የ መተግበሪያ ቀለሞች

ቀለሞች ማሰናጃ ለ LibreOffice ተጠቃሚ ገጽታ እርስዎ የ አሁኑን ማሰናጃ እንደ ገጽታ ማስቀመጫ እና በኋላ መጫን ይችላሉ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ - LibreOffice - የ መተግበሪያ ቀለም


መድረሻ በ LibreOffice

የ ቀለም ገጽታ

የ ቀለም ገጽታዎች ማስቀመጫ እና ማጥፊያ

ገጽታ

መጠቀም የሚፈልጉትን የ ገጽታ ቀለም ይምረጡ

ማስቀመጫ

የ አሁኑን ማሰናጃ እንደ ገጽታ ማስቀመጫ እና በኋላ መጫኛ ስሙ ይጨመራል ወደ ገጽታ ሳጥን ውስጥ

የ ቀለም ገጽታ ስም

ስም ያስገቡ ለ ቀለም እቅድ

ማጥፊያ

የሚታየውን የ ቀለም ገጽታ ማጥፊያ ከ ገጽታ ሳጥን ውስጥ: እርስዎ ነባር ገጽታ ማጥፋት አይችሉም

ገጽታ

ለ ተጠቃሚ ገጽታ አካሎች ቀለም ይምረጡ

በ ተጠቃሚ ገጽታ አካል ላይ ቀለም ለ መፈጸም: እርግጠኛ ይሁኑ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን ከ ስሙ በፊት ምልክት እንደ ተደረገበት: የ ተጠቃሚ ገጽታ አካል ለ መደበቅ ምልክቱን ያጽዱ

የ ማስታወሻ ምልክት

አንዳንድ የ ተጠቃሚ ገጽታ አካላቶችን መደበቅ አይቻልም


የ ማስታወሻ ምልክት

የ መጠቆሚያ መመልከቻውን ለማሻሻል: ተጠቃሚው የ መተግበሪያ መደብ ቀለም ካሰናዳ በ 40% እና 60% ግራጫ መካከል: ራሱ በራሱ ወደ 40% ግራጫ ይቀየራል


ራሱ በራሱ ቀለም ማሰናጃ የ ተጠቃሚ ገጽታ አካሎችን ይቀይራል ወደ ነበረበት ቀለም ከ ቀለም ገጽታ ውስጥ

የ ቀለም ማሰናጃ ለ "ተጎበኙ አገናኞች" እና "ላልተጎበኙ አገናኞች" የሚፈጸመው ማሰናጃው ከ ተፈጸመ በኋላ ለ ተፈጠሩ ሰነዶች ብቻ ነው