ዘዴዎች በ መጻፊያ ውስጥ
የሚቀጥለው መረጃ የሚመለከተው የ መጻፊያ ዘዴዎችን ነው እርስዎ መጠቀም የሚችሉት በ ዘዴዎች ማሳረፊያ በ ጎን መደርደሪያ ውስጥ
እርስዎ ከ ፈለጉ: የ አሁኑን ሰነድ ዘዴዎች ማረም ይችላሉ: እና ከዛ ሰነዱን ያስቀምጡት እንደ ቴምፕሌት: ሰነዱን እንደ ቴምፕሌት ለማስቀመጥ ይምረጡ ፋይል - ቴምፕሌት – እንደ ቴምፕሌት ማስቀመጫ
የ ዘዴ ምድብ
እነዚህ ናቸው የ ተለያዩ ምድቦች ለ ዘዴዎች አቀራረብ
ስም |
መግለጫ |
የ ባህሪ ዘዴዎች |
ይጠቀሙ የ ባህሪዎች ዘዴ ለ ነጠላ ባህሪዎች: ወይንም ለ ጠቅላላ ቃሎች እና ሐረጎች አቀራረብ: እርስዎ ከ ፈለጉ: የ ባህሪ ዘዴዎች መገንባት ይችላሉ |
የ አንቀጽ ዘዴዎች |
ይጠቀሙ የ አንቀጽ ዘዴዎች ለ አንቀጾች አቀራረብ: የ ፊደል አይነት እና መጠን ያካትታል: እርስዎ እንዲሁም መምረጥ ይችላሉ የ አንቀጽ ዘዴ ወደሚቀጥለው አንቀጽ መፈጸም ይችላሉ |
የ ክፈፍ ዘዴዎች |
የ ክፈፍ ዘዴዎች ይጠቀሙ ለ ጽሁፍ እና ንድፍ ክፈፎች አቀራረብ |
የ ገጽ ዘዴዎች |
የ ገጽ ዘዴዎች ይጠቀሙ የ ሰነድ አካል ለማደራጀት: እና የ ገጽ ቁጥሮች ለ መጨመር: እርስዎ እንዲሁም መወሰን ይችላሉ የ ገጽ ዘዴ ለ መጀመሪያው ገጽ ተከትሎ ለሚመጣው የ ገጽ መጨረሻ |
ዝርዝር ዘዴዎች |
የ ዝርዝር ዘዴዎች ይጠቀሙ ቁጥር የ ተሰጠውን ወይንም የ ነጥብ ዝርዝር ለማቅረብ |
የ ዘዴ ቡድኖች
እነዚህን የ ዘዴ ቡድን ነው እርስዎ ማሳየት የሚችሉት በ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ
ስም |
ትርጉም |
ራሱ በራሱ |
ለ አሁኑ አገባብ ተገቢ የሆነ ዘዴዎች ማሳያ |
ሁሉንም ዘዴዎች |
የ ንቁ ዘዴ ምድብ ሁሉንም ዘዴዎች ማሳያ |
የተፈጸሙ ዘዴዎች |
ዘዴዎች ማሳያ (ለ ተመረጠው ምድብ) በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ የ ተፈጸመውን |
ዘዴዎች ማስተካከያ |
በ ተመረጠው የ ዘዴ ምድብ ውስጥ በ ተጠቃሚ-የሚወሰን ዘዴዎች ማሳያ |
የ ባህሪ ዘዴዎች |
የ ጽሁፍ ዘዴዎች አቀራረብ ማሳያ |
የ ምእራፍ ዘዴዎች |
የ ራስጌ ዘዴዎች አቀራረብ ማሳያ |
ዝርዝር ዘዴዎች |
የ ቁጥር መስጫ ወይንም የ ነጥብ ዝርዝር ዘዴዎች አቀራረብ ማሳያ |
የ ማውጫ ዘዴዎች |
የ ማውጫ ዘዴዎች አቀራረብ ማሳያ |
የተለየ አካባቢ ዘዴዎች |
የ አቀራረብ ዘዴዎች ማሳያ ለ ራስጌ: ለ ግርጌ: ለ ግርጌ ማስታወሻ: ለ መጨረሻ ማስታወሻ: ለ ሰንጠረዥ እና መግለጫዎች |
የ HTML ዘዴዎች |
ለ HTML ሰነዶች ዝርዝር ዘዴዎች ማሳያ |
እንደ ሁኔታው ዘዴዎች |
በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ እንደ ሁኔታው ዘዴዎች ማሳያ |
ደረጃው |
በ ተመረጠው ምድብ ውስጥ ዘዴዎች ማሳያ በ ቅደም ተከተል ዝርዝር: ዘዴዎቹን በ ንዑስ ደረጃ ለ መመልከት: ይጫኑ በ መደመሪያ ምልክት (+) ላይ ከ ንዑስ ደረጃው ስም አጠገብ ያለውን |