የ ዲጂታል ፊርማ መፈጸሚያ

የምስክር ወረቀት ማግኛ

እርስዎ የ ምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላሉ ከ የ ምስክር ወረቀት ከሚሰጡ ባለስልጣናት: እርስዎ ከ መረጡ የ መንግስት ድርጅት ወይንም የ ግል ድርጅት ለ ግልጋሎቱ መክፈል የ ተለመደ ነው: ለምሳሌ: የ እርስዎን ማንነት ሲያረጋግጡ: በጣም ጥቂት ድርጅቶች የ ምስክር ወረቀት በ ነፃ ይሰጣሉ: እንደ Open Source Project ያሉCAcert ይህ መሰረት ያደረገው በጣም-የታወቀ እና አስተማማኝ የ ዌብ ታማኝነት በ መወደዱ ከፍተኛ ዝና አግኝቷል

የ ምስክር ወረቀቶች ማስተዳደሪያ

ሰነድ መፈረሚያ

  1. ይምረጡ ፋይል - ዲጂታል ፊርማ - ዲጂታል ፊርማ

  2. የ መልእክት ሳጥን እርስዎን ያሳስባል ሰነዱን እንዲያስቀምጡ ይጫኑ አዎ ፋይሉን ለማስቀመጥ

  3. ካስቀመጡ በኋላ ይህን ያያሉ የ ዲጂታል ፊርማዎች ንግግር ይጫኑ መጨመሪያ ለ መጨመር የ ሕዝብ ቁልፍ ወደ ሰነድ ውስጥ

  4. ምስክር ወረቀት ምርጫ ንግግር ውስጥ ይምረጡ የ እርስዎን የ ምስክር ወረቀት እና ይጫኑ እሺ

  5. ለ እርስዎ ይታያል እንደገና የ ዲጂታል ፊርማዎች ንግግር: እርስዎ ከ ፈለጉ ተጨማሪ የ ምስክር ወረቀት የሚጨምሩበት: ይጫኑ እሺ ለ መጨመር የ ሕዝብ ቁልፍ ወደ ተቀመጠው ፋይል ውስጥ

የ ተፈረመ ሰነድ ምልክት ያሳያል ምልክት በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ ምልክቱን በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ያለውን የ ምስክር ወረቀቱን ለ መመልከት

የ ፊርማ ማረጋገጫ ማሳያ ውጤት የሚታየው በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ነው: እና በ ዲጂታል ፊርማ ንግግር ውስጥ: በርካታ ሰነዶች እና የ ማክሮስ ፊርማዎች ይኖራሉ በ ODF ሰነድ ውስጥ: ከ ፊርማው ጋር ችግር ከ ተፈጠረ: የ ማረጋገጫ ውጤት ለ አንድ ፊርማ እንደ ለ ሁሉም ፊርማዎች ይወሰዳል: ይህም ማለት አስር ዋጋ ያላቸው ፊርማዎች ቢኖሩ እና አንድ ዋጋ የ ሌለው ፊርማ ካለ: ከዛ የ ሁኔታዎች መደርደሪያ እና የ ሁኔታዎች ሜዳ በ ንግግር ውስጥ ፊርማው ዋጋ እንደሌለው ምልክት ያሳያል

በ ሰነድ ውስጥ ያሉ ማክሮስ መፈረሚያ

ብዙ ጊዜ: ማክሮስ የ ሰነድ አካል ነው: እርስዎ ሰነድ ከ ፈረሙ: ማክሮስ በ ሰነዱ ውስጥ ራሱ በራሱ ይፈረማል: እርስዎ ማክሮስ ብቻ መፈረም ከ ፈለጉ: ነገር ግን ሰነዱን መፈረም ካልፈለጉ የሚቀጥለውን ያድርጉ:

  1. ይምረጡ መሳሪያዎች - ማክሮስ - የ ዲጂታል ፊርማ

  2. ለ ሰነዶቹ ፊርማውን መፈጸሚያ ከ ላይ እንደ ተገለጸው

እርስዎ በሚከፍቱ ጊዜ የ Basic IDE የ ተፈረመ ማክሮስ የያዘ: ምልክት ይታያል  ምልክት በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ ምልክቱን በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ያለውን የ ምስክር ወረቀቱን ለማየት