የ ገጽ ቁጥር

የ አሁኑ የ ገጽ ቁጥር በዚህ ሜዳ የ ሁኔታ መደርደሪያ ላይ ነው: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ መቃኛ ለ መክፈት: እርስዎ ከዛ ሰነዱን መቃኘት ይችላሉ: በ ቀኝ-ይጫኑ ሁሉንም ምልክት ማድረጊያዎች በ ሰነድ ውስጥ ለማየት: ይጫኑ ምልክት ማድረጊያውን የ ጽሁፍ መጠቆሚያውን ወደ ምልክት ማድረጊያው አካባቢ ለማድረግ

የሚታየው ገጽ (x) ጠቅላላ የ ገጾች ቁጥር (y) የሚታዩት በ ገጽ x/y ነው: እርስዎ በ ሰነድ ውስጥ በ አይጥ በሚሸበልሉ ጊዜ: የ ገጽ ቁጥር የሚታየው አይጡን ሲለቁ ነው: እርስዎ በ አይጥ የ ቀኝ መጫኛ የሚሸበልሉ ከሆነ: የ ገጽ ቁጥሮች እንደ ጠቃሚ እርዳታ ይታያሉ: የ ገጽ ቁጥር መስጫ አቀራረብ በ ሁኔታ መደርደሪያ እና መሸብለያ መደርደሪያ ተመሳሳይ ናቸው

ማብራት ይችላሉ የ መቃኛ መመልከቻውን ማብሪያ ወይንም ማጥፊያ ሁለት-ጊዜ በመጫን የ ገጽ ቁጥር ሜዳ

ወደ ተወሰነ ገጽ ለ መሄድ የገጹን ቁጥር ያስገቡ በ ገጽ ማሸከርከሪያ ቁልፍ መቃኛ ውስጥ እና ይጫኑ ማስገቢያ ቁልፍን

የ ማስታወሻ ምልክት

በ መጫን አቋራጭ ቁልፎችን Shift++F5, ወደ ገጽ ቁጥር መቀየሪያ ይገባሉ ፡ ማስገቢያውን ሲጫኑ መጠቆሚያው ወደ ተመረጠው ገጽ ይሄዳል