ፋይል
ይህ ዝርዝር የያዛቸው ባጠቃላይ ትእዛዞች በ መቀመሪያ ሰነዶች ውስጥ ለ መስራት ነው እንደ መክፈት ማስቀመጥ እና ማተም
መፍጠሪያ አዲስ LibreOffice ሰነድ
የ አካባቢ ወይንም የ ሩቅ ፋይል መክፈቻ: ወይንም ማምጫ
በቅርብ ጊዜ የተከፈቱ ፋይሎች ዝርዝር: ፋይል ለ መክፈት ከ ዝርዝር ውስጥ ስሙ ላይ ይጫኑ
የ ንግድ እና የ ግል ደብዳቤዎች: ፋክሶች: አጄንዳዎች: ማቅረቢያዎች እና ተጨማሪዎች እንዴት እንደሚፈጥሩ ይመራዎታል
የ አሁኑን ሰነድ መዝጊያ ከ ፕሮግራሙ ሳይወጣ
የ አሁኑን ሰነድ በተለየ አካባቢ ማስቀመጫ: ወይንም በተለየ የ ፋይል ስም ወይንም አይነት ማስቀመጫ
ማሰቀመጫ ሁሉንም የ ተሻሻሉ LibreOffice ሰነዶች
የ አሁኑን ሰነድ መቀየሪያ: መጨረሻ ተቀምጦ በ ነበረው
ማሰቀመጫ እና ማደራጃ በርካታ እትሞች የ አሁኑን ሰነድ በ ተመሳሳይ ፋይል ውስጥ: እርስዎ መክፈት: ማጥፋት: እና ማወዳደር ይችላሉ ያለፉ እትሞችን
የ አሁኑን ሰነድ በተለየ ስም እና አቀራረብ እርስዎ በሚወስኑት አካባቢ ማስቀመጫ
የ አሁኑን ሰነድ ለ ተለያዩ መተግበሪያዎች ኮፒ መላኪያ
የ አሁኑን ፋይል ባህሪዎች ማሳያ: እንደ ስታስቲክስ የ ቃላት ቆጠራ እና ፋይሉ የተፈጠረበትን ቀን የመሳሰሉ
የ አሁኑን ሰነድ ማተሚያ: ምርጫ ወይንም እርስዎ መወሰን የሚፈልጉትን ገጽ: እርስዎ እንዲሁም ማስገባት ይችላሉ የ ማተሚያ ምርጫ ለ አሁኑ ሰነድ የ ማተሚያ ምርጫ ይለያያል እንደ ማተሚያው እና እርስዎ እንደሚጠቀሙት የ መስሪያ ስርአት አይነት
መዝጊያ ሁሉንም LibreOffice ፕሮግራሞች እና የ እርስዎን ለውጦች እንዲያስቀምጡ ይነግርዎታል ይህ ትእዛዝ በ Mac OS X ስርአት ውስጥ የለም