ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ መፍጠሪያ

እርስዎ መፍጠር ይችላሉ የ ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ የ እርስዎን አድማጮች እንደሚያስደስት አድርገው: ተንሸራታቾችን በ መጠቀም በ አሁኑ ማቅረቢያ ውስጥ

ተንሸራታች ማስያ ማስተካከያ ለመፍጠር:

  1. ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ

  2. ይጫኑ አዲስ እና ያስገቡ ስም ለ እርስዎ ተንሸራታች በ ስም ሳጥን ውስጥ

  3. በቅድሚያ ከ ነበረው ተንሸራታች ውስጥ ይምረጡ ወደ እርስዎ ተንሸራታች መጨመር የሚፈልጉትን: እና ከዛ ይጫኑ የ >> ቁልፍ፡ ተጭነው ይያዙ Shift ቁልፍ የ ተንሸራታች መጠን ለመምረጥ ወይንም Ctrl በርካታ ተንሸራታቾች ለመምረጥ

እርስዎ የ ተንሸራታች ቅደም ተከተል መቀየር ይችላሉ በ እርስዎ የ ተንሸራታች ማስተካከያ ማሳያ ውስጥ: በ መጎተት እና በ መጣል ተንሸራታቹን በ ተመረጠው ተንሸራታች ስር

ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ ለ ማስጀመር:

  1. ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ

  2. ከ ዝርዝር ውስጥ በ መጀመሪያ ማሳየት የሚፈልጉትን ይምረጡ

  3. ይጫኑ ማስጀመሪያ

የ ምክር ምልክት

እርስዎ ከ ፈለጉ የተመረጠው ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ እንዲጀምር እርስዎ በ ሚጫኑ ጊዜ የ ተንሸራታች ማሳያ ምልክት በ ማቅረቢያ እቃ መደርደሪያ ላይ: ወይንም እርስዎ ሲጫኑ F5, ይምረጡ ይጠቀሙ ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ


ተንሸራታች ማሳያ ለማስኬድ ምርጫዎች

ሁል ጊዜ ተንሸራታች ማሳያ ከ አሁኑ ተንሸራታች እንዲጀምር:

  1. ይምረጡ - LibreOffice ማስደነቂያ - ባጠቃላይ.

  2. ማቅረቢያ ማስጀመሪያ ቦታ ይምረጡ የ ሁል ጊዜ በ አሁኑ ገጽ ይጀምር ሳጥን ውስጥ ምልክት ያድርጉ

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

የ ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ ማስኬድ ከፈለጉ ይህን ምርጫ አይምረጡ


ተንሸራታች ለመደበቅ:

የ አሁኑን ተንሸራታች ለ መደበቅ፡ ይጫኑ የ ተንሸራታች መደበቂያ ቁልፍ ይጫኑ

  1. በርካታ ተንሸራታቾች ለ መደበቅ ይምረጡ መመልከቻ - ተንሸራታች መለያ እና ከዛ ይምረጡ ተንሸራታች(ቾች) መደበቅ የሚፈልጉትን

  2. ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማስያ/መደበቂያ

    ተንሸራታቹ ከሰነዱ ውስጥ አልተወገደም

የ ተደበቀ ተንሸራታች ለማሳየት:

  1. ይምረጡ መመልከቻ - ተንሸራታች መለያ እና ከዛ ይምረጡ ተንሸራታች(ቾች) ማሳየት የሚፈልጉትን

  2. ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማስያ/መደበቂያ