የ ምእራፍ ቁጥር መጨመሪያ ለ መግለጫው

በ መግለጫው ላይ የ ምእራፍ ቁጥሮች መጨመር ይችላሉ

እርግጠኛ ይሁኑ በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ የ ጽሁፍ ሰነዶች በ ምእራፎች መደራጀታቸውን: እና የ ምእራፍ አርእስት እንዳላቸው: እን እርስዎ ከፈለጉ የ ክፍል አርእስት: ይጠቀሙ በ ቅድሚያ የተገለጹ የ ራስጌ አንቀጽ ዘዴዎች: እርስዎ እንዲሁም መመደብ አለብዎት የ ቁጥር መስጫ ምርጫ ለ ራስጌ አንቀጽ ዘዴዎች

  1. በ መግለጫው ላይ መጨመር የሚፈልጉትን እቃ ይምረጡ

  2. ይምረጡ ማስገቢያ - መግለጫ

  3. ይምረጡ የ መግለጫ አርእስት ከ ምድብ ሳጥን ውስጥ እና ይምረጡ የ ቁጥር መስጫ ዘዴ በ ቁጥር መስጫ ሳጥን ውስጥ
    እንዲሁም የ ጽሁፍ መግለጫ በዚህ ንግግር ሳጥን ውስጥ: ማስገባት ከፈለጉ ጽሁፍ በ መግለጫ ሳጥን ውስጥ

  4. ይጫኑ ምርጫዎች

  5. ደረጃ ሳጥን ውስጥ ይምረጡ የ ራስጌ ደረጃ ቁጥር ለ መጨመር ወደ ምእራፍ ቁጥር ውስጥ

  6. ይጻፉ ባህሪውን መለያየት የሚፈልጉትን የ ምእራፍ ቁጥር(ሮች) ከ መግለጫ ቁጥር በ መለያያ ሳጥን ውስጥ እና ከዛ ይጫኑ እሺ

  7. መግለጫ ንግግር ውስጥ ይጫኑ እሺ

የ ምክር ምልክት

LibreOffice ራሱ በራሱ መግለጫ መጨመሪያ እቃዎች ንድፎች ወይንም ሰንጠረዥ ሲያስገቡ ይምረጡ - LibreOffice መጻፊያ - በራሱ መግለጫ