ምእራፎችን በ መቃኛ ውስጥ ማዘጋጃ
እርስዎ ራስጌዎች እና ዝቅተኛ ጽሁፍ ወደ ላይ እና ወደ ታች ማንቀሳቀስ ይችላሉ: በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ መቃኛውን በ መጠቀም: እርስዎ እንዲሁም የ ራስጌ ደረጃዎችን ማሳደግ እና መቀነስ ይችላሉ: ይህን ገጽታ ለመጠቀም: በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ የ ራስጌ አቀራረብ ከ እነዚህ በ አንዱ የ አንቀጽ ዘዴዎች ይግለጹ: ለ ራስጌ የ አንቀጽ ዘዴዎች ለማስተካከል ይምረጡ መሳሪያዎች - የ ምእራፍ ቁጥር መስጫ : ይምረጡ ዘዴውን ከ አንቀጽ ዘዴ ሳጥን ውስጥ: እና ከዛ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ቁጥር ላይ ከ ደረጃዎች ዝርዝር ውስጥ:
በፍጥነት የ ጽሁፍ መጠቆሚያውን ወደ ራስጌ ለመውሰድ በ ሰነድ ውስጥ ሁለት-ጊዜ ይጫኑ ራስጌውን ከ መቃኛው ዝርዝር ውስጥ
ለማንቀሳቀስ መቃኛውን የ አርእስት መደርደሪያውን ይዘው ይጎትቱ ወደሚፈልጉት የ ስራ ቦታ: ለማሳረፍ መቃኛውን ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ክፈፉ ላይ ተጭነው ይዘው የ ትእዛዝ Ctrl ቁልፍ
በ ሰነድ ውስጥ ራስጌን ወደ ላይ እና ወደ ታች ማንቀሳቀሻ
በ መቃኛ ውስጥ የ አርእስት ደረጃዎች መታየታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ: በ ነባር ሁሉም ደረጃዎች ይታያሉ: ከ ታች ያሉትን ደረጃዎች ይመልከቱ የሚታዩ የ አርእስት ደረጃዎችን እንዴት እንደሚቀይሩ
-
በ መደበኛ መደርደሪያው ላይ ይጫኑ የ መቃኛውን ምልክት ለ መክፈት መቃኛውን
-
በ መቃኛ ይጫኑ የ ይዞታ መመልከቻ ምልክት
-
ከ እነዚህ አንዱን ይስሩ:
-
ራስጌውን ወደ አዲስ ቦታ ይጎትቱ ከ መቃኛው ዝርዝር ውስጥ
-
ይጫኑ ራስጌ ከ መቃኛው ዝርዝር ውስጥ: እና ይጫኑ ምእራፍ ማሳደጊያ ወይንም ምእራፍ መቀነሻ ምልክት
ራስጌ ለማንቀሳቀስ ያለ ዝቅተኛ ጽሁፍ: ተጭነው ይያዙ ትእዛዝCtrl እርስዎ በሚጎትቱ ጊዜ ወይንም ይጫኑ የ ምእራፍ ማሳደጊያ ወይንም ምእራፍ ማሳነሻ ምልክቶች
የ ራስጌውን ደረጃ ማሳደጊያ ወይንም ማሳነሻ
-
ራስጌውን ይምረጡ ከ መቃኛው ዝርዝር ውስጥ
-
ይጫኑ የ ከፍ ማድረጊያ ደረጃ ወይንም ዝቅ ማድረጊያ ደረጃ ምልክት
የሚታየውን የ ራስጌ ደረጃዎች ቁጥር መቀየሪያ
ይጫኑ የ ራስጌ ደረጃዎች ማሳያ ምልክት እና ቁጥሩን ከ ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ