ማውጫ

የሚቀጥለው ምርጫ ዝግጁ የሚሆነ ሲመርጡ ነው ሰንጠረዥ ማውጫ እንደ የ ማውጫ አይነት

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ማስገቢያ - የ ሰንጠረዥ ማውጫ እና ማውጫ - የ ሰንጠረዥ ማውጫ: ወይንም የ ጽሁፎች ዝርዝር - አይነት tab (የ ማውጫ ሰንጠረዥ አይነት በሚመረጥበት ጊዜ)


አይነት እና አርእስት

ይወስኑ አይነት እና አርእስት ለ ማውጫ

አይነት

እርስዎ ማስገባት የሚፈልጉትን አይነት ማውጫ ይምረጡ ዝግጁ የሆኑ ምርጫዎች ለዚህ tab እርስዎ እንደ መረጡት አይነት ማውጫ ይወሰናል: መጠቆሚያው በ ማውጫ ውስጥ ከሆነ እርስዎ ሲመርጡ የ ማስገቢያ - ማውጫዎች እና ሰንጠረዦች – ማውጫዎች እና ሰንጠረዦች ወይንም የ ጽሁፎች ዝርዝር እርስዎ ማውጫ ማረም ይችላሉ

አርእስት

ለተመረጠው ማውጫ አርእስት ያስገቡ

በ እጅ እንዳይቀየር መጠበቂያ

የ ማውጫ ይዞታ እንዳይቀየር መከልከያ እርስዎ በ ማውጫው ላይ በ እጅ የ ቀየሩት ይጠፋል ማውጫው በሚነቃቃ ጊዜ: እርስዎ መጠቆሚያው እንዲሸበለል ከፈለጉ በሚጠበቁ ቦታዎች በሙሉ: ይምረጡ - LibreOffice መጻፊያ - የ አቀራረብ እርዳታ እና ከዛ ይምረጡ የ መጠቆሚያ ማስቻያ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን በሚጠበቁ ቦታዎች ክፍል ውስጥ

ማውጫ መፍጠሪያ ለ

ይምረጡ ማውጫ የሚፈጠረው ለ ሰነዱ ነው ወይንስ ለ አሁኑ ምእራፍ

መፍጠሪያ ከ

ማውጫ ለ መፍጠር አብሮ የሚቀላቀለውን መረጃ ይወስኑ

የ መግለጫ ጽሁፍ

ከ እቃ መግለጫ ውስጥ የ ማውጫ ማስገቢያ መፍጠሪያ መግለጫ ወደ እቃ ውስጥ ለ መጨመር: እቃ ይምረጡ: እና ከዛ ይምረጡ መግለጫ - ማስገቢያ

ምድብ

ይምረጡ የ መግለጫ ምድብ እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን ለ ማውጫ ማስገቢያ

ማሳያ

ይምረጡ የ መግለጫ ክፍል እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን ለ ማውጫ ማስገቢያ የሚቀጥሉት የ ስንጠረዥ ዝርዝር ምርጫ ይታያል: የ መግለጫ ጽሁፉን መሰረት ያደረገ ጽሁፍ "ማብራሪያ24: ፀሐይ" ይህ "ማብራሪያ24" ራሱ በራሱ ይመነጫል እና "ፀሐይ" በ ተጠቃሚው ተጨምሯል

የ ማሳያ ሳጥን ዝርዝር ምርጫዎች

ማውጫ ውስጥ ማስገቢያ

ማመሳከሪያ ጽሁፍ

ማብራሪያ 24: ፀሐይ

ምድብ እና ቁጥር

ማብራሪያ 24

የ መግለጫ ጽሁፍ

ፀሃይ


እርስዎ ከ መረጡ የ "መግለጫ ጽሁፍ", ስርአተ ነጥብ እና ክፍተት በ መግለጫ መጀመሪያ ላይ አይታይም በ ማውጫ ማስገቢያ ላይ

የ እቃው ስሞች

የ ማውጫ ማስገቢያ ከ እቃ ስም መፍጠሪያ እርስዎ የ እቃ ስም በ መቃኛ ማየት ይችላሉ: ለምሳሌ: እና በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ መቀየር ይችላሉ