ዝርዝሮች

የ ዝርዝር መደርደሪያ የያዛቸው ትእዛዞች ለ መስሪያ ነው በ LibreOffice ሂሳብ: የያዛቸው በርካታ አንቀሳቃሽ እና እንዲሁም ትእዛዞች ነው ለ ማረም: ለ መመልከቻ: ለ ማዘጋጃ: ለ አቀራረብ: እና የ ሰነዶችን መቀመሪያ በርካታ የ ዝርዝር እና በውስጣቸው የተያዙትን እቃ ማተም ነው: በርካታ የ ዝርዝር ትእዛዞች ዝግጁ የሚሆኑት እርስዎ መቀመሪያ በሚፈጥሩ እና በሚያርሙ ጊዜ ነው

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ መስራት የሚፈልጉትን ሰነድ የያዘ መስኮት መመረጥ አለበት ዝርዝር ትእዛዙን ለ መጠቀም: በ ተመሳሳይ: እርስዎ እቃ መምረጥ አለብዎት በ ሰነዱ ውስጥ ዝርዝር ትእዛዙን ለ መጠቀም ከ እቃው ጋር የ ተዛመደውን


የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

ዝርዝር አገባብ sensitive ነው: ይህ ማለት እነዚህ ዝርዝር እቃዎች ዝግጁ የሚሆኑት አሁን ለሚሰሩት ስራ አስፈላጊ ሲሆኑ ነው: መጠቆሚያው በ ጽሁፍ አካባቢ ካለ: እነዚህ ሁሉም ዝርዝር እቃዎች ዝግጁ ይሆናሉ ጽሁፉን ለማረም: እርስዎ ንድፍ ከ መረጡ በ ሰነድ ውስጥ: ለ እርስዎ የ ንድፍ ማረሚያ ዘዴ ይታያል


ፋይል

ይህ ዝርዝር የያዛቸው ባጠቃላይ ትእዛዞች በ መቀመሪያ ሰነዶች ውስጥ ለ መስራት ነው እንደ መክፈት ማስቀመጥ እና ማተም

ማረሚያ

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉት ትእዛዞች የሚጠቅሙት መቀመሪያ ለ ማረም ነው: በ ተጨማሪ መሰረታዊ ትእዛዞች (ለምሳሌ: ይዞታዎችን ኮፒ ማድረግ) ለ ተወሰኑ ተግባሮች አሉ ለ LibreOffice ሂሳብ እንደ መፈለጊያ የ ቦታ ያዢዎች ወይንም ስህተቶች

መመልከቻ

የ ማሳያ መጠን እና መግለጫ ማሰናጃ: የትኛው አካል እንደሚታይ እርስዎ ይወስኑ: በርካታ ትእዛዞች እርስዎ የሚያስገቡት ወደ ትእዛዞች መስኮት ውስጥ መድረስ ይቻላል በ አይጥ መጠቆሚያ በ መጫን እርስዎ ቀደም ብለው የ አካላቶች ክፍል ከፍተው ከ ነበረ: በ መመልከቻ - አካላቶች.

አቀራረብ

ይህ ዝርዝር የያዛቸው ትእዛዞች ለ መቀመሪያ አቀራረብ አስፈላጊ ናቸው

መሳሪያዎች

ይህን ዝርዝር ይጠቀሙ የ ምልክቶች መዝገብ ለ መክፈት እና ለ ማረም: ወይንም ተጨማሪ መቀመሪያ ለማምጣት እንደ የ ዳታ ፋይል ወይንም በ ቁራጭ ሰሌዳ: የ ፕሮግራሙን ገጽታ ማስተካከል ይቻላል የ እርስዎን ፍላጎት እንዲያሟላ: እርስዎ እንዲሁም የ ፕሮግራሙን ምርጫ መቀየር ይችላሉ

መስኮት

በ መስኮት ዝርዝር ውስጥ አዲስ መስኮት መክፈት እና የ ሰነድ ዝርዝር ማየት ይችላሉ

እርዳታ

የ እርዳታ ዝርዝር የሚያስችለው ማስጀመር እና መቆጣጠር ነው የ LibreOffice እርዳታ ስርአት