የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ

የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ንግግር ቴምፕሌት ያስተዳድራል እና አዲስ ቴምፕሌት በ መጠቀም ሰነድ መጀመር ያስችላል

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ዝርዝር ይምረጡ ፋይል - አዲስ - ቴምፕሌቶች

ዝርዝር ይምረጡ ፋይል – ቴምፕሌት – ቴምፕሌቶች አስተዳዳሪ

ያስገቡ +Shift+N በ ማንኛውም LibreOffice ክፍል ውስጥ

ይጫኑ የ ቴምፕሌቶች ቁልፍ በ ማስጀመሪያ ክፍል ውስጥ

ይምረጡ ማንኛውንም አይነት ቴምፕሌት ከ ቴምፕሌቶች ቁልፍ በ ማስጀመሪያ ክፍል ውስጥ


ቴምፕሌቶች የ ማረሚያ ጊዜ ይቀንሳሉ አዲስ ሰነድ በ ቅድሚያ-የተሞሉ ይዞታዎች እና አቀራረብ በ ማስጀመር: የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ እርስዎን የሚያስችለው የ ተደራጁ ቴምፕሌቶች ጋር መድረስ ነው በ LibreOffice.

LibreOffice የሚመጣው አብሮት-የተገነባ ቴምፕሌት ይዞ ነው: እርስዎ ሰነድ ማስደነቂያዎች: ሰንጠረዦች ወይንም ስእሎች ለ መፍጠር ሊጠቀሙበት ይችላሉ: እርስዎ መጠቀም ይችላሉ ዝግጁ ቴምፕሌቶች ከ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ውስጥ: እርስዎ የ ራስዎትን ቴምፕሌት መፍጠር ይችላሉ ወይንም በ መስመር ላይ መቃኘት ተጨማሪ ቴምፕሌቶች

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ ከ ከፈቱ የ LibreOffice መሀከል ማስጀመሪያ እና ሰነድ ወይንም መተግበሪያ ካልተከፈተ: የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ጋር በ ተለየ ሁኔታ መድረስ ይቻላል: Ctrl-Shift-N የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ይከፍታል: እንዲሁም መድረስ ይችላሉ በ መምረጥ ቴምፕሌት ከ ጎን መደርደሪያ ውስጥ: እና ከዛ ይምረጡ የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ


ዋናው መስኮት - ቴምፕሌት መምረጫ

ዝግጁ የሆኑ ቴምፕሌቶች በ ቅድመ እይታ ማሳያ በ ዋናው መስኮት ውስጥ ይታያል: እንደ እርስዎ መፈለጊያ እና ማጣሪያ ምርጫ: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ማንኛውም ቴምፕሌት ምልክት ላይ ለ መክፈት አዲስ ሰነድ ከ ቴምፕሌቱ ይዞታዎች እና አቀራረብ ጋር

መፈለጊያ

እርስዎ ቴምፕሌት መፈለግ ይችላሉ ጽሁፍ በ ማስገባት በ መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ ከ ላይ በ ግራ በኩል: ዋናው መስኮት የሚያሳየው የ ተገኘውን ቴምፕሌት ነው

ማጣሪያ

እርስዎ ማጣራት ይችላሉ ሁሉንም መተግበሪያዎች: ሰነዶች: ሰንጠረዦች ወይንም መሳያዎች በ መምረጥ ከሚዘረገፈው ምርጫ ውስጥ: ከ ላይ-መሀከል በኩል: በ ዋናው መስኮት የ ተጣራውን ቴምፕሌቶች ያሳያል

ምድቦች

ምድቦች ፎልደሮች ናቸው የ እርስዎ ቴምፕሌቶች የሚቀመጡበት: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ከ ነባር ምድቦች ውስጥ የ እኔ ቴምፕሌቶች: የ ንግድ ልውውጥ: MediaWiki, ሌሎች የ ንግድ ሰነዶች: የ ግል ልውውጥ እና ሰነዶች: ማቅረቢያዎች ወይንም ዘዴዎች: እርስዎ አዲስ ምድቦች መፍጠር ይችላሉ ለ እርስዎ የ ግል መጠቀሚያ: የ ማሰናጃውን ቁልፍ ይጠቀሙ የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ አዲስ ምድብ ለ መፍጠር

የ ማስታወሻ ምልክት

ምድቦች በ ምድብ ውስጥ አይፈቀድም


የ ማስታወሻ ምልክት

ቴምፕሌት ወደ ሌላ ፎልደር ውስጥ ለ መጨመር የ እኔ ቴምፕሌት ምድብ ውስጥ: ይምረጡ - LibreOffice - መንገድ እና መንገዱን ያስገቡ


ማሰናጃዎች

ይጫኑ በ ማሰናጃ ምልክት ላይ ከ ታች በ ግራ በኩል ያለውን ለ መክፈት ዝርዝር ማሰናጃ: ምርጫዎቹ አዲስ ምድብ መፍጠሪያ: ምድብ ማጥፊያ: ወይንም ማነቃቂያ ናቸው: ነባር ቴምፕሌት ለ አዲስ ሰነዶች ተቀይሮ ከሆነ: ተጨማሪ ምርጫ ወደ ነባሩ ወደ ፋክቶሪው እንደ ነበር መመለሻ ቴምፕሌት ዝግጁ ይሆናል

በ መስመር ላይ ቴምፕሌቶች መቃኛ

በ መስመር ላይ በርካታ ቴምፕሌቶች ለ መቃኘት: ይጫኑ የ አለም ምልክት ከ ታች በ ግራ በኩል በ መቃኛ መስኮት ውስጥ እና ቴምፕሌት ይፈልጉ በ https://templates.libreoffice.org.

መክፈቻ

በ ዋናው መስኮት ውስጥ ቴምፕሌት ይምረጡ እና በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ መክፈቻ: ማስገቢያ ይጫኑ ወይንም ሁለት ጊዜ ይጫኑ ይህን ቴምፕሌት በ መጠቀም አዲስ ሰነድ ለ መክፈት

ማረሚያ

በ ዋናው መስኮት ውስጥ ቴምፕሌት ይምረጡ እና በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ማረሚያ ቴምፕሌት ለ ማረም: ይህ ተግባር ዝግጁ የሚሆነው ለ ቴምፕሌት አብሮ ላልተገነባ-ነው

እንደ ነባር ማሰናጃ

በ ዋናው መስኮት ውስጥ ቴምፕሌት ይምረጡ እና በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ማሰናጃ ቴምፕሌት: እንደ ነባር ቴምፕሌት ለ ማሰናዳት: ይህ ተግባር በ ወፍራም አረንጓዴ ቀለም ይፈጥራል በ ቴምፕሌት ላይ እና ቴምፕሌቱ ራሱ በራሱ ይጫናል: አዲስ ሰነድ በሚፈጠር ጊዜ ተመሳሳይ መተግበሪያ በ መጠቀም:

የ ምክር ምልክት

ማመሳከሪያ ወደ መደበኛ ቴምፕሌት


እንደገና መሰየሚያ

በ ዋናው መስኮት ውስጥ ቴምፕሌት ይምረጡ እና በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ቴምፕሌት እንደገና መሰየሚያ: ቴምፕሌት እንደገና ለ መሰየም: ይህ ተግባር የ ንግግር ሳጥን ይፈጥራል እርስዎ አዲስ ስም ለ ቴምፕሌት የሚመርጡበት: አዲስ ስም ይጻፉ እና ይምረጡ ለ ቴምፕሌት: ስም ይጻፉ እና ይምረጡ እሺ ወይንም ይምረጡ መሰረዣ በ ቅድሚያ ወደ ተሰናዳው ስም ለ መመለስ

ማጥፊያ

በ ዋናው መስኮት ውስጥ ቴምፕሌት ይምረጡ እና ይጫኑ ማጥፊያ ቁልፍ: ወይንም በ ቀኝ-ይጫኑ እና ከዛ ይምረጡ ማጥፊያ ቴምፕሌት ለ ማጥፋት: ይህ ተግባር የ ንግግር ሳጥን ይፈጥራል እርስዎን ማረጋገጫ ይጠይቃል: እርስዎ ይምረጡ አዎ ለ ማጥፋት ወይንም አይ ለ መሰረዝ

ማንቀሳቀሻ

ይጫኑ የ ማንቀሳቀሻ ምርጫ ከ ታች በ ቀኝ በኩል ያለውን: እርስዎ ከ መረጡ በኋላ የሚንቀሳቀሰውን ቴምፕሌት ወደ ሌላ ምድብ: ነባር ቴምፕሌት ማንቀሳቀስ አይቻልም: ነገር ግን ኮፒ ይፈጠራል በ ሌላ ምድብ ውስጥ

መላኪያ

ይምረጡ ቴምፕሌት በ ዋናው መስኮት ውስጥ እና ከዛ ይጫኑ መላኪያ ቁልፍ ከ ታች በ ቀኝ በኩል ለ መላክ ቴምፕሌት ወደ ፎልደር በ እርስዎ ኮምፒዩተር ውስጥ.

ማምጫ

ይጫኑ የ ማምጫ ቁልፍ ከ ታች በ ቀኝ በኩል: እና ከዛ ይምረጡ ምድብ ቴምፕሌት ለ ማምጣት ከ እርስዎ ኮምፒዩተር ውስጥ ወደ ምድብ ከ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ውስጥ

ምሳሌዎች

ለምሳሌ 1 – የ ንግድ ደብዳቤ መፍጠሪያ

 1. መክፈቻ LibreOffice መጻፊያ

 2. ይጫኑ ++Shift+N ወይንም ይምረጡ ፋይል – አዲስ ቴምፕሌት ለ መክፈት ከ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ውስጥ

 3. ይጻፉ “የ ንግድ ደብዳቤ” በ መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ

 4. ይምረጡ አንዱን ቴምፕሌት ከ ዋናው መስኮት ውስጥ ሁለት ጊዜ-በመጫን ወይንም ይጫኑ tab ለ መምረጥ እና ከዛ ማስገቢያውን ይጫኑ

 5. ቴምፕሌቱን በ መጠቀም አዲስ ሰነድ ይፈጠራል: በ አዲስ ሁኔታ በ LibreOffice መጻፊያ ውስጥ

 6. ጽሁፍ እና አርማ እንደ አስፈለገ መቀየሪያ

ለምሳሌ 2 – ቲምፕሌት ማምጫ – የ ግል በጀት ሰንጠረዥ

 1. መክፈቻ LibreOffice ሰንጠረዥ

 2. ይጫኑ ++Shift+N ወይንም ይምረጡ ፋይል – አዲስ ቴምፕሌት ለ መክፈት ከ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ውስጥ

 3. ይጫኑ የ ቃል ምልክት ለ መቃኘት ቴምፕሌት በ መስመር ላይ

 4. የ ግል በጀት ቴምፕሌት መፈለጊያ: እና ከዛ ያውርዱ

 5. የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ይክፈቱ: እና የ ማምጫ ቁልፍ ይምረጡ

 6. አዲሱን ቴምፕሌት ላ ማስቀመጥ ምድብ ይምረጡ በ (ለምሳሌ: የ እኔ ቴምፕሌቶች)

 7. እርስዎ ያወረዱትን ቴምፕሌት በ ፎልደር ውስጥ መቃኛ: ይምረጡ እና ይጫኑ መክፈቻ

 8. እርስዎ በ መረጡት ምድብ ውስጥ ቴምፕሌቱ አሁን ዝግጁ ነው

ለምሳሌ 3 – LibreOffice ማስደነቂያ – ማቅረቢያ ቲምፕሌት

 1. መክፈቻ LibreOffice ማስደነቂያ

 2. የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ራሱ በራሱ ይከፈታል እርስዎ በሚከፍቱ ጊዜ LibreOffice ማስደነቂያ

 3. ለ እርስዎ ማቅረቢያ ቴምፕሌት ይምረጡ: ማጣሪያ በ ምድብ ወይንም በ መፈለጊያ

 4. ተጨማሪ ገጽታዎች ዝግጁ አይደሉም: እና እርስዎ መምረጥ የሚችሉት ቴምፕሌት በ ማጣሪያ ወይንም በ ማምጫ ነው

 5. እርስዎ ካስጀመሩ በኋላ LibreOffice ማስደነቂያ እርስዎ የ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ እንደገና ማስኬድ ይችላሉ ተጨማሪ ገጽታዎች ጋር ለ መድረስ

የ ምክር ምልክት

የ እርስዎን ቴምፕሌቶች በ ምድብ ያደራጁ: አዲስ ቴምፕሌት ይፍጠሩ: ወይንም ቴምፕሌቶች ያውርዱ እና በ ቴምፕሌት አስተዳዳሪ ያደራጁ: ለ ተደጋጋሚ ሰነዶች ቴምፕሌት መጠቀም ጊዜ እንዳያባክኑ ይረዳዎታል


ይህን ይመልከቱ ቴምፕሌቶች እና ዘዴዎች ለ ተዛመደ መረጃ

ይህን ይመልከቱ የ ሰነድ ቴምፕሌት መፍጠሪያ ለ ተዛመደ መረጃ

ይህን ይመልከቱ ምዕራፍ 3 – ዘዴዎች እና ቴምፕሌቶች በ መጠቀም እንዴት እንደሚጀምሩ መምሪያ: ዝግጁ ነው በ ድሕረ ገጽ ሰነድ ውስጥ

ያመሳክሩ ወደ https://templates.libreoffice.org ቴምፕሌት ለ ማውረድ