መቀመሪያ

የ መቀመሪያ አገባብ ምርጫ መግለጫ እና መጫኛ ምርጫ ለ LibreOffice ሰንጠረዥ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

የ ሰንጠረዥ ሰነድ መክፈቻ ይምረጡ - LibreOffice ሰንጠረዥ - መቀመሪያ


የ መቀመሪያ ምርጫ

የ መቀመሪያ አገባብ

ሶስት ምርጫዎች አሉ: በ ምሳሌ እንያቸው: በ ናሙና ሰንጠረዥ ውስጥ ሁለት የ ስራ ወረቀቶች አሉ ወረቀት1 እና ወረቀት2 በ A1 ክፍል በ ወረቀት1 ማመሳከሪያ አለ ለ C4 ክፍል በ ወረቀት2. ውስጥ

የ እንግሊዝኛ የ ተግባር ስሞችን ይጠቀሙ

የ LibreOffice ሰንጠረዥ ተግባር ስሞችን መተርጎም ይቻላል: በ ነባር የ ምልክት ማድረጊያ ሳጥኑ ይጠፋል: ይህ ማለት የ ተግባር ትርጉም ስሞች እየተጠቀመ ነው ማለት ነው: እዚህ ሳጥን ውስጥ ምልክት ካደረጉ ይቀይረዋል የ ተግባር ትርጉም ስሞች ወደ እንግሊዝኛው: ይህ ለውጥ ተፅእኖ የሚፈጥረው በ ሁሉም በሚቀጥሉት ቦታዎች ነው: በ መቀመሪያ ማስገቢያ እና ማሳየ ውስጥ: የ ተግባር አዋቂ: እና የ መቀመሪያ ምክሮ ውስጥ ነው: እርስዎ ምልክቱን በ ማጥፋት ወደ የ ተግባር ትርጉም ስሞች መመለስ ይችላሉ

መለያያዎች

ይህ የ ምርጫ ቡድን እርስዎን የሚያስችለው መለያያዎችን ለማሰናዳት ነው በ እርስዎ መቀመሪያ መግለጫ ውስጥ: ይህ በጣም አስፈላጊ ነው: ለምሳሌ: እርስዎ መለያየት ይፈልጋሉ የ ተግባር ደንቦችን በ ኮማ (,) ከ ሴሚኮለን (;) ይልቅ

ለምሳሌ: ይህን ከ መጻፍ ይልቅ የ =ድምር(A1;B1;C1) እርስዎ መጻፍ ይችላሉ =ድምር(A1,B1,C1).

በተጨማሪ: እርስዎ መቀየር ይችላሉ የ አምድ እና ረድፍ መለያያዎች ለ መስመር-ውስጥ መለያዎች: ቀደም ብለው: የ መስመር-ውስጥ መለያ የሚጠቀመው ሴሚ ኮለን (;) ነው እንደ አምድ መለያያ እና የ ቧንቧ ምልክቶች (|) እንደ ረድፍ መለያያ: ስለዚህ ይህ አይነት የ መስመር-ውስጥ መለያ መግለጫ ይህን ይመስላል ለ 5 x 2 matrix array:

={1;2;3;4;5|6;7;8;9;10}

በ መቀየር የ አምድ መለያያ በ ኮማ (,) እና የ ረድፍ መለያያ በ ሴሚኮሌን (;): ተመሳሳይ መግለጫ ይህን ይመስላል:

={1,2,3,4,5;6,7,8,9,10}

ዝርዝር ማስሊያ ማሰናጃዎች

እዚህ እርስዎ ማሰናዳት ይችላሉ የ መቀመሪያ አገባብ ማመሳከሪያዎች በሚተነትኑ ጊዜ ለ ተሰጠው ሀረግ ደንቦች: ይህ ተጽእኖ ይፈጥራል አብሮ-የተገነባ ተግባሮች እንደ በ ተዘዋዋሪ ማመሳከሪያ ለሚወስዱ እንደ ሀረግ ዋጋ

ፋይል በሚጫን ጊዜ እንደገና ማስሊያ

መቀመሪያ እንደገና ማስላት በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል በጣም ትልልቅ ፋይሎችን በሚጫኑ ጊዜ

Excel 2007 እና አዲስ:

ትልቅ የ ሰንጠረዥ ፋይል መጫን ረጅም ጊዜ ይወስዳል: እርስዎ ማሻሻል ካልፈለጉ የ እርስዎን ትልቅ የ ሰንጠረዥ ዳታ: እርስዎ ማስተላለፍ ይችላሉ እንደገና ማስሊያውን ለ ሌላ ጊዜ: LibreOffice ይህ እርስዎን የሚያስችለው እንደገና ማስላቱን ማዘግየት ነው ለ Excel 2007 (እና ከዛ በላይ) ሰንጠረዥ የ መጫኛ ጊዜውን ለማፍጠን

ODF ሰንጠረዥ (አልተቀመጠም በ LibreOffice):

የ ቅርብ ጊዜ እትሞች LibreOffice ያጠራቅማል በ ሰንጠረዥ መቀመሪያ ውጤቶች ወደ ODF ፋይል ውስጥ: ይህ ገጽታ ይረዳል LibreOffice እንደገና ለማስላት ትልቅ የ ODF ሰንጠረዥ ፋይል የ ተቀመጠ LibreOffice በፍጥነት

የ ODF ሰንጠረዥ የ ተቀመጠ በሌላ ፕሮግራሞች: እነዚህ የ ተቀመጡ መቀመሪያ ውጤቶች ካልተገኙ: እንደገና ማስላት ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ይቻላል ለማፍጠን ፋይል መጫኛውን በ Excel 2007 ፋይሎች

ከ ላይ ላለው ማስገቢያ የሚቀጥሉት ምርጫዎች ዝግጁ ናቸው:

የ ምክር ምልክት

LibreOffice የ ተቀመጠ ODF ሰንጠረዥ ያከብራል በፍጹም እንደገና አታስላ እና ሁልጊዜ እንደገና አስላ ምርጫዎችን