የተንሸራታች ቅደም ተከተል መቀየሪያ
ከ እነዚህ አንዱን ይስሩ:
-
ይምረጡ መመልከቻ - ተንሸራታች መለያ ይምረጡ አንድ ወይንም ክዚያ በላይ ተንሸራታቾች: እና ከዛ ተንሸራታቾቹን ይጎትቱ ወደ ሌላ አካባቢ: በርካታ ተንሸራታቾች ለ መምረጥ: ተጭነው ይያዙ shift ቁልፍ እና ይጫኑ በ ተንሸራታቾች ላይ: የ ተመረጠውን ተንሻራታች ኮፒ ለ መፍጠር: ተጭነው ይያዙ Ctrl ቁልፍ በሚጎትቱ ጊዜ: የ አይጥ መጠቆሚያው ይቀየራል ወደ መደመሪያ ምልክት: እርስዎ እንዲሁም መጎተት ይችላሉ የ ተንሸራታች ኮፒ ወደ ሌላ የተከፈተ LibreOffice ማስደነቂያ ሰነድ ውስጥ
-
ይምረጡ መመልከቻ - ረቂቅ ተንሸራታች ይምረጡ እና ተንሸራታቹን ወደ ሌላ ቦታ ይጎትቱ
-
ይምረጡ መመልከቻ - መደበኛ ወይንም ማስታወሻ የተንሸራታች ቅድመ እይታን ይምረጡ ከ ተንሸራታች ክፍል እና የተንሸራታቹን ቅድመ እይታ ወደ ሌላ ቦታ ይጎትቱ
ከ ማቅረቢያ ውስጥ ተንሸራታች ለጊዜው ለ ማስወገድ: ይሂዱ ወደ ተንሸራታች መለያ ተንሸራታቹን በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ/መደበቂያ የሚደበቀው ተንሸራታች ቁጥር ይሰረዛል: ተንሸራታቹን ለማሳየት ተንሸራታቹን በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ/መደበቂያ