የ ጽሁፍ ሰነዶችን ኮፒ ማድረጊያ እና ማንቀሳቀሻ

  1. ይምረጡ ማንቀሳቀስ ወይንም ኮፒ ማድረግ የሚፈልጉትን ጽሁፍ

  2. ከ እነዚህ አንዱን ይስሩ:

    የ ተመረጠውን ጽሁፍ ለማንቀሳቀስ: ጽሁፉን ይዘው ይጎትቱ ወደ ተለየ ቦታ በ ሰነዱ ውስጥ እና ይልቀቁት: በሚጎትቱ ጊዜ የ አይጥ መጠቆሚያው ወደ ግራጫ ሳጥን ይቀየራል:.
    የ አይጥ መጠቆሚያው ዳታ እያንቀሳቀሰ ነው

    የ ተመረጠውን ጽሁፍ ኮፒ ለማድረግ: ተጭነው ይያዙ እርስዎ በሚጎትቱ ጊዜ: በዚህ ጊዜ የ አይጥ መጠቆሚያው ወደ መደመሪያ ምልክት ይቀየራል (+).
     የ አይጥ መጠቆሚያው ዳታውን ኮፒ እያደረገ ነው