የሚያስችሎት ንግግር መክፈቻ

የ ግርጌ ወይንም የ መጨረሻ ማስታወሻ

ማረሚያ የ ተመረጠውን የ ግርጌ ማስታወሻ ወይንም የ መጨረሻ ማስታወሻ ማስቆሚያ: ይጫኑ ከ ግርጌ ማስታወሻ ወይንም ከ መጨረሻ ማስታወሻ በፊት እና ከዛ ይምረጡ ይህን ትእዛዝ

ማውጫ ማስገቢያ

የ ተመረጠውን የ ማውጫ ማስገቢያ ማረሚያ: ይጭኑ ከ ማውጫ ማስገቢያው ፊት ለ ፊት ወይንም በ ማውጫ ማስገቢያው ላይ: እና ከዛ ይምረጡ ይህን ትእዛዝ

የ ጽሁፎች ዝርዝር ማስገቢያ

ለ ተመረጠው የ ጽሁፎች ዝርዝር ማስገቢያ ማረሚያ

ሜዳዎች

እርስዎ የ ባህሪዎችን ሜዳ ሊያርሙ የሚችሉበት ንግግር መክፈቻ: ይጫኑ ከ ሜዳው ፊት ለ ፊት: እና ከዛ ይምረጡ ይህን ትእዛዝ በ ንግግር ውስጥ: እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የ ቀስት ቁልፍ በ መጠቀም ቀደም ወዳለው ወይንም ወደሚቀጥለው ሜዳ ለ ማንቀሳቀስ

አገናኞች

በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ የ አገናኝ ባህሪዎችን ማረም ያስችሎታል: እንዲሁም የ ፋል ምንጩን መንገድ: ይህ ትእዛዝ ዝግጁ አይደለም በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ አገናኝ ከሌለ ወደ ሌሎች ፋይሎች

የ ምስል ካርታ

እርስዎን URLs ማያያዝ ያስችሎታል ወደ ተወሰነ ቦታዎች ትኩስ ቦታ የሚባል: በ ንድፍ ወይንም በ ቡድን ንድፎች: የ ምስል ካርታ ቡድን አንድ ወይንም ተጨማሪ ትኩስ ቦታ

እቃ

በ እርስዎ ፋይል ውስጥ በ መምረጥ ያስገቡትን እቃ ማረም ያስችሎታል በ ማስገቢያ - እቃ ትእዛዝ

ዳታቤዝ መቀያየሪያ

ለ አሁኑ ሰነድ የ ዳታ ምንጭ መቀየሪያ የ ገቡትን ሜዳዎች ይዞታዎች በ ትክክል ለማሳየት: የ ተቀየረው ዳታቤዝ ተመሳሳይ ስም መያዝ አለበት

ፋይል ማረሚያ

ይጠቀሙ የ ፋይል ማረሚያ ምልክት የ ማረሚያ ዘዴን ለ ማስጀመር ወይንም ለ ማቦዘን