የ ስህተት መግለጫ መሳሪያ
የ ስህተተ መግለጫ መሳሪያ ራሱ በራሱ ይጀምራል ፕሮግራም በሚጋጭ ጊዜ
የ ስህተት መግለጫ መሳሪያ ሁሉንም አስፈላጊ መረጃ ይሰበስባል: ፕሮግራም አበልጻጊዎቹ ኮዱን እንዲያሻሻሉ: ስለዚህ በሚቀቀጥለው እትም ይህ ስህተት ይወገዳል: እባክዎን የ መነጨውን ስህተት በ መላክ ሶፍትዌሩን እንድናሻሻል ይርዱን:
የ ስህተት መግለጫ መሳሪያ ማስጀመሪያ
በ በርካታ ፕሮግራም ውስጥ ግጭት የ ስህተት መግለጫ መሳሪያ ራሱ በራሱ ይጀምራል
መግለጫውን መጨረሻ
በ ዋናው የ ስህተት መግለጫ መሳሪያ ንግግር ውስጥ: እርስዎ ተጨማሪ መረጃ ማስገባት ይችላሉ አበልጻጊዎቹን ስለ ስህተቱ ሊረዳ የሚችል: ለምሳሌ: ስህተቱ የ ተፈጠረው በ ጠንካራ አክል ለውጥ እንደሆነ ወይንም ሶፍትዌር ምክንያት: ወይንም እርስዎ ምን ቁልፍ ሲጫኑ ስህተቱ እንደ ተፈጠረ: እባክዎን መረጃውን ያካትቱ
የ ስህተት መግለጫ በ መላክ ላይ
የ ስህተት መግላጫ የሚጠቀመው መሳሪያ የ HTTP PUT / SOAP አሰራር ነው ዳታ ለ መላክ: እርስዎ በ ምርጫ ያስገቡ መግለጫ ጽሁፍ እንዲረዳ ለ መለያ ይዞታ ለ ፕሮግራሙ ግጭት: እና ከዛ ይጫኑ የ መላኪያ ቁልፍ
ለ እርስዎ የ ስህተት መግለጫ ምንም መልስ አያገኙም: እርስዎ እርዳታ ከ ፈለጉ ይህን ይጎብኙ የ እርዳታ ክፍል ከ ኢንተርኔት ላይ
እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ጥያቄዎችን ለ መመለስ አበልጻጊዎቹ ያላቸውን ስለ እርስዎ ያሳወቁት ስህተቶች: በ ምልክት ማድረጊያው ሳጥን ውስጥ ምልክት ያድርጉ እርስዎን እንዲገናኙዎት በ ኢ-ሜይል: ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ: በ ነባር እዚህ ሳጥን ውስጥ ምልክት አይደረግም: ስለዚህ እርስዎ ኢ-ሜይል አያገኙም
ምን ዳታ ተላከ?
የ ስህተት መግለጫ በርካታ ፋይሎች ይይዛል: ዋናው ያዘው ፋይል ስለ ስህተት አይነቶች ነው: የ መስሪያ ስርአት ስም እና እትም: የ ማስታወሻ አጠቃቀም: እና እርስዎ ያስገቡትን መግለጫ ነው: እርስዎ መጫን ይችላሉ የ መግለጫ ማሳያ ቁልፍ ከ ዋናው ንግግር ውስጥ ከ ስህተት መግለጫ መሳሪያ ውስጥ መመልከት ይችላሉ በ ዋናው ፋይል ውስጥ የሚላከውን
በተጨማሪ የ ተገኘው የ ማስታወሻ ይዞታ እና መከመሪያ ምልክት የሚመነጨው እና የሚሰበሰበው በ አንዳንድ መደበኛ መሳሪያ ነው ("dbhhelp.dll" በ Windows ስርአት ውስጥ: "pstack" በ UNIXስርአት ውስጥ). ይህ መረጃ እንዲሁም ይላካል