ማረሚያ

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉት ትእዛዞች የሚጠቅሙት መቀመሪያ ለ ማረም ነው: በ ተጨማሪ መሰረታዊ ትእዛዞች (ለምሳሌ: ይዞታዎችን ኮፒ ማድረግ) ለ ተወሰኑ ተግባሮች አሉ ለ LibreOffice ሂሳብ እንደ መፈለጊያ የ ቦታ ያዢዎች ወይንም ስህተቶች

መተው

መጨረሻ የሰሩትን ወይንም መጨረሻ ጽፈው ያስገቡትን መገልበጫ: እርስዎ ይምረጡ መገልበጥ የሚፈልጉትን: ይጫኑ ቀስቱ ላይ በ መተው ምልክት በ መደበኛ መደርደሪያ ላይ

እንደገና መስሪያ

መጨረሻ የ ሰሩትን መገልበጫ መተው ትእዛዝ: ለ መምረጥ የ መተው ደረጃን እርስዎ መገልበጥ የሚፈልጉትን: ይጫኑ ቀስቱ ላይ የ እንደገና መስሪያ ምልክት አጠገብ ያለውን በ መደበኛ እቃ መደርደሪያ ላይ

መቁረጫ

ማስወገጃ እና ኮፒ ማድረጊያ የተመረጠውን ወደ ቁራጭ ሰሌዳ

ኮፒ

የተመረጠውን ወደ ቁራጭ ሰሌዳ ኮፒ ማድረጊያ

መለጠፊያ

መጠቆሚያው ባለበት ቦታ የ ቁራጭ ሰሌዳ ይዞታ ማስገቢያ: እና የ ተመረጠውን ጽሁፍ ወይንም እቃዎች መቀየሪያ

ሁሉንም መምረጫ

የ አሁኑን ፋይል ጠቅላላ ይዞታ ክፈፍ: ወይንም የ ጽሁፍ እቃ መምረጫ

የሚቀጥለው ምልክት

መጠቆሚያውን ወደሚቀጥለው ምልክት ማንቀሳቀሻ (ወደ ቀኝ).

ቀደም ያለው ምልክት

መጠቆሚያውን ቀደም ወዳለው ምልክት ማንቀሳቀሻ (ወደ ግራ).

የሚቀጥለው ስህተት

መጠቆሚያውን ወደሚቀጥለው ስህተት ማንቀሳቀሻ (ወደ ቀኝ ማንቀሳቀሻ).

ቀደም ያለው ስህተት

መጠቆሚያውን ቀደም ወዳለው ስህተት ማንቀሳቀሻ (ወደ ግራ ማንቀሳቀሻ).