አይነት

ለ ተመረጠው እቃ ወይንም ክፈፍ በ ገጹ ላይ መጠን እና ቦታ መወሰኛ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ አቀራረብ - ምስል - አይነት tab

ይምረጡ አቀራረብ - ክፈፍ እና እቃ - ባህሪዎች - ይጻፉ tab

ይምረጡ መመለከቻ - ዘዴዎች - ዝርዝር አገባብ መክፈቻ ማሻሻያ/አዲስ - አይነት tab

ይምረጡ ማስገቢያ - ክፈፍ - ክፈፍ - አይነት tab


መጠን

ስፋት

ለ ተመረጠው እቃ እርስዎ የሚፈልጉትን ስፋት ያስገቡ

ዝምድናው

የ ተመረጠውን እቃ ስፋት በ ፐርሰንት ማስሊያ በ ጽሁፍ ገጽ ቦታ ስፋት ውስጥ

አንፃራዊ የ ስፋት ግንኙነት

መወሰኛ 100% ስፋት ማለት: ከ ሁለቱ አንዱን የ ጽሁፍ ቦታ (መስመር አያካትትም) ወይንም ጠቅላላ ገጹን ( መስመር ያካትታል):

እርዝመት

ለ ተመረጠው እቃ እርስዎ የሚፈልጉትን እርዝመት ያስገቡ

ዝምድናው

የ ተመረጠውን እቃ እርዝመት በ ፐርሰንት ማስሊያ በ ጽሁፍ ገጽ ቦታ እርዝመት ውስጥ

አንፃራዊ የ ስፋት ግንኙነት

መወሰኛ 100% እርዝመት ማለት: ከ ሁለቱ አንዱን የ ጽሁፍ ቦታ (መስመር አያካትትም) ወይንም ጠቅላላ ገጹን ( መስመር ያካትታል).

መጠኑን መጠበቂያ

የ እርዝመት እና ስፋት መጠን መጠበቂያ እርስዎ ስፋት እና እርዝመት በሚቀይሩ ጊዜ የ ማሰናጃውን

ዋናው መጠን

የ ተመረጠው እቃ ወደ ዋናው መጠን ወደ ነበረበት መጠን መመለሻ

የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ ምርጫ ለ ክፈፎች ዝግጁ አይደለም


ራሱ በራሱ

ራሱ በራሱ የ ክፈፍ ስፋት ወይንም እርዝመት ማስተካከያ ለ ክፈፍ ይዞታዎች እንዲስማማ: እርስዎ ከ ፈለጉ: የ ክፈፍ አነስተኛ ስፋት ወይንም እርዝመት መወሰን ይችላሉ

የ ማስታወሻ ምልክት

ራሱ በራሱ ምርጫዎች ዝግጁ የሚሆነው ክፈፍ ሲመርጡ ብቻ ነው


ማስቆሚያ

ለ ተመረጠው እቃ ወይንም ክፈፍ የ ማስቆሚያ ምርጫ መወሰኛ: የ ማስቆሚያ ምርጫ አይኖርም እርስዎ ንግግር ሲከፍቱ ከ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ

ወደ ገጽ

የ ተመረጠውን የ አሁኑ ገጽ ማስቆሚያ

ወደ አንቀጽ

የ ተመረጠውን የ አሁኑ አንቀጽ ማስቆሚያ

ወደ ባህሪ

የ ተመረጠውን የ አሁኑ ባህሪ ማስቆሚያ

እንደ ባህሪ

የ ተመረጠውን እንደ ባህሪ ማስቆሚያ: የ አሁኑ መስመር እርዝመት እንደገና ይመጠናል: ለ ተመረጠው እርዝመት እንዲስማማ

ቦታ

በ ገጹ ላይ ለ ተመረጠውን እቃ ቦታ ይወስኑ

በ አግድም

ለ እቃው የ አግድም ማሰለፊያ ምርጫ ይምረጡ ይህ ምርጫ ዝግጁ አይሆንም እርስዎ ከ መረጡ "እንደ ባህሪ ማስቆሚያ"

እርስዎ ከ ተመረጠው እቃ በ ግራ ጠርዝ በኩል መተው የሚፈልጉትን ክፍተት መጠን ያስገቡ: ለ ተመረጠው እቃ እና ለ ማመሳከሪያ ነጥብ እርስዎ የ መረጡትን ሳጥን ውስጥ ይህ ምርጫ ዝግጁ የሚሆነው እርስዎ ከ መረጡ ነው "በ ግራ" በ አግድም ሳጥን ውስጥ

የ ማመሳከሪያ ነጥብ ይምረጡ ለ ተመረጠው የ አግድም ማሰለፊያ ምርጫ

ለ እርስዎ ይታያል የ ውጤት ማሰለፊያ ምርጫ እርስዎ በ መረጡት በ ቅድሚያ እይታ ሳጥን ውስጥ

በ ሙሉ ገጾች ላይ ማንፀባረቂያ

እንደ ነበር መመለሻ የ አሁኑን የ አግድም ማሰለፊያ ማሰናጃ በ ሙሉ ቁጥር ገጾች ላይ

የ ምክር ምልክት

እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የ ምስል መገልበጫ ምርጫ ለ ማስተካከል የ እቃዎች እቅድ በ ሙሉ እና ጎዶሎ ገጾች ላይ


በ ቁመት

ለ እቃው የ ቁመት ማሰለፊያ ምርጫ ይምረጡ

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ እቃ ካስቆሙ ወደ ክፈፍ በ ተወሰነ እርዝመት ውስጥ: የ "ታችኛው" እና "መሀከል" ማሰለፊያ ምርጫ ዝግጁ ናቸው


እርስዎ ከ ላይ ጠርዝ በኩል መተው የሚፈልጉትን ክፍተት መጠን ያስገቡ: ለ ተመረጠው እቃ እና ለ ማመሳከሪያ ነጥብ እርስዎ የ መረጡትን ሳጥን ውስጥ ይህ ምርጫ ዝግጁ የሚሆነው እርስዎ ከ መረጡ ነው የ "ከ ላይ" ወይንም "ከ ታች" (እንደ ባህሪ) በ ቁመት ሳጥን ውስጥ ነው

የ ማመሳከሪያ ነጥብ ይምረጡ ለ ተመረጠው የ ቁመት ማሰለፊያ ምርጫ

የ ጽሁፉን ፍሰት መከተያ

በ ረቂቅ ድንበሮች ውስጥ የ ተመረጠውን እቃ መጠበቂያ በ ጽሁፍ እቃ ማስቆሚያ ውስጥ: ወደ ተመረጠው ማንኛውም ቦታ ለ ማድረግ በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ: ይህን ምርጫ አይምረጡ

በ ነባር የ ጽሁፍ ፍሰት መከተያ ምርጫ ይመረጣል: እርስዎ ሰነድ በሚከፍቱ ጊዜ በ መጻፊያ አሮጌ እትም ከ OpenOffice.org 2.0. ነገር ግን: ይህ ምርጫ አይመረጥም ወይንም እርስዎ በሚከፍቱ ጊዜ በ Microsoft Word format (*.doc).

የ ቅድመ እይታ ሜዳ

አሁን የተመረጠውን በቅድመ እይታ ማሳያ

አረንጓዴ አራት ማእዘን የሚወክለው የ ተመረጠውን እቃ ነው እና ቀይ አራት ማእዘን የሚወክለው የ ማሰለፊያ ማመሳከሪያ ነጥብ ነው: እርስዎ እቃውን ካስቆሙ እንደ ባህሪ: ማመሳከሪያው አራት ማእዘን ወደ ቀይ መስመር ይቀየራል

አቀራረብ - መጨረሻ

አቀራረብ - ማሰለፊያ