ባህሪዎች መፍጠሪያ

በዚህ ንግግር ውስጥ እርስዎ መግለጽ ይችላሉ: ከ ሌሎች ጋር: የ ዳታ ምንጮች እና ሁኔታዎች ለ ፎርሙ ባጠቃላይ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

መክፈቻ የ አገባብ ዝርዝር የ ተመረጠውን የ ፎርም አካል - ይምረጡ ፎርም

ምልክት

ፎርም


እርስዎ ዳታ ካስገቡ በ ባህሪዎች ንግግር ውስጥ: ያስታውሱ በርካታ መስመር ማስገባት እንደሚቻል ለ አንዳንድ ወደ ታች-ለሚዘረገፍ ማጣመሪያ ሳጥኖች: ይህ ሁሉንም ሜዳዎች ይመለከታል በ SQL አረፍተ ነገር በሚገባበት: እንዲሁም ባህሪዎች ለ ጽሁፍ ሳጥኖች ወይንም ለ ምልክት ሜዳዎች: እርስዎ መክፈት ይችላሉ እነዚህን ሜዳዎች እና ጽሁፍ ማስገባት በ ተፈተው ዝርዝር ውስጥ: የሚቀጥለው አቋራጭ ቁልፍ ዋጋ ያለው ነው:

ቁልፎች

ተጽዕኖው

+ቀስት ወደ ታች

መክፈቻ የ መቀላቀያ ሳጥን

+ቀስት ወደ ላይ

መዝጊያ የ መቀላቀያ ሳጥን

Shift+ማስገቢያ

አዲስ መስመር ማስገቢያ

ቀስት ወደ ላይ

መጠቆሚያውን ቀደም ወዳለው መስመር መውሰጃ

ቀስት ወደ ታች

መጠቆሚያውን ወደሚቀጥለው መስመር መውሰጃ

ማስገቢያ

በ ሜዳ ውስጥ ማስገቢያውን ይፈጽማል: እና መጠቆሚያውን ወደሚቀጥለው ሜዳ ይሄዳል


ከ ዝርዝር ሳጥኖች ወይንም መቀላቀያ ሳጥኖች ውስጥ: እርስዎ መክፈት ወይንም መዝጋት ይችላሉ ከ ዝርዝር ውስጥ በ አይጥ መጠቆሚያ: ይጫኑ በ ቀስቱ ላይ በ ሜዳው ቀኝ መጨረሻ በኩል: ነገር ግን እዚህ ማስገባት የሚቻለው በ አንዱ በ ተከፈተው ዝርዝር ወይንም ከ ላይ በ ጽሁፍ ሜዳ ውስጥ ነው: የ ተለየ ለ ባህሪዎች ዝርዝር ውክልና ለሚጠብቁ ይደረጋል: ለምሳሌ: ለ ባህሪ ዝርዝር ማስገቢያ ማሰናዳት ይቻላል በ መቆጣጠሪያ ሜዳ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ እና መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ: እዚህ እርስዎ ማስገቢያዎችን ማረም ይችላሉ ሜዳው በ ተከፈተበት

ባጠቃላይ

ዳታ

ዳታ tab ገጽ የሚገልጸው የ ፎርም ባህሪዎች ነው: ወደ ዳታቤዝ የሚያመሳክሩ ከ ፎርም ጋር የ ተገናኙ

ሁኔታዎች

ሁኔታዎች tab ገጽ: እርስዎን የሚያስችለው መመደብ ነው ማክሮስ ለ አንዳንድ ሁኔታዎች በ ፎርም ውስጥ ለሚፈጠር