ስለ ዲጂታል ፊርማዎች

ይህ LibreOffice, እርስዎን ሰነዶች እና ማክሮስ ዲጂታሊ መፈረም ይስችሎታል

የምስክር ወረቀቶች

ሰነድ በ ዲጂታል ፊርማ ለ መፈረም: እርስዎ የ ግል ቁልፍ ያስፈልጎታል: የ ምስክር ወረቀት የ ግል ቁልፍ የሚቀመጠው በ እርስዎ ኮምፒዩተር እንደ መቀላቀያ የ ግል ቁልፍ ነው: እንደ ሚስጥር መቀመጥ አለበት: እና እንደ ሕዝብ ቁልፍ: እርስዎ እንደ ፊርማ መጨመር የሚችሉት ወደ እርስዎ ሰነዶች ውስጥ

ማስቀመጫ እና ሰነዱን መፈረሚያ

እርስዎ የ ዲጂታል ፊርም በ ሰነድ ውስጥ በሚፈርሙ ጊዜ: በ እርስዎ ኮምፒዩተር ውስጥ የ ጠቅላላ ድምር ሁኔታ ይካሄዳል በ እርስዎ ሰነድ ይዞታዎች እና የ እርስዎ የ ግል ቁልፍ መካከል: የ ጠቅላላ ድምር እና የ እርስዎ የ ሕዝብ ቁልፍ የሚቀመጠው በ አንድ ላይ በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ነው

የ ተፈረመ ሰነድ መክፈቻ

ሌላ ሰው በኋላ ሰነዱን በሚከፍትበት ጊዜ በማንኛውም ኮምፒዩተር በ ቅርብ ጊዜ LibreOffice: ፕሮግራሙ ጠቅላላ ድምሩን ይመረምራል እና ያወዳድራል ከ ተቀመጠው ጠቅላላ ድምር ጋር: ሁለቱም አንድ አይነት ከሆኑ: ፕሮግራሙ ዋናውን ያልተቀየረ ሰነድ እንደሚያዩ ያረጋግጣል: በ ተጨማሪ: ፕሮግራሙ የ ሕዝብ ቁልፍ መረጃ የ ምስክር ወረቀት ያሳያል

እርስዎ ማወዳደር ይችላሉ የ ሕዝብ ቁልፍ ከ ሕዝብ ቁልፍ አታሚዎች ጋር በ ድህረ ገጽ ውስጥ በ የ ምስክር ወረቀት ባለስልጣኖች ጋር

በ ሰነድ ውስጥ ማንም አንድ ነገር በሚቀይር ጊዜ: ይህ ለውጥ የ ዲጂታል ፊርማውን ይሰብራል: ከ ለውጡ በኋላ: ከዚያ በኋላ እርስዎ ዋናውን ሰነድ መመልከትዎን የሚያሳይ ምንም ምልክት የለም

የ ፊርማ ማረጋገጫ ማሳያ ውጤት የሚታየው በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ነው: እና በ ዲጂታል ፊርማ ንግግር ውስጥ: በርካታ ሰነዶች እና የ ማክሮስ ፊርማዎች ይኖራሉ በ ODF ሰነድ ውስጥ: ከ ፊርማው ጋር ችግር ከ ተፈጠረ: የ ማረጋገጫ ውጤት ለ አንድ ፊርማ እንደ ለ ሁሉም ፊርማዎች ይወሰዳል: ይህም ማለት አስር ዋጋ ያላቸው ፊርማዎች ቢኖሩ እና አንድ ዋጋ የ ሌለው ፊርማ ካለ: ከዛ የ ሁኔታዎች መደርደሪያ እና የ ሁኔታዎች ሜዳ በ ንግግር ውስጥ ፊርማው ዋጋ እንደሌለው ምልክት ያሳያል

እርስዎ ከ እነዚህ አንዱን ምልክት እና መልእክቶች ሊያዩ ይችላሉ የ ተፈረመ ሰነድ ሲከፍቱ

ምልክት በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ

የ ፊርማ ሁኔታዎች

ምልክት

ፊርማው ዋጋ አለው

ምልክት

ፊርማው ትክክል ነው: ነገር ግን የምስክር ወረቀቱን ማረጋገጥ አልተቻለም

ፊርማው እና የምስክር ወረቀቱ ጥሩ ናቸው: ነገር ግን የ ሰነድ ሁሉም አክል አልተፈረመም: (በ አሮጌው እትም ሶፍትዌር ለ ተፈረሙ ሰነዶች: ይህን ይመልከቱ)

ምልክት

ፊርማው ዋጋ የለውም


ፊርማዎች እና የ ሶፍትዌር እትሞች

ይዞታዎችን መፈረም ተቀይሯል በ OpenOffice.org 3.2 እና በ StarOffice 9.2. አሁን ሁሉም የ ፋይል ይዞታዎች ከ ፊርማው በስተቀር (META-INF/documentsignatures.xml) ይፈረማል

እርስዎ ሰነድ በሚፈርሙ ጊዜ በ OpenOffice.org 3.2 ወይንም በ StarOffice 9.2 ወይንም በ ዘመናዊ እትም: እና እርስዎ ሰነዱን በ አሮጌ እትም ሶፍትዌር ለ መክፈት ሲሞክሩ: ፊርማው እንደ "ዋጋ የለውም" የሚል ማስጠንቀቂያ ይታይዎታል: በ አሮጌ እትም የ ተፈጠሩ ፊርማዎች ምልክት ይደረግባቸዋል በ "አንዳንድ የ ሰነዱ አካል ተፈርሟል" የሚል ማስጠንቀቂያ ይታይዎታል በ አዲስ ሶፍትዌር ሲከፍቱት

እርስዎ በሚፈርሙ ጊዜ የ OOXML ሰነድ: ፊርማው ሁል ጊዜ ምልክት ይደረግበታል "በ ከፊል ሰነዱ ተፈርሟል": Metadata of OOXML ፋይሎች አልተፈረሙም: ተስማሚ እንዲሆኑ ከ Microsoft Office ጋር

እርስዎ የ PDF ሰነድ ሲፈርሙ: ይህን ምልክት ማድረጊያ አይጠቀሙም: የ ሰነዱን ትንሽ አካል መፈረም በ ቀላሉ ምንም ዋጋ የ ሌለው ፊርማ ነው

የ ሌላ ሰነድ አቀራረብ መፈረም ለ ጊዜው የ ተደገፈ አይደለም

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ የ ODF ሰነድ: ለ እርስዎ ይታይዎት ይሆናል ምልክት በ ሁኔታ መደርደሪያ እና በ ሁኔታ ሜዳ መደርደሪያ ንግግር ውስጥ ይታያል ሰነዱ የ ተፈረመው በ ከፊል ነው የሚል ማስጠንቀቂያ: ይህ ሁኔታ የሚታየው ፊርማው እና የምስክር ወረቀቱ ዋጋ ያለው ሲሆን ነው: ነገር ግን የ ተፈጠረው በ OpenOffice.org ከ 3.2 በፊት ወይንም በ StarOffice ከ 9.2. በፊት እትም OpenOffice.org ከ 3.0 በፊት ወይንም StarOffice ከ 9.0, በፊት ከሆነ የ ሰነድ ፊርማ የሚፈጸመው ለ ዋናው ይዞታ: ስእሎች: እና የ ተጣበቁ እቃዎች ብቻ እና አንዳንድ ሁኔታዎች ነው: ማክሮስ: አይፈረምም በ OpenOffice.org 3.0 እና በ StarOffice 9.0 የ ሰነድ ፊርማ ለ በርካታ ይዞታዎች ይፈጸማል: ማክሮስ ያካትታል: ነገር ግን: የ mimetype እና የ ይዞታ ለ META-INF ፎልደር አይፈረምም: እና በ OpenOffice.org 3.2, StarOffice 9.2, እና ሁሉም እትሞች ለ LibreOffice ሁሉም ይዞታዎች: ከ ፊርማ ፋይል በስተቀር (META-INF/documentsignatures.xml), ይፈረማሉ


የ ደህንነት ማስጠንቀቂያዎች

እርስዎ በሚቀበሉ ጊዜ የ ተፈረመ ሰነድ: እና የ ሶፍትዌር መግለጫ ፊርማው ዋጋ እንዳለው: ይህ ማለት እርስዎ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ ማለት ነው እርስዎ የ ተቀበሉት ሰነድ ላኪው የላከው መሆኑን: ሰነዶችን መፈረም በ ሶፍትዌር የምስክር ወረቀት በ ትክክል የ ደህንነት አስተማማኝ ዘዴ አይደለም: በርካታ ሌሎች መንገዶች አሉ አስተማማኝ የ ደህንነት ዘዴ ለ መፈጸም

ለምሳሌ: ያስቡ አንድ ሰው ራሱን በ መደበቅ እርስዎን ማታለል የሚፈልግ ከ እርስዎ ባንክ በማስመሰል ደብዳቤ ሊልክልዎት ይችላል: የምስክር ወረቀት በ ቀላሉ ማግኘት ይችላል የ ሀሰት ስም በ መጠቀም: እና ከዛ የ ተፈረመ ኢ-ሜይል ለ እርስዎ ሊልክ ይችላል ራሱን የ ባንክ ሰራተኛ አስመስሎ: እርስዎ ይህን ኢ-ሜይል ያገኛሉ: እና ይህ ኢ-ሜይል ወይንም ሰነድ በ ውስጡ "ዋጋ ያለው የ ተፈረመ" ምልክት ይኖረዋል

ምልክቱን አይመኑ የምስክር ወረቀቱን ይመርምሩ እና ያረጋግጡ

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

የ ፊርማ ማረጋገጫ ማንኛውንም ሕጋዊ ማስተማመኛ አይሰጥም


በ Windows operating systems, የ Windows ገጽታዎች ይጠቀማል ፊርማ ለ ማረጋገጥ: በ Solaris እና Linux systems, ፋይሎች የ ቀረቡ በ Thunderbird, Mozilla ወይንም Firefox ይጠቀማል: እርስዎ እርግጠኛ ይሁኑ እርስዎ እየተጠቀሙ ያሉት ፋይሎች በ እርስዎ ስርአት ውስጥ ዋባው ፋይሎች መሆናቸውን እና በ ዋናው አበልጻጊዎች የ ቀረቡ መሆናቸውን ያረጋግጡ: ለ ተንኮለኞች በርካታ መንገድ አለ ዋናውን ፋይል እነሱ ባቀረቡት በ ሌሎች ፋይሎች የሚቀይሩበት

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

የ ፊርማ ማረጋገጫ መልእክቶች ለ እርስዎ የሚታየው በ LibreOffice ውስጥ መልእክቶች ናቸው የ ማረጋገጫ ፋይል የሚመልሰው: ይህ LibreOffice ሶፍትዌር ምንም ማረጋገጫ የለውም መልእክቶች የ እውነት ሁኔታ እንደሚያመለክቱ በ ማንኛውም የምስክር ወረቀት ውስጥ: ይህ LibreOffice ሶፍትዌር የሚያሳየው መልእክቶች ሌሎች ፋይሎች በዚህ መቆጣጠሪያ ስር እንዳልሆኑ LibreOffice ብቻ መግለጫ ነው: ምንም ሕጋዊ ሀላፊነት የለበትም LibreOffice የሚታየው መልእክት ትክክለኛ ሁኔታ ስለ ዲጂታል ፊርማ እንደሚያንፀባርቅ