ቁጥር መስጫ

የ ቁጥር አቀራረብ እና ቅደም ተከተል ለ ምእራፍ ቁጥር መስጫ በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ መወሰኛ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ መሳሪያዎች - ምእራፍ ቁጥር መስጫ - ቁጥር መስጫ tab


ደረጃ

ይጫኑ የ ምእራፍ እና ረቂቅ ደረጃ እርስዎ ማሻሻል የሚፈልጉትን: እና ከዛ ይወስኑ የ ቁጥር መስጫ ምርጫ ለ ደረጃ የ ቁጥር መስጫ ምርጫ ለ መፈጸም: ከ አንቀጽ ዘዴ በስተቀር: ለ ሁሉም ደረጃዎች: ይጫኑ "1-10".

ቁጥር መስጫ

ለ ተመረጠው የ ረቂቅ ደረጃ አቀራረብ ይወስኑ

የ አንቀጽ ዘዴ

ይምረጡ የ አንቀጽ ዘዴ እርስዎ መመደብ የሚፈልጉትን ለ ተመረጠው የ ምእራፍ እና ረቂቅ ደረጃ እርስዎ ከ ተጫኑ "ምንም": የ ተመረጠው ረቂቅ ደረጃ አይገለጽም

ቁጥር

እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን የ ቁጥር መስጫ ዘዴ ይምረጡ ለ ተመረጠው የ ረቂቅ ደረጃ

ምርጫዎች

መግለጫ

A, B, C, ...

አቢይ ፊደል

a, b, c, ...

የ ታችኛው ጉዳይ ፊደሎች

I, II, III, ...

የ ሮማውያን ቁጥር (በ ላይኛው ጉዳይ)

i, ii, iii, ...

የ ሮማውያን ቁጥር (በ ታችኛው ጉዳይ)

1, 2, 3, ...

የ አረብኛ ቁጥሮች

A,... AA,... AAA,...

በ ፊደል ቅደም ተከተል ቁጥር መስጫ በ ተመሳሳይ ፊደሎች: የ ፊደሎች ቁጥር የ ምእራፉን ደረጃ ያሳያል: ለምሳሌ: ሁለተኛው ቁጥር በ ደረጃ ሶስት "BBB" ነው

a,... aa,... aaa,...

በ ፊደል ቅደም ተከተል ቁጥር መስጫ በ ዝቅተኛ ጉዳይ ፊደሎች: የ ፊደሎች ቁጥር የ ምእራፉን ደረጃ ያሳያል: ለምሳሌ: ሶስተኛው ቁጥር በ ደረጃ ሁለት "cc" ነው

ምንም

ምንም ቁጥር መስጫ ምልክት የለም: ባህሪዎች ብቻ ወይንም የ ተገለጹ ምልክቶች በ መለያያ ሜዳዎች ውስጥ ይታያል ቁጥር በ ተሰጣቸው መስመር ላይ


የ ባህሪ ዘዴ

የ ቁጥር መስጫ ባህሪውን አቀራረብ ይምረጡ

ንዑስ ደረጃዎች ማሳያ

ይምረጡ የ ቁጥር መስጫ ደርጃዎች በ ምእራፍ ቁጥር መስጫ ውስጥ የሚካተቱትን: ለምሳሌ: ይምረጡ "3" ለ ማሳየት ሶስት ደረጃዎች የ ምእራፍ ቁጥር መስጫ 1.1.1

መለያያ በፊት

ከ ምእራፍ ቁጥር በፊት እንዲታይ የሚፈልጉትን ጽሁፍ ያስገቡ ለምሳሌ: ይጻፉ "ምእራፍ " ለማሳየት "ምእራፍ 1".

መለያያ በኋላ

ከ ምእራፍ ቁጥር በኋላ እንዲታይ የሚፈልጉትን ጽሁፍ ያስገቡ ለምሳሌ: ይጻፉ ነጥብ (.) ለማሳየት "1."

መጀመሪያ በ

እርስዎ የ ምእራፍ ቁጥር መስጫ እንዲጀምር የሚፈልጉበትን ቁጥር ያስገቡ