የ ፎርም መቃኛ መደርደሪያ

ፎርም መቃኛ መደርደሪያ የያዛቸው ምልክቶች የ ዳታቤዝ ሰንጠረዥ ለማረም ነው ወይንም የ ዳታ መመልከቻ መቆጣጠሪያ ነው: መደርደሪያው የሚታየው በ ሰነዱ ከ ታች በኩል ነው ሜዳዎች እንደ አገናኝ በ ዳታቤዝ ውስጥ የያዘ

መጠቀም ይችላሉ የ ፎርም መቃኛ መደርደሪያ በ መዝገቦች ውስጥ ለማንቀሳቀስ እንዲሁም መዝገቦችን ለማስገባት እና ለማጥፋት: ዳታ በ ፎርም ዘዴ ከተቀመጠ ለውጦቹ በሙሉ ወደ ዳታቤዝ ይተላለፋሉ: የ ፎርም መቃኛ መደርደሪያ ለ ዳታ መዝገቦች መለያ: ማጣሪያ እና የ መፈለጊያ ተግባሮች ይዟል

የ ምክር ምልክት

እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የ መቃኛ መደርደሪያ ምልክት በ ተጨማሪ መቆጣጠሪያ መደርደሪያ ላይ በ ፎርሙ ላይ የ መቃኛ መደርደሪያ ለ መጨመር


የ ማስታወሻ ምልክት

የ መቃኛ መደርደሪያ የሚታየው ከ ዳታቤዝ ጋር ለተገናኙ ፎርሞች ነው: የ ንድፍ መመልከቻ ለ ፎርም: የ መቃኛ መደርደሪያ አልተገኘም: ይህን ይመልከቱ የ ሰንጠረዥ ዳታ መደርደሪያ


እርስዎ መቆጣጠር ይችላሉየ ዳታ መመልከቻን በ መለያ እና ማጣሪያ ተግባሮች: ዋናው ሰንጠረዥ አይቀየርም

የ አሁኑ መለያ ደንብ ወይንም ማጣሪያ በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ ተቀምጧል፡ ማጣሪያ ከተሰናዳ የ ማጣሪያ መፈጸሚያ ምልክት በ መቃኛ መደርደሪያ ላይ ንቁ ይሆናል መለያ እና ማጣሪያ ገጽታዎች በ ሰነዱ ውስጥ ማዋቀር ይቻላል በ ፎርም ባህሪዎች ንግግር ውስጥ (ይምረጡ የ ፎርም ባህሪዎች - ዳታ - ባህሪዎች መለያ እና ማጣሪያ )

የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ የ SQL አረፍተ ነገር የ ፎርም መሰረት ነው (ይመልከቱ የ ፎርም ባህሪዎች - tab ዳታ - የ ዳታ ምንጭ ) እና ከዛ ማጣሪያ እና መለያ ተግባሮች ዝግጁ ይሆናሉ የ SQL አረፍተ ነገር የሚያመሳክረው አንድ ሰንጠረዥ ነው እና በ native SQL ዘዴ የ ተጻፈ አይደለም


ፍጹም መዝገብ

የ አሁኑን መዝገብ ቁጥር ማሳያ: ቁጥር ያስገቡ ወደ ተመሳሳዩ መዝገብ ለመሄድ

የ መጀመሪያው መዝገብ

ምልክት

ወደ መጀመሪያው መዝገብ ይወስዶታል

ቀደም ያለው መዝገብ

ምልክት

ቀደም ወዳለው መዝገብ ይወስዶታል

የሚቀጥለው መዝገብ

ምልክት

ወደ የሚቀጥለው መዝገብ ይወስዶታል

የ መጨረሻው መዝገብ

ምልክት

ወደ መጨረሻው መዝገብ ይወስዶታል

መዝገብ ማስቀመጫ

ምልክት

አዲስ የ ዳታ ማስገቢያ ማስቀመጫ: ለውጡ በ ዳታቤዝ ውስጥ ይመዘገባል

መተው: ዳታ ማስገባቱን

ምልክት

የ ዳታ ማስገቢያውን መተው ያስችሎታል

አዲስ መዝገብ

ምልክት

አዲስ መዝገብ ይፈጥራል

መዝገብ ማጥፊያ

ምልክት

መዝገብ ማጥፊያ: ጥያቄ መዝገብ ከማጥፋቱ በፊት ማረጋገጫ ይጠይቃል

ማነቃቂያ

የሚታየውን ዳታ ማነቃቂያ በ በርካታ-ተጠቃሚዎች አካባቢ: የሚታየውን ዳታ ማነቃቃት ዳታውን ዘመናዊ ያደርገዋል

ምልክት

ማነቃቂያ

መዝገብ መፈለጊያ

መፈለጊያ ከ ዳታ ሰንጠረዥ እና ፎርሞች ውስጥ በ ፎርሞች ወይንም ዳታቤዝ ሰንጠረዦች ውስጥ እርስዎ መፈለግ ይችላሉ በ ሙሉ የ ዳታቤዝ ሜዳዎች: ዝርዝር ሳጥኖች: እና ምልክት ማድረጊያ ሳጥኖች ውስጥ ለ ተወሰኑ ዋጋዎች

ምልክት

መዝገብ መፈለጊያ

እየጨመረ በሚሄድ መለያ

የ ጽሁፍ ሜዳ የሚለየው በ ፊደል ቅደም ተከተል ነው: የ ቁጥር ሜዳ የሚለየው በ ቁጥር ነው

ምልክት

እየጨመረ በሚሄድ መለያ

እየቀነሰ በሚሄድ መለያ

የ ጽሁፍ ሜዳ የሚለየው በ ፊደል ቅደም ተከተል ነው: የ ቁጥር ሜዳ የሚለየው በ ቁጥር ነው

ምልክት

እየቀነሰ በሚሄድ መለያ

በራሱ ማጣሪያ

አሁን የተመረጠውን የ ዳታ ሜዳ ይዞታ መሰረት ባደረገ መዝገብ ማጣሪያ

ምልክት

በራሱ ማጣሪያ

ፎርም-መሰረት ያደረገ ማጣሪያ

የሚታይ ዳታ በ ተወሰነ መመዘኛ የ ዳታቤዝ ሰርቨር እንዲያጣራ መወሰኛ

ምልክት

ፎርም-መሰረት ያደረገ ማጣሪያ

መለያ

ለ ዳታ ማሳያ የ መለያ መመዘኛ መወሰኛ ማሳያ

ምልክት

የ መለያ ደንብ

እንደ ነበር መመለሻ ማጣሪያ/መለያ

የ ማጣሪያ ማሰናጃ መሰረዣ: በ አሁኑ ሰንጠረዥ ውስጥ እና ሁሉንም መዝገቦች ማሳያ

ምልክት

እንደ ነበር መመለሻ ማጣሪያ/መለያ

የ ዳታ ምንጭ እንደ ሰንጠረዥ

ተጨማሪ የ ሰንጠረዥ መመልከቻ ማስጀመሪያ በ መመልከቻ ዘዴ ውስጥ ሲሆኑ ይህ የ ዳታ ምንጭ ሰንጠረዥ እንደ ተግባር ይጀምራል: ለ እርስዎ ሰንጠረዥ ክ ፎርሙ በላይ ይታያል

ምልክት

የ ዳታ ምንጭ እንደ ሰንጠረዥ

ማጣሪያ መፈጸሚያ

በ ሰንጠረዡ የተጣረው እና ያልተጣራው መመልከቻ መካከል መቀያየሪያ

ምልክት

ማጣሪያ መፈጸሚያ