ዘዴዎች

የ ዘዴዎች ማሳረፊያ መደርደሪያ በ ጎን በኩል ያለውን ለ መፈጸም ይጠቀሙ: ለ መፍጠር: ለ ማረም: እና ለ ማስወገድ የ አቀራረብ ዘዴዎችን: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ማስገቢያው ላይ ዘዴውን ለ መፈጸም

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ መመልከቻ - ዘዴዎች

ማቅረቢያ መደርደሪያ ላይ ይጫኑ

ምልክት

ዘዴዎች


ማሳረፊያ የ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ: ይጎትቱ የ አርእስት መደርደሪያ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ የ ስራ ቦታ በኩል: መስኮቱን ለማስወገድ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ እቃ መደርደሪያው በ ነፃ ባዶ ቦታ ላይ

በ ነባር የ ዘዴዎች ማሳረፊያ የሚያሳየው ቅድመ እይታ ዝግጁ የሆኑ ዘዴዎችን ነው: ቅድመ እይታውን ማሰናከል ይችላሉ በ ባለሞያ ማዋቀሪያ በ ባህሪ ማሰናጃ ውስጥ /org.openoffice.Office.Common/StylesAndFormatting ቅድመ እይታ ወደ ሀሰት

ዘዴዎችን እንዴት እንደሚፈጽሙ:

  1. ጽሁፍ ይምረጡ: የ ባህሪ ዘዴ ለ መፈጸም ወደ አንድ ቃል: ቃሉ ላይ ይጫኑ: የ አንቀጽ ዘዴ ለ መፈጸም: አንቀጹ ላይ ይጫኑ

  2. ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ዘዴ ላይ ከ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ

የ ምክር ምልክት

እርስዎ አቋራጭ ቁልፍ መመደብ ይችላሉ ለ ዘዴዎች በ መሳሪያዎች - ማስተካከያ - የ ፊደል ገበታ tab ገጽ ውስጥ


የ ዘዴዎች እቃ መደርደሪያ የያዛቸው ምልክቶች ለ እርስዎ ሰነድ አቀራረብ ነው:

የ ዘዴ ምድብ

ምልክት

የ አንቀጽ ዘዴዎች

ለ አንቀጾች የ አቀራረብ ዘዴዎች ማሳያ ይጠቀሙ የ አንቀጽ ዘዴዎች ለ መፈጸም ተመሳሳይ አቀራረብ እንደ ፊደል: ቁጥር መስጫ: እና እቅድ ያሉ በ እርስዎ ሰነድ አንቀጽ ውስጥ

ምልክት

የ ባህሪ ዘዴዎች

ለ ባህሪዎች የ አቀራረብ ዘዴዎች ማሳያ የ ባህሪ ዘዴዎች ለ መፈጸም ይጠቀሙ የ ፊደል ዘዴዎች በ አንቀጽ ውስጥ ለ ተመረጠው ጽሁፍ

ምልክት

የ ክፈፍ ዘዴዎች

ለ ክፈፎች የ አቀራረብ ዘዴዎች ማሳያ: የ ክፈፍ ዘዴዎች ይጠቀሙ የ ክፈፍ እቅዶች እና ቦታ ለማቅረብ

ምልክት

የ ገጽ ዘዴዎች

ለ ገጾች የ አቀራረብ ዘዴዎች ማሳያ የ ገጽ ዘዴዎች ይጠቀሙ የ ገጽ እቅድ ለ መወሰን እንዲሁም ራስጌዎች እና ግርጌዎች እንዲያካትት

ምልክት

ዝርዝር ዘዴዎች

ለ ቁጥር መስጫ እና ለ ነጥብ መስጫ ዝርዝር አቀራረብ ማሳያ የ ዘዴዎች ዝርዝር ይጠቀሙ ለ ቁጥር መስጫ እና ለ ነጥብ መስጫ ባህሪዎች እና ማስረጊያ ለመወሰን

ምልክት

የ መሙያ አቀራረብ ዘዴ

የ ተመረጠውን ዘዴ ወደ እቃ ወይንም ጽሁፍ እርስዎ በ መረጡት ሰነድ ውስጥ መፈጸሚያ: ይጫኑ ይህን ምልክት: እና ከዛ ይጎትቱ ምርጫውን ወደ ሰነድ ውስጥ ዘዴው እንዲፈጸም በሚፈልጉበት ላይ ከዚህ ዘዴ ውስጥ ለ መውጣት: ይጫኑ ምልክቱን እንደገና ወይንም መዝለያ ቁልፍ

ምልክት

አዲስ ዘዴ ከ ምርጫው ውስጥ

ንዑስ ዝርዝር ከተጨማሪ ትእዛዞች ጋር መክፈቻ

አዲስ ዘዴ ከ ምርጫው ውስጥ

አዲስ ዘዴ መፍጠሪያ የ አሁኑ አንቀጽ አቀራረብ: ገጽ: ወይንም ምርጫ መሰረት ያደረገ

የ ማሻሻያ ዘዴ

ለ ጽሁፍ በ እጅ የ ቀረበ መለያ መጠቆሚያው ባለበት ቦታ በ ሰነድ ውስጥ ይጨመራል: ወደ ተመረጠው ዘዴ በ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ

ዘዴዎች መጫኛ

የ መጫኛ ዘዴዎች ንግግር መከፈቻ ፡ ዘዴዎች ከሌላ ሰነድ ለማምጫ

የ ምክር ምልክት

በ በለጠ ለ መረዳት ስለ ዘዴዎች


የተፈጸሙ ዘዴዎች

ለ አሁኑ አንቀጽ ዘዴ መመደቢያ: ለ ተመረጠው አንቀጽ ወይንም ለ ተመረጠው እቃ ዘዴ መመደቢያ