የ Microsoft Office ሰነዶችን ስለ መቀየሪያ

LibreOffice ራሱ በራሱ መክፈት ይችላል የ Microsoft Office 97/2000/XP ሰነዶች: ነገር ግን አንዳንድ የ እቅድ ገጽታዎች እና አቀራረብ መለያዎች በ ውስብስብ የ Microsoft Office ሰነዶች የሚያዙት በ ተለየ ዘዴ ነው በ LibreOffice ወይንም የ ተደገፉ አይደሉም: ስለዚህ የ ተቀየሩ ፋይሎች በትንሽ ደረጃ በ እጅ አቀራረብ ማሰናዳት ያስፈልጋል: የሚያስፈልገው አቀራረብ እንደ መጠኑ እና ተመጣጣኝነት ይለያያል እንደ ውስብስብነቱ እና የ አካሉ አቀራረብ ለ ሰነዱ ምንጭ LibreOffice የ Visual Basic Scripts, ማስኬድ አይችልም: ነገር ግን እርስዎ እንዲመረምሩ መጫን ይችላል

የ ማስታወሻ ምልክት

በጣም የ ቅርብ ጊዜ እትም LibreOffice መጫን እና ማስቀመጥ ይቻላል የ Microsoft Office Open XML ሰነድ አቀራረብ ከ ተጨማሪዎች ጋር ከ docx, xlsx, እና pptx. ተመሳሳይ እትም ማስኬድ ይችላል አንዳንድ የ Excel Visual Basic scripts, እርስዎ ይህን ገጽታ ካስቻሉ በ - መጫኛ/ማስቀመጫ - VBA ባህሪዎች


የሚቀጥለው ዝርዝር የሚያቀርበው ባጠቃላይ መመልከቻ ነው ለ Microsoft Office ገጽታዎች በሚቀየር ጊዜ ችግር ለሚፈጥሩ: ይህ እርስዎን ይህን ሰነድ ከ መጠቀም ወይንም ከ መስራት አያግዶትም በ ተቀየረው ሰነድ ይዞታ ላይ

Microsoft Word

  1. በራሱ ቅርጾች

  2. የ መገምገሚያ ምልክቶች

  3. የ OLE እቃዎች

  4. አንዳንድ መቆጣጠሪያዎች እና የ Microsoft Office ፎርም ሜዳዎች

  5. ማውጫዎች

  6. የ ሰንጠረዥ: ክፈፎች: እና በርካታ-አምድ አቀራረብ

  7. Hyperlinks እና ምልክት ማድረጊያዎች

  8. Microsoft WordArt graphics

  9. የሚንቀሳቀስ ጽሁፍ/ባህሪዎች

Microsoft PowerPoint

  1. በራሱ ቅርጾች

  2. Tab: መስመር: እና የ አንቀጽ ክፍተት

  3. ዋናው የ መደብ ንድፎች

  4. በ ቡድን የተመደቡ እቃዎች

  5. አንዳንድ በርካታ መገናኛ ውጤቶች

Microsoft Excel

  1. በራሱ ቅርጾች

  2. የ OLE እቃዎች

  3. አንዳንድ መቆጣጠሪያዎች እና የ Microsoft Office ፎርም ሜዳዎች

  4. የ ፒቮት ሰንጠረዥ

  5. አዲስ የ ቻርትስ አይነቶች

  6. እንደ ሁኔታው አቀራረብ

  7. አንዳንድ ተግባሮች/መቀመሪያዎች (ከ ታች ይመልከቱ)

አንድ ምሳሌ በ ሰንጠረዥ እና በ Excel መካከል ያለው ልዩነት የ ቡልያን ዋጋዎች አያያዝ ነው: ያስገቡ እውነት ወደ ክፍሎች A1 እና A2.

የ ማስታወሻ ምልክት

ስለ የ Microsoft Office ሰነዶችን መቀየሪያ ዝርዝር መግለጫ ለማግኘት ይህን ይመልከቱ የ መሸጋገሪያ መምሪያ:


በ መግቢያ ቃል የሚጠበቁ የ Microsoft Office ሰነዶች መክፈቻ

LibreOffice መክፈት ይቻላል የሚቀጥለውን የ Microsoft Office ሰነድ አይነት በ መግቢያ ቃል የሚጠበቅ

የ Microsoft Office አቀራረብ

የ ተደገፉ የ መመስጠሪያ ዘዴዎች

Word 6.0, Word 95

ደካማ የ Xወይንም መመስጠሪያ

Word 97, Word 2000, Word XP, Word 2003

Office 97/2000 ተስማሚ መመስጠሪያ

Word XP, Word 2003

ደካማ የ Xወይንም መመስጠሪያ ከ አሮጌ የ ቃል እትሞች

Excel 2.1, Excel 3.0, Excel 4.0, Excel 5.0, Excel 95

ደካማ የ Xወይንም መመስጠሪያ

Excel 97, Excel 2000, Excel XP, Excel 2003

Office 97/2000 ተስማሚ መመስጠሪያ

Excel XP, Excel 2003

ደካማ የ Xወይንም መመስጠሪያ ከ አሮጌ የ Excel እትሞች


የ Microsoft Office ፋይሎች የ ተመሰጠሩ በ AES128 መክፈት ይቻላል: ሌላ መመስጠሪያ ዘዴ የ ተደገፈ አይደለም