ተጨማሪ መቆጣጠሪያ
ተጨማሪ የ እቃ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ መክፈቻ እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ ተጨማሪ መቆጣጠሪያ ምልክት በ ፎርም መቆጣጠሪያ እቃ መደርደሪያ ውስጥ
ማሽከርከሪያ ቁልፍ
ማሽከርከሪያ ቁልፍ መፍጠሪያ
እርስዎ ከ ጨመሩ የ ማሽከርከሪያ ቁልፍ ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ: እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የዳታ tab ገጽ ለ መፍጠር የ ሁለት-በኩል አገናኝ በ ማሽከርከሪያ ቁልፍ እና በ ክፍል ውስጥ: ውጤቱ የ ክፍሉን ሁኔታ ሲቀይሩ: የ ማሽከርከሪያ ቁልፍ ይሻሻላል: በ ግልባጭ እርስዎ ዋጋ ከ ቀየሩ በ ማሽከርከሪያ ቁልፍ ውስጥ የ ክፍሉ ይዞታ ይሻሻላል
መሸብለያ መደርደሪያ
መሸብለያ መደርደሪያ መፍጠሪያ
መወሰን ይችላሉ የሚቀጥሉትን ባህሪዎች ለ መሸብለያ መደርደሪያ:
የ ተጠቃሚ ገጽታ ስም |
ትርጉም |
የ መሸብለያ አነስተኝ ዋጋ |
ለ መሸብለያ መደርደሪያ አነስተኛ እርዝመት ወይንም አነስተኛ ስፋት መወሰኛ |
የ መሸብለያ ከፍተኛ ዋጋ |
ለ መሸብለያ መደርደሪያ ከፍተኛ እርዝመት ወይንም ከፍተኛ ስፋት መወሰኛ |
ነባር መሸብለያ ዋጋ |
ለ መሸብለያ መደርደሪያ ነባር ዋጋ መወሰኛ ፎርሙ እንደ ነበር በሚመለስበት ጊዜ |
አቅጣጫ |
በ አግድም ወይንም በ ቁመት የ መሸብለያ መደርደሪያ አቅጣጫ መወሰኛ |
ትንሽ ለውጥ |
ለ እርስዎ አነስተኛ መጠን እንደሚሸበልሉ መወሰኛ: መሸብለያ መደርደሪያውን: ለምሳሌ: ቀስቱን በ መጫን |
ትልቅ ለውጥ |
ለ እርስዎ ከፍተኛ መጠን እንደሚሸበልሉ መወሰኛ: መሸብለያ መደርደሪያውን: ለምሳሌ: እርስዎ በሚሸበልሉ ጊዜ በ አውራ ጥፍር እና በ መሸብለያ መደርደሪያ ቀስቱን ሲጫኑ |
ማዘግያ |
ማዘግያ መወሰኛ በ ሚሊ ሰከንዶች በ መሸብለያ ማስጀመሪያ ሁኔታ መካከል: ለምሳሌ ማዘግያ የሚፈጠረው እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ የ ቀስት ቁልፍ በ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ እና ተጭነው ይያዙ የ አይጥ ቁልፍ |
የ ምልክት ቀለም |
የ ቀስት ቀለም በ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ መወሰኛ |
የሚታይ መጠን |
የ መሸብለያ መደርደሪያ መጠን መወሰኛ በ አውራ ጥፍር ልክ በ "ዋጋ ክፍሎች": ውስጥ: ለምሳሌ ዋጋ የ ("መሸብለያ ዋጋ ከፍተኛው" መቀነሻ "መሸብለያ ዋጋ ዝቅተኛው") / 2 ውጤቱ በ መሸብለያ መደርደሪያ አውራ ጥፍር ልክ የ መሸብለያ መደርደሪያ ግማሽ መጠን ይሆናል የ መሸብለያ ስፋት ከ መሸብለያ እርዝመት ጋር እኩል ለማድረግ: የሚታየውን መጠን ዜሮ ያድርጉ በ ማሰናጃው ውስጥ |
በ ሰንጠረዥ ውስጥ እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የ ዳታ tab ገጽ ለ መፍጠር የ ሁለት-በኩል አገናኝ መካከል መሸብለያ መደርደሪያ በ ክፍል ውስጥ
የ ምስል ቁልፍ
እንደ ምስል የሚታይ ቁልፍ መፍጠሪያ ንድፍ ከ መወከል ባሻገር: የ ምስል ቁልፍ ተመሳሳይ ባህሪ ነው ያለው እንደ "መደበኛ" ቁልፍ
ምስል መቆጣጠሪያ
የ ምስል መቆጣጠሪያ መፍጠሪያ: እርስዎ መጠቀም የሚችሉት ምስሎችን ከ ዳታቤዝ ውስጥ ለ መጨመር ብቻ ነው: በ ፎርም ሰነድ ውስጥ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ አንዱ መቆጣጠሪያ ይከፈታል የ ንድፍ ማስገቢያ ንግግር ምስል ለማስገባት: እንዲሁም የ አገባብ ዝርዝር አለ (በ ንድፍ ዘዴ አይደለም) በ ትእዛዝ ምስል ማስገቢያ እና ማጥፊያ
ምስሎች ከ ዳታቤዝ ውስጥ በ ፎርም ላይ ማሳየት ይቻላል: እና አዲስ ምስሎች ማስገባት ይቻላል የ ምስል መቆጣጠሪያ ለመጻፍ-የሚጠበቅ ካልሆነ በስተቀር: መቆጣጠሪያው ወደ ዳታቤዝ ሜዳ ምስል አይነት መምራት አለበት: ስለዚህ ያስገቡ የ ዳታ ሜዳ ወደ ባህሪዎች መስኮት ከ ዳታ tab ገጽ ውስጥ
የ ቀን ሜዳ
የ ቀን ሜዳ መፍጠሪያ ፎርሙ ከ ዳታቤዝ ጋር ከ ተገናኘ የ ቀን ዋጋዎች ከ ዳታቤዝ ይቀበላል
እርስዎ ከ መደቡ "ወደ ታች የሚዘረገፍ" ባህሪዎች ለ ቀን ሜዳ: ተጠቃሚው የ ቀን መቁጠሪያ መክፈት ይችላል ቀን ለ መምረጥ በ ቀን ሜዳ ውስጥ: ይህን ለ ቀን ሜዳ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ሜዳ ውስጥ መፈጸም ይቻላል
የ ቀን ሜዳ በቀላሉ ማረም ይቻላል በ ተጠቃሚው ቀስት ወደ ላይ እና ቀስት ወደ ታች ቁልፍ በ መጠቀም: መጠቆሚያው እንዳለበት ሁኔታ የ ቀን: ወር: ወይንም አመት መጨመር ወይንም መቀነስ ይቻላል የ ቀስት ቁልፍ በ መጠቀም
የ ሰአት ሜዳ
የ ቀን ሜዳ መፍጠሪያ ፎርሙ ከ ዳታቤዝ ጋር ከ ተገናኘ የ ቀን ዋጋዎች ከ ዳታቤዝ ይቀበላል
የ ሰአት ሜዳ በቀላሉ ማረም ይቻላል በ ተጠቃሚው ቀስት ወደ ላይ እና ቀስት ወደ ታች ቁልፍ በ መጠቀም: መጠቆሚያው እንዳለበት ሁኔታ የ ሰአት: ደቂቃ: ወይንም ሰከንዶች መጨመር ወይንም መቀነስ ይቻላል የ ቀስት ቁልፍ በ መጠቀም
የ ፋይል ምርጫዎች
የ ፋይል ምርጫዎች የሚያስችል ቁልፍ መፍጠሪያ
የ ቁጥር ሜዳ
የ ቁጥር ሜዳ መፍጠሪያ ፎርሙ ከ ዳታቤዝ ጋር ከ ተገናኘ የ ቁጥር ዋጋዎች ከ ዳታቤዝ ይቀበላል
የ ገንዘብ ሜዳ
የ ገንዘብ ሜዳ መፍጠሪያ ፎርሙ ከ ዳታቤዝ ጋር ከ ተገናኘ: የ ገንዘብ ሜዳ ይዞታዎች ለ ፎርሙ ከ ዳታቤዝ ማግኘት ይቻላል
የ ንድፍ ሜዳ
የ ድግግሞሽ ሜዳ መፍጠሪያ. የ ድግግሞሽ ሜዳ ይዟል የ edit mask እና የ literal mask. የ edit mask የሚወስነው የትኛው ዳታ እንደሚገባ ነው: የ literal mask የሚወስነው የ ድግግሞሽ ሜዳ ይዞታዎችን ነው: ፎርሙን በሚጭኑ ጊዜ
እባክዎን ያስታውሱ የ ድግግሞሽ ሜዳዎች መላክ አይቻልም ወደ HTML አቀራረብ
የ ቡድን ሳጥን
ክፈፍ መፍጠሪያ በርካታ መቆጣጠሪያዎች በ ቡድን ለማየት የ ቡድን ሳጥኖች እርስዎን የሚያስችለው የ ምርጫ ቁልፎችን በ ቡድን ማድረግ ነው በ ክፈፍ ውስጥ
በ ሰነድ ውስጥ የ ቡድን ክፈፍ ካስገቡ የ ቡድን አካል አዋቂ ይጀምራል: ይህም በ ቀላሉ የ ምርጫ ቡድን መፍጠር ያስችሎታል
ማስታወሻ: እርስዎ የ ቡድን ሳጥን በሚጎትቱ ጊዜ ቀደም ብሎ መቆጣጠሪያ የነበረው እና እርስዎ መቆጣጠሪያ መምረጥ ከፈለጉ: እርስዎ በ መጀመሪያ መክፈት አለብዎት የ ቡድኑን ሳጥን አገባብ ዝርዝር እና ይምረጡ ማዘጋጃ - ወደ ኋላ መላኪያ : እና ከዛ ይምረጡ መቆጣጠሪያ ተጭነው ይዘው ትእዛዝ Ctrl
የ ቡድን ሳጥኖች የሚጠቅሙት ለ መመልከቻ ውጤት ባቻ ነው: ተግባራዊ የ ሜዳ ምርጫ መስራት ይቻላል በ ስም መግለጫ: በ ስም ባህሪዎ ስር: በ ሁሉም የ ሜዳዎች ምርጫ: ተመሳሳይ ስም ያስገቡ በ አንድ ቡድን ውስጥ ለማድረግ
ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ
የ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ መፍጠሪያ የ ዳታቤዝ ሰንጠረዥ ለማሳየት አዲስ የ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ከ ፈጠሩ የ ሰንጠረዥ አካል አዋቂ ይታያል
መቃኛ መደርደሪያ
የ መቃኛ መደርደሪያ መፍጠሪያ
የ መቃኛ መደርደሪያ እርስዎን የሚያስችለው በ ዳታቤዝ መዝገቦች ውስጥ መንቀሳቀስ ነው: ወይንም የ ዳታቤዝ ፎርም ውስጥ: በዚህ መቃኛ መደርደሪያ ላይ ያለው መቆጣጠሪያ የሚሰራው እንደ ነባሩ ነው እንደ መቃኛ መደርደሪያ በ LibreOffice