ተንሸራታች ማሳያ ማሰናጃዎች

ለ እርስዎ ተንሸራታች ማሳያ ማሰናጃ መግለጫ: እንዲሁም ተንሸራታቹ ከ የት እንደሚጀምር: ተንሸራታቹ እንዴት እንደሚቀጥል: የ ማቅረቢያው አይነት: እና የ መጠቆሚያ ምርጫ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማሳያ ማሰናጃዎች


መጠን

በ ተንሸራታች ማሳያ ውስጥ የትኞቹ ተንሸራታቾች እንደሚካተቱ መወሰኛ

ሁሉንም ተንሸራታቾች

በ እርስዎ ተንሸራታች ማሳያ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ተንሸራታቾች ያካትታል

ከ:

እንዲጀምር የሚፈጉትን የ ተንሸራታች ቁጥር ያስገቡ

ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ

የ ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ ማስኬጃ እርስዎ በ ገለጹት ደንብ መሰረት ተንሸራታች ማሳያ - ተንሸራታች ማሳያ ማስተካከያ :

የ ማቅረቢያ ዘዴ

የ ተንሸራታች ማሳያ አይነት ይምረጡ

በ ሙሉ መመልከቻ

ተንሸራታች በ ሙሉ መመልከቻ ዘዴ ማሳያ

በ መስኮት ውስጥ

ተንሸራታች ማሳያ በ LibreOffice ፕሮግራም መስኮት

ዙር እና መደገሚያ በኋላ

እንደገና ማስጀመሪያ እርስዎ ከ ወሰኑት ትንሽ እረፍት በኋላ: የ ትንሽ እረፍት ተንሸራታች ይታያል ይታያል በ ዋናው ተንሸራታች እና በ ተንሸራታች ማስጀመሪያ መካከል: ይጫኑ መዝለያ ቁልፍ ትእይንቱን ለ ማስቆም

የሚቆይበት ጊዜ

ተንሸራታቹ ከ መደገሙ የሚያርፍበትን ጊዜ ያስገቡ: እርስዎ ዜሮ ካስገቡ: ትእይንቱ ወዲያውኑ እንደገና ይጀምራል ምንም የ እረፍት ተንሸራታች ሳያሳይ

አርማ ማሳያ

ማሳያ LibreOffice አርማ በ ማቅረቢያ እረፍት መካከል ምልክቱን መቀያየር አይቻልም

ምርጫዎች

ተንሸራታች በእጅ መቀየሪያ

ተንሸራታች ራሱ በራሱ በፍጹም አይቀይርም ይህን ሳጥን ሲመረጡ

የአይጥ መጠቆሚያ የሚታይ

የአይጥ መጠቆሚያ ይታይ ተንሸራታች በሚታይ ጊዜ

የአይጥ መጠቆሚያ እንደ ብዕር

የ አይጥ መጠቆሚያውን ወደ ብዕር መቀየሪያ: የ ተንሸራታች ትርኢት በሚያሳዩ ጊዜ በ ተንሸራታቹ ላይ መጻፍ ይችላሉ እንዲሁም የመጻፊያውንም ቀለም መቀያየር ይችላሉ

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ በ ብዕር የጻፉት ማንኛውም ነገር በ እርስዎ ተንሸራታች ላይ ከ ተንሸራታች ትእይንት ሲወጡ ይታያል: የ ብዕር ባህሪዎች መቀየር ይቻላል በ መምረጥ የ ብዕር ስፋት ወይንም የ ብዕር ቀለም መቀየሪያ ትእዛዝ በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ: ተንሸራታች በሚያሳዩ ጊዜ


እንቅስቃሴ የተፈቀደ

ሁሉንም ክፈፎች ማሳያ የ እንቅስቃሴ GIF ፋይሎች ተንሸራታች በሚታይ ጊዜ ይህ ምርጫ ካልተመረጠ: የ መጀመሪያው ክፈፍ ብቻ የ እንቅስቃሴ GIF ፋይል ይታያል

የተንሸራታቹን መደብ በመጫን መቀየሪያ

እርስዎ የ ተንሸራታቹን መደብ በሚጫኑ ጊዜ ወደሚቀጥለው ተንሸራታች መሄጃ

ማቅረቢያው ሁልጊዜ ከ ላይ

የ LibreOffice መስኮት ከላይ ይታያል በሚያቀርቡ ጊዜ: የ ሌላ ምንም ፕሮግራም መስኮት ከ ማቅረቢያ ፊት ለ ፊት አይታይም

በርካታ ማሳያዎች

በ ነባር ቀዳሚ መመልከቻ ይጠቀማል ለ ተንሸራታች ማሳያ ዘዴ: የ አሁኑ ዴስክቶፕ የሚታይ ከሆነ ከ አንድ በላይ ማሳያ ውስጥ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ የትኛውን ማሳያ በ ሙሉ መመልከቻ ተንሸራታች ማሳያ ዘዴ እንደሚጠቀሙ: የ አሁኑ ዴስክቶፕ አንድ ማሳያ ብቻ ካለው ወይንም በርካታ የ ማሳያ ዘዴ የ ተደገፈ ካልሆነ በ አሁኑ ስርአት ውስጥ: እርስዎ ሌላ መመልከቻ መምረጥ አይችሉም

ማቅረቢያ ማሳያ

ይምረጡ ማሳያ ተንሸራታች በ ሙሉ መመልከቻ ዘዴ ለማሳየት

ስርአቱ የሚያስችል ከሆነ ተጠቃሚውን መስኮቱን ማስፋት ይችላል በ ሁሉም ዝግጁ ማሳያዎች ውስጥ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ "ሁሉንም ማሳያዎች" በዚህ ጊዜ ማቅረቢያ ይታያል በ ሁሉም ዝግጁ ማሳያዎች ውስጥ

የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ ማሰናጃ የሚቀመጠው በ ተጠቃሚ ማወቀሪያ ውስጥ ነው እና በ ሰነድ ውስጥ አይደለም