ባጠቃላይ

ይህ ባጠቃላይ tab እርስዎን መግለጽ ያስችላል ባጠቃላይ ባህሪዎች ለ ፎርም መቆጣጠሪያ: እነዚህ መቆጣጠሪያዎች ይለያያሉ: እንደ መቆጣጠሪያው አይነት: ሁሉም የሚቀጥሉት ባህሪዎች ዝግጁ አይደሉም ለ ሁሉም መቆጣጠሪያዎች

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

መክፈቻ የ አገባብ ዝርዝር የ ተመረጠውን አካል - ይምረጡ መቆጣጠሪያ - ባጠቃላይ tab

መክፈቻ የ ፎርም መቆጣጠሪያ እቃ መደርደሪያ ወይንም የ ንድፍ እቃ መደርደሪያ: ይጫኑ መቆጣጠሪያ ምልክት - ባጠቃላይ tab


የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ ከላኩ የ አሁኑን ፎርም ሰነድ ወደ HTML አቀራረብ: ነባር መቆጣጠሪያ አጋዎች ይላካሉ: የ አሁኑ መቆጣጠሪያ ዋጋዎች አይደለም: ነባር ዋጋዎች ይወሰናሉ - እንደ መቆጣጠሪያው አይነት - በ ባህሪዎች' ነባር ዋጋ (ለምሳሌ: በ ጽሁፍ ሜዳዎች ውስጥ) ነባር ሁኔታዎች (ሳጥን ውስጥ ምልክት ማድረጊያ: እና የ ምርጫ ሜዳዎች) እና ነባር ምርጫ (ለ ዝርዝር ሳጥኖች).


URL

ያስገቡ የ URL አድራሻ ለ ተከፈተ ሰነድ ወይንም በ ድህረ ገጽ ቁልፍ አይነት ውስጥ በ URL ሳጥን ውስጥ: አድራሻው ይከፈታል እርስዎ ቁልፍ ሲጫኑ

እርስዎ የ አይጥ መጠቆሚያውን በ ቁልፉ ላይ ካንቀሳቀሱ በ ተጠቃሚ ዘዴ ውስጥ: የ URL ይታያል እንደ የ ተስፋፋ ጠቃሚ ምክር: ሌላ ምንም የ እርዳታ ጽሁፍ ሳይገባ

ለንባብ-ብቻ

ንባብ-ብቻ ባህሪ መመደብ ይቻላል ለ ሁሉም መቆጣጠሪያዎች ተጠቃሚው ጽሁፍ የሚያስገባበት: እርስዎ ከ መደቡ ለ ንባብ-ብቻ ባህሪዎች የ ምስል ሜዳ የ ንድፍ ሜዳ የሚጠቀም ከ ዳታቤዝ ውስጥ: ተጠቃሚው አዲስ ንድፎች ማስገባት አይችልም ወደ ዳታቤዝ ውስጥ

ሊታተም የሚችል

የ መቆጣጠሪያ ሜዳ በሚታተመው በ እርስዎ ሰነድ ላይ ይካተት እንደሆን መወሰኛ

መመዝገቢያ ምልክት ማድረጊያ

የ መጀመሪያው አምድ ከ ረድፍ ምልክቶች ጋር ይታይ እንደሆን መወሰኛ: የ አሁኑ መግለጫ በ ቀስት ምልክት የ ተደረገበት

መስመር መቁጠሪያ

ውስጥ: ለ መቀላቀያ ሳጥኖች ከ ወደ ታች የሚዘረገፍ ባህሪዎች ጋር: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ምን ያህል መስመሮች እንደሚታዩ በ ወደ ታች የሚዘረገፍ ዝርዝር ውስጥ: በ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ወደ ታች የሚዘረገፍ ምርጫ የሌላቸው: የ መስመሮች ማሳያ በ መጠን መቆጣጠሪያ ሜዳ እና የ ፊደል መጠን ይወሰናል

መሸብለያ መደርደሪያ

እርስዎ የወሰኑትን አይነት የ መሸብለያ መደርደሪያ ወደ ጽሁፍ ሳጥን ውስጥ መጨመሪያ

መቀያየሪያ

የ መግፊያ ቁልፍ እንዴት እንደሚሆን በ መቀያየሪያ ቁልፍ ውስጥ: እርስዎ ከ ቀየሩ ወደ "አዎ": እርስዎ መቀየር ይችላሉ በ "ተመረጠው" እና "ባልተመረጠው" መቆጣጠሪያ መካከል እርስዎ ቁልፍ በሚጫኑ ጊዜ ወይንም ክፍተት ማስገቢያ መቆጣጠሪያው ላይ ትኩረት ሲኖር: ቁልፍ በ "ተመርጧል" ሁኔታ ያታያል "ተጭነዋል ውስጥ"

መቃኛ

በ ተመረጠው መቃኛ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ ላይ የ ተግባሮች ደንብ ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ የሚከተሉት የ መቃኛ እቃዎች ናቸው: የ መጀመሪያ መዝገብ: ያለፈው መዝገብ: የሚቀጥለው መዝገብ: የ መጨረሻው መዝገብ:

መቃኛ መደርደሪያ

የ መቃኛ መደርደሪያ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ከታች ድንበር በኩል ይታይ እንደሆን መወሰኛ

መነሻ ምልክቶች

የ ገንዘብ ምልክት የሚታየው ከ ቁጥሩ በፊት ወይንም በኋላ መሆኑን መወሰኛ የ ገንዘብ ሜዳ ሲጠቀሙ ነባር ማሰናጃው የ ገንዘብ ምልክቶች በ ቅድሚያ የ ተወሰኑ አይደሉም

መድገሚያ

የ ተግባር መቆጣጠሪያ መወሰኛ እንደ ማዞሪያ ቁልፍ መድገሚያ እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ መቆጣጠሪያ እና የ አይጥ ቁልፍ ተጭነው ይያዙ

መጠን

እንደገና መመጠኛ ምስል በ መቆጣጠሪያው ልክ

ማሰለፊያ/ ንድፎች ማሰለፊያ

የ ማሰለፊያ ምርጫዎች በ ግራ-ማሰለፊያዎች: በ ቀኝ-ማሰለፊያዎች እና መሀከል ማሰለፊያ ናቸው: እነዚህ ምርጫዎች ዝግጁ ናቸው ለሚቀጥሉት አካላቶች:

  1. የ ምልክት ሜዳዎች አርእስት

  2. የጽሁፍ ሜዳዎች ይዞታ

  3. የ ሰንጠረዥ ሜዳዎች ይዞታ በ አምዶች ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ውስጥ

  4. ንድፎች ወይንም ጽሁፍ በ ቁልፎች ውስጥ የ ተጠቀሙት

    የ ማስታወሻ ምልክት

    ማሰለፊያ ምርጫ ለ ቁልፎች የሚባለው ንድፎች ማሰለፊያ ነው


ማስረጊያ ማስቆሚያ

ማስረጊያ ማስቆሚያ ባህሪ የሚወስነው የ መቆጣጠሪያ ሜዳ መምረጥ ይቻላል በ tab ቁልፍ የሚቀጥሉት ምርጫዎች ዝግጁ ናቸው:

አይ

የ ማስረጊያ ቁልፍ በሚጠቀሙ ጊዜ: ትኩረቱን ከ መቆጣጠሪያው ውስጥ ይዘላል

አዎ

መቆጣጠሪያ መምረጥ ይቻላል በ Tab ቁልፍ


ማስቆሚያ

የ መቆጣጠሪያ ማስቆሚያ መግለጫ

ማሽከርከሪያ ቁልፍ

የ ቁጥር ሜዳዎች: የ ገንዘብ ሜዳዎች: የ ቀን እና ሰአት ሜዳዎች በ ፎርም ውስጥ እንደ ማሽከርከሪያ ቁልፍ መጠቀም ይችላሉ

ማዘግያ

ማዘግያ መወሰኛ በ ሚሊ ሰከንዶች በሚደጋገሙ ሁኔታ መካከል የሚደጋገሙ ሁኔታ የሚፈጠረው እርስዎ ሲጫኑ ነው የ ቀስት ቁልፍ ወይንም የ መሸብለያ መደረደሪያ መደብ ቦታ ላይ ሲጫኑ ነው: ወይንም አንዱን የ መዝገብ መቃኛ ቁልፍ በ መቃኛ መደርደሪያ ላይ ሲጫኑ ነው: እና እርስዎ የ አይጥ ቁልፍ ተጭነው ይያዙ ለ ተወሰነ ጊዜ: እርስዎ ከ ፈለጉ ዋጋ ያለው ጊዜ መለኪያ ማካተት ይችላሉ ለምሳሌ 2 ሰ ወይንም 500 ማሰ

ማጣሪያ / መለያ

በ ተመረጠው መቃኛ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ ላይ ማጣሪያዎች ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ የሚከተሉት የ ማጣሪያ እና መለያ እቃዎች ናቸው: እየጨመረ በሚሄድ መለያ: እየቀነሰ በሚሄድ መለያ: ራሱ በራሱ ማጣሪያ መለያ: ነባር ማጣሪያ: ማጣሪያ መፈጸሚያ: እንደ ነበር መመለሻ ማጣሪያ/መለያ

ምልክት

የ ምልክት ባህሪ ማሰናጃ ለ ምልክት መቆጣጠሪያ ሜዳ ላይ የሚታየው በ ፎርም ላይ: ይህ ባህሪ የሚወስነው የሚታይ ምልክት ወይንም የ አምድ ራስጌ ለ ዳታ ሜዳ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ፎርም ውስጥ ነው

እርስዎ አዲስ መቆጣጠሪያ በሚፈጥሩ ጊዜ: መግለጫው በ ቅድሚያ የ ተገለጸ በ ስም ባህሪ ይጠቀማል እንደ ነባር መቆጣጠሪያውን ምልክት ለ መስጠት: ምልክቱ የ መቆጣጠሪያ ስም እና ኢንቲጀር ቁጥር መስጫ ለ መቆጣጠሪያ ይይዛል (ለምሳሌ: ትእዛዝ ቁልፍ1) በ አርእስት ባህሪ ውስጥ: እርስዎ ሌላ መግለጫ መመደብ ይችላሉለ መቆጣጠሪያ ስለዚህ ምልክቱ ያንፀባርቃል የ ተግባር መቆጣጠሪያ: ማስገቢያውን ይቀይሩ ለ መመደብ መግለጫ የ ምልክት መቆጣጠሪያ ለ ተጠቃሚ የሚታይ ለ መፍጠር

ለ መፍጠር በርካታ-መስመር አርእስት ያለው: መክፈቻ ለ መቀላቀያ ሳጥን የ ቀስት ቁልፍ በ መጠቀም: እርስዎ ማስገባት ይችላሉ የ መስመር መጨረሽ በ መጫን Shift++Enter.

የ ማስታወሻ ምልክት

አርእስት ባህሪ የሚጠቅመው ለ ምልክት ብቻ ነው የ ፎርም አካሎችን በሚታየው የ ተጠቃሚ ገጽታ ውስጥ: እርስዎ የሚሰሩ ከሆነ በ ማክሮስ: የ ማስኬጃ ጊዜ ያስታውሱ: መቆጣጠሪያ ጋር ሁል ጊዜ የሚደረሰው በ ስም ባህሪዎች ነው


ምርጫውን መደበቂያ

የ ጽሁፍ ምርጫ በ ተመረጠው መቆጣጠሪያው ላይ ይቆይ እንደሆን ትኩረቱ በ መቆጣጠሪያው ላይ ሳይሆን ሲቀር እርስዎ ካሰናዱ ምርጫ መደበቂያ ወደ "አይ" የ ተመረጠው ጽሁፍ ይቆያል እንደ ተመረጠ ትኩረቱ በ መቆጣጠሪያው ላይ ሳይሆን ሲቀር ጽሁፉን በያዘው ላይ ሳይሆን ሲቀር

ሰአት ደቂቃ

ተጠቃሚ ማስገባት የሚችለው አነስተኛ ጊዜ መወሰኛ

ስም

እያንዳንዱ መቆጣጠሪያ ሜዳ እና እያንዳንዱ ፎርም ስም አለው: የሚለይበት ባህሪ: ስሙ ይታያል በ ፎርም መቃኛ ውስጥ: እና ስሙን መጠቀም: የ መቆጣጠሪያ ሜዳ ማመሳከር ይቻላል ከ ማክሮስ ጋር: ነባር ማሰናጃው ስም ቀደም ብሎ ወስኗል የ ሜዳዎች ምልክት እና ቁጥር በ መጠቀም:

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ በ ማክሮስ የሚሰሩ ከሆነ: እርግጠኛ ይሁኑ የ መቆጣጠሪያ ስሞች ልዩ መሆናቸውን


ስሙ እንዲሁም ይጠቅማል በ ቡድን ለማድረግ የ ተለያዩ መቆጣጠሪያዎች በ አንድ ላይ መሆን የሚገባቸውን ተግባሮች: እንደ ሬዲዮ ቁልፍ ያሉ: ይህን ለማድረግ: ተመሳሳይ ስም ይስጡ ለ ሁሉም አባሎች በ ቡድን ውስጥ: የ ተመሳሳይ ስሞች መቆጣጠሪያ ከ ቡድን ውስጥ: በ ቡድን የሆኑ መቆጣጠሪያዎች በሚታይ ይወከላሉ በ መጠቀም የ ቡድን ሳጥን

ስፋት

የ አምድ ስፋት ማሰናጃ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ሜዳ በ ተሰጠው ክፍል ውስጥ በ LibreOffice ክፍል ምርጫ: እርስዎ ከ ፈለጉ ማስገባት ይችላሉ ዋጋ ተከትሎ ዋጋ ያለው መለኪያ ክፍል: ለምሳሌ: 2 ሴሚ

ስፋት

የ መቆጣጠሪያውን ስፋት መግለጫ

ሶስት ሁኔታ

የ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን የ ዜሮ ዋጋዎችን ይወክል እንደሆን መወሰኛ ለ ተገናኘው ዳታቤዝ ከ እውነት እና ሀሰት ዋጋዎች ሌላ ይህ ተግባር ዝግጁ የሚሆነው ዳታቤዝ ሶስት ሁኔታዎች የሚቀበል ከሆነ ነው: እውነት: ሀሰት እና ዜሮ

የ ማስታወሻ ምልክት

ሶስት ሁኔታ ባህሪዎች የሚገለጸው ለ ዳታቤዝ ፎርሞች ብቻ ነው ለ HTML ፎርሞች አይደለም


ሺዎች መለያያ

በ ቁጥር እና ገንዘብ ሜዳዎች የ ሺዎች መለያያ ይጠቀሙ እንደሆን እርስዎ መወሰን ይችላሉ

ሽፋን ማረሚያ

በ መወሰን የ ባህሪ ኮድ በ ንድፍ ዘዴዎች ውስጥ: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚያስገባውን በ ንድፍ ሜዳ ውስጥ

የ edit mask የሚወስነው የ ማስገቢያ ቦታዎች ቁጥር መጠን ነው: ተጠቃሚው ባህሪዎች ካስገባ የማይመልስ ወደ edit mask, ማስገቢያውን አይቀበልም ተጠቃሚው ከ ሜዳው በሚወጣ ጊዜ: እርስዎ የሚቀጥሉትን ባህሪዎች መግለጽ ይችላሉ ለ edit mask:

ባህሪ

ትርጉም

L

መደበኛ ጽሁፍ: ይህን ቦታ ማረም አይቻልም: ባህሪዎች የሚታዩት በ ተመሳሳይ ቦታ ነው በ Literal Mask.

a

እነዚህ ባህሪዎች a-z እና A-Z ማስገባት ይቻላል: አቢይ ባህሪዎችን መቀየር አይቻልም ወደ ታችኛው ጉዳይ ፊደል ባህሪዎች

A

እነዚህ ባህሪዎች A-Z ማስገባት ይቻላል: የ ታችኛው ጉዳይ ፊደል ከ ገባ: ራሱ በራሱ ወደ አቢይ ፊደል ይቀየራል

c

እነዚህ ባህሪዎች a-z: A-Z እና 0-9 ማስገባት ይቻላል: አቢይ ባህሪዎችን መቀየር አይቻልም ወደ ታችኛው ጉዳይ ፊደል ባህሪዎች

C

እነዚህ ባህሪዎች A-Z እና 0-9 ማስገባት ይቻላል: የ ታችኛው ጉዳይ ፊደል ካስገቡ: ራሱ በራሱ ይቀየራል ወደ አቢይ ፊደል

N

ከ 0-9 ላሉ ባህሪዎች ብቻ ማስገቢያ

x

ሁሉንም ሊታተም የሚችል ባህሪዎች ማስገባት ይችላሉ

X

ሁሉም ሊታተሙ የሚችሉ ባህሪዎች ማስገባት ይቻላል: የ ታችኛው ጉዳይ ፊደል ከ ተጠቀሙ: ራሱ በራሱ ወደ አቢይ ፊደል ይቀየራል


ለ literal mask "__.__.2000", ለምሳሌ: መግለጫ የ "NNLNNLLLLL" edit mask ስለዚህ ተጠቃሚው አራት አሀዝ ብቻ የ ቀን ቁጥር ማስገባት ይችላል

ቃል በ ቃል መሸፈኛ

ከ masked ሜዳዎች ጋር እርስዎ መወሰን ይችላሉ የ literal mask. የ literal mask የያዘው የ ፎርም መጀመሪያ ዋጋዎች ነው እና ሁል ጊዜ ይታያሉ ፎርሙ ከ ወረደ በኋላ የ ባህሪ ኮድ በ መጠቀም ለ Edit mask, እርስዎ ማስገቢያዎች መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚጽፈው ወደ የ masked ሜዳ ውስጥ

የ ማስታወሻ ምልክት

የ literal mask ሁል ጊዜ እርዝመቱ ተመሳሳይ መሆን አለበት ከ edit mask እርዝመት ጋር: ይህ ካልሆነ የ edit mask ተቆርጧል ወይንም በ ባዶ ተሞልቷል የ edit mask እርዝመት


በ መዝገብ ላይ መፈጸሚያ

በ ተመረጠው መቃኛ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ ላይ የ ተግባሮች ደንብ ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ የሚከተሉት የ ተግባር እቃዎች ናቸው: መዝገብ ማስቀመጫ: መተው: አዲስ መዝገብ: መዝገብ ማጥፊያ: ማነቃቂያ:

በሚጫኑ ጊዜ ትኩረቱን መውሰጃ

እርስዎ ይህን ምርጫ ካሰናዱ ለ "አዎ": የ መግፊያ ቁልፍ ትኩረት ያገኛል እርስዎ ቁልፉን በሚጫኑ ጊዜ

በራሱ መሙያ

የ በራሱ መሙያ ተግባር የሚያሳየው ዝርዝር ቀደም ብለው የገቡ ዝርዝሮችን ነው እርስዎ ማስገቢያ መጻፍ ከ ጀመሩ በኋላ

በርካታ ምርጫዎች

እርስዎን ከ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ ከ አንድ በላይ እቃ መምረጥ ያስችሎታል

ተችሏል

የ መቆጣጠሪያ ሜዳ አስችለው ከሆነ "ተችሏል" (አዎ): የ ፎርም ተጠቃሚው የ መቆጣጠሪያ ሜዳ መጠቀም ይችላል ባህሪው ተሰናክሎ ከሆነ: ማስቻል አይቻልም (አይ) እና ይታያል በ ግራጫ ቀለም

ተግባር

እርስዎ የ መቃኛ ተግባር ለ ንድፍ መጠቀም ይችላሉ በ እርስዎ የ ዳታቤዝ መቃኛ ቁልፍ ውስጥ

የሚቀጥለው ሰንጠረዥ እርስዎ ለ ቁልፍ መመደብ የሚችሉትን ተግባሮች ይገልጻል

ተግባር

መግለጫ

ምንም

ምንም ተግባር አልተፈጸመም

ማስገቢያ ፎርም

የ ገባውን ዳታ ወደ ሌላ መቆጣጠሪያ መላኪያ የ አሁኑን ፎርም ወደ ተወሰነው አድራሻ በ ፎርም ባህሪዎችURL.

ያስገቡ የ URL ወደ ዳታ ባህሪ ውስጥ "URL" በ ጽሁፍ ሳጥን ውስጥ እርስዎ በሚልኩ ጊዜ ወደ PDF ፋይል

ፎርም እንደነበር መመለሻ

ማሰናጃውን እንደ ነበር መመለሻ በ ሌሎች መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ውስጥ ወደ በ ቅድሚያ የተወሰኑ ነባሮች (ነባር ሁኔታዎች: ነባር ምርጫ: ነባር ዋጋ)

መክፈቻ ሰነድ / ድህረ ገጽ

መክፈቻ የ URL የ ተወሰነ በ URL እርስዎ መጠቀም ይችላሉ ክፈፍ የ ታለመውን ክፈፍ ለ መግለጽ

የ መጀመሪያው መዝገብ

የ አሁኑን ፎርም ወደ መጀመሪያው መዝገብ ማንቀሳቀሻ

ቀደም ያለው መዝገብ

የ አሁኑን ፎርም ቀደም ወዳለው መዝገብ ማንቀሳቀሻ

የሚቀጥለው መዝገብ

የ አሁኑን ፎርም ወደ ሚቀጥለው መዝገብ ማንቀሳቀሻ

የ መጨረሻው መዝገብ

የ አሁኑን ፎርም ወደ መጨረሻው መዝገብ ማንቀሳቀሻ

መዝገብ ማስቀመጫ

የ አሁኑን መዝገብ ማስቀመጫ: አስፈላጊ ከሆነ

የ ዳታ ማስገቢያን መተው

የ አሁኑን መዝገብ ለውጥ እንደ ነበር መመለሻ

አዲስ መዝገብ

የ አሁኑን ፎርም ወደ ረድፍ ማስገቢያ ማንቀሳቀሻ

መዝገብ ማጥፊያ

የ አሁኑን መዝገብ ማጥፊያ

ፎርም ማነቃቂያ

እንደገና መጫኛ በጣም በ ቅርብ ጊዜ የ ተቀመጠውን የ አሁኑን ፎርም እትም


ትልቅ ለውጥ

መወሰኛ ዋጋ ለ መጨመር ወይንም ለ መቀነስ ተጠቃሚው በሚጫን ጊዜ በ ተንሸራታች ላይ በ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ

ትንሽ ለውጥ

መወሰኛ ዋጋ ለ መጨመር ወይንም ለ መቀነስ ተጠቃሚው በሚጫን ጊዜ የ ቀስት ምልክቶች በ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ

ነባር ሁኔታው

መወሰኛ የ ምርጫ ወይንም የ ምልክት ማድረጊያ ሳጥኖች ይመረጡ እንዲሆን በ ነባር

ለ እንደ ነበር መመለሻ አይነት ቁልፍ: እርስዎ መግለጽ ይችላሉ ሁኔታውን ለ መቆጣጠሪያው: እንደ ነበር መመለሻ ቁልፍ በ ተጠቃሚ እንዲጀምር

ለ ቡድን ምርጫ ሜዳዎች: የ ቡድን ተመሳሳይ ለ ነባር ማሰናጃ የሚገለጸው በ ነባር ሁኔታ ባህሪ ነው

ነባር መሸብለያ ዋጋ

ነባር ዋጋ ለ መሸብለያ መደርደሪያ ማሰናጃ

ነባር ምርጫ

መወሰኛ የ ዝርዝር ሳጥን ማስገቢያ ምልክት ለማድረግ እንደ ነባር ማስገቢያ

ለ እንደ ነበር መመለሻ አይነት ቁልፍ: የ ነባር ምርጫዎች ማስገቢያ መግለጫ ለ ሁኔታው በ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ እንደ ነበር መመለሻ በ ተጠቃሚው ማስጀመሪያ

ለ ዝርዝር ሳጥን የ ዋጋ ዝርዝር የያዘ: እርስዎ መጫን ይችላሉ የ ... ቁልፍ ለ መክፈት የ ነባር ምርጫ ንግግር

ነባር ምርጫዎች ንግግር ውስጥ: ይምረጡ ማስገቢያዎች እርስዎ የሚፈልጉትን ምልክት ለማድረግ እንደ ተመረጠ እርስዎ ፎርም በሚከፍቱ ጊዜ የ ዝርዝር ሳጥን የያዘ

ነባር ሰአት

ነባር ሰአት ማሰናጃ

ነባር ቀን

ነባር ቀን ማሰናጃ

ነባር ቁልፍ

ነባር ቁልፍ ባህሪ የሚወስነው ተመሳሳይ ቁልፍ ይጀምራል እርስዎ ማስገቢያ ቁልፍ ሲጫኑ: እርስዎ ንግግር ከ ከፈቱ ወይንም ፎርም እና ሌላ ምንም ተግባር ካልፈጸሙ: ቁልፍ በዚህ ባህሪ ነባር ቁልፍ ነው

የ ማስታወሻ ምልክት

በ ሰነዱ ውስጥ ይህ ባህሪ መመደብ ያለበት ለ ነጠላ ቁልፍ ብቻ ነው


የ ዌብ ገጽ ፎርሞች በሚጠቀሙ ጊዜ: ምናልባት እነዚህ ባህሪዎች ጋር ይደርሱ ይሆናል በ መፈለጊያ masks ውስጥ: እነዚህ ናቸው የ edit masks የያዙ የ ጽሁፍ ሜዳ እና የ ማስገቢያ አይነት ቁልፍ: የ መፈለጊያ ደንብ ይገባል በ ጽሁፍ ሜዳ ውስጥ እና ፍለጋው ይጀመራል ቁልፉን በማስጀመር: ቁልፉ ከ ተገለጽ እንደ ነባር ቁልፍ: ነገር ግን በ ቀላሉ ማስገቢያውን ይጫኑ የ ፍለጋ ቃሉን ካስገቡ በኋላ ፍለጋውን ለ መጀመር

ነባር ዋጋ

ነባር ዋጋ ለ መቆጣጠሪያ ሜዳ ማሰናጃ ለምሳሌ: ነባር ዋጋ ይገባል ፎርም በሚከፈት ጊዜ

ለ እንደ ነበር መመለሻ አይነት ቁልፍ: የ ነባር ዋጋ ማስገቢያ መግለጫ ሁኔታውን በ መቆጣጠሪያ ውስጥ እንደ ነበር መመለሻ ቁልፍ በ ተጠቃሚው እንዲጀምር

ነባር ጽሁፍ

ነባር ጽሁፍ ማሰናጃ ለ ጽሁፍ ሳጥን ወይንም ለ መቀላቀያ ሳጥን

ንድፎች

የ ምስል ቁልፍ የ ንድፍ ባህሪዎች አለው ንድፍ ባህሪዎች የሚወስኑት የ ንድፍ መንገድ እና ስም ነው: እርስዎ እንዲታይ የሚፈልጉት በ ቁልፍ ላይ እርስዎ ከ መረጡ የ ንድፍ ፋይል መንገድ በ ... ቁልፍ ውስጥ: መንገድ እና የ ፋይል ስም በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ራሱ በራሱ ይካተታል

አቀማመጥ

በ ተመረጠው የ መቃኛ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ ላይ የ እቃዎች ቦታ ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ የሚከተሉት እቃዎች ናቸው ቦታቸው የሚቀየረው: የ መቅረጫ ምልክት: የ መቅረጫ ቦታ: የ መቅረጫ ምልክት መቁጠሪያ: የ መቅረጫ መቁጠሪያ:

አቀራረብ

የ አቀራረብ ኮድ ለ መቆጣጠሪያ መወሰኛ: ይጫኑ የ ... ቁልፍ የ አቀራረብ ኮድ ለ መምረጥ

አቅጣጫ

የ አግድም ወይንም የ ቁመት አቅጣጫ ለ መሸብለያ መደርደሪያ ወይንም ማሽከርከሪያ ቁልፍ መወሰኛ

አነስተኛ ቀን

ተጠቃሚ ማስገባት የሚችለው የ ቅድሚያ ቀን መወሰኛ

አነስተኛ ዋጋ

ለ ቁጥር እና ገንዘብ ሜዳዎች: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚያስገባውን አነስተኛ ዋጋ

እርዝመት

የ መቆጣጠሪያ እርዝመት መግለጫ

ከፍተኛ መሸብለያ ዋጋ

ከፍተኛ ዋጋ ለ መሸብለያ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ መወሰኛ

ከፍተኛ ሰአት

እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚያስገባውን ከፍተኛ ሰአት

ከፍተኛ ቀን

እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚያስገባውን ከፍተኛ ቀን

ከፍተኛ ዋጋ

ለ ቁጥር እና ገንዘብ ሜዳዎች: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጠቃሚ የሚያስገባውን ከፍተኛ ዋጋ

ከፍተኛ የ ጽሁፍ እርዝመት

ለ ጽሁፍ እና መቀላቀያ ሳጥኖች እርስዎ መወሰን ይችላሉ ከፍተኛውን ቁጥር ባህሪዎች ተጠቃሚ የሚያስገባውን: ይህ መቆጣጠሪያ ሜዳ ባህሪ አስተማማኝ ካልሆነ ነባር ማሰናጃው ዜሮ ይሆናል

መቆጣጠሪያ ከ ተገናኘ ከ ዳታቤዝ ጋር እና የ ጽሁፍ እርዝመት የሚቀበል ከሆነ ከ ዳታቤዝ መግለጫ ውስጥ: እርስዎ እዚህ የ ጽሁፍ እርዝመት ማስገባት የለብዎትም: ማሰናጃ የሚቀበለው ከ ዳታቤዝ ብቻ ነው መቆጣጠሪያ ባህሪ ካልተገለጸ ("አልተገለጸም" ሁኔታው)

ክፈፍ

እርስዎ እንዲሁም መወሰን ይችላሉ የ ታለመውን ክፈፍ ለ ማሳየት የ URL እርስዎ የ ከፈቱትን ቁልፍ በ መጫን የ ተመደበውን ለ Open document ወይንም ድህረ ገጽ ተግባር ).

እርስዎ ሜዳ ላይ ከ ተጫኑ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ከ ምርጫ ዝርዝር ውስጥ የሚወስን ወደ ክፈፍ ውስጥ ለሚጫነው የ ጽሁፍ ሰነድ: የሚቀጥሉት ምርጫዎች ይኖራሉ:

ማስገቢያ

ትርጉም

_ባዶ

የሚቀጥለው ሰነድ የተፈጠረው በ አዲስ ባዶ ክፈፍ ነው

_ወላጅ

የሚቀጥለው ሰነድ የሚፈጠረው በ ወላጅ ክፈፍ ነው: ምንም ወላጅ ከሌለ: ሰነድ ይፈጠራል በ ተመሳሳይ ክፈፍ ውስጥ

_ራስ

የሚቀጥለው ሰነድ የሚፈጠረው በ ተመሳሳይ ክፈፍ ነው

ከ _ላይ

የሚቀጥለው ሰነድ የሚፈጠረው በ ከፍተኛ-ደረጃ መስኮት ነው: ይህም ማለት: በ ከፍተኛው ክፈፍ ከ ቅደም ተከተል ውስጥ: የ አሁኑ ክፈፍ ከፍተኛ መስኮት ከሆነ: ሰነዱ የሚፈጠረው በ አሁኑ ክፈፍ ውስጥ ነው


የ ማስታወሻ ምልክት

የ ክፈፍ ባህሪ ዋጋ አለው ለ HTML ፎርሞች: ነገር ለ ዳታቤዝ ፎርሞች ዋጋ የለውም


ወደ ታች የሚዘረገፍ

የ መቆጣጠሪያ ሜዳ ከ ወደ ታች የሚዘረገፍ ባህሪ ተጨማሪ የ ቀስት ቁልፍ አለው የሚከፈት የ ነበረውን ማስገቢያዎች አይጥ በሚጫኒ ጊዜ: በ መስመር መቁጠሪያ ውስጥ: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ምን ያህል መስመሮች (ወይንም ረድፎች) እንደሚታዩ በ ወደ ታች በሚዘረገፍ ሁኔታ ውስጥ: መቀላቀያ ሜዳዎች ወደ ታች የሚዘረገፍ ባህሪ አላቸው

በ አምድ ውስጥ የ ገቡ መቀላቀያ ሳጥኖች በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ውስጥ በ ነባር ሁልጊዜ ወደ ታች የሚዘረገፍ ነው

ዋጋ

ተደበቀ መቆጣጠሪያ ስር በ ዋጋ ውስጥ: እርስዎ የ ተወረሰውን ዳታ ማስገባት ይችላሉ በ ተደበቀ መቆጣጠሪያ: ይህ ዳታ ይተላለፋል ፎርሙ በሚላክ ጊዜ

ዋጋ ማሰናጃ

እርስዎ የ ዋጋ ክፍተት በቅድሚያ ማሰናዳት ይችላሉ ለ ቁጥር እና ለ ገንዘብ ማዞሪያ ቁልፍ: ይጠቀሙ ቀስት ወደ ላይ እና ወደ ታች የ ማዞሪያ ቁልፍ ዋጋውን ለ መጨመር ወይንም ለ መቀነስ

ዘዴ

መወሰኛ የ ምልክት ማድረጊያ ሳጥኖች እና ምርጫ ቁልፎች ይታዩ እንደሆን በ 3ዲ መመልከቻ (ነባር) ወይንም በ ጠፍጣፋ መመልከቻ ውስጥ

ዝርዝር ማስገቢያዎች

እባክዎን ያስታውሱ የ ጠቃሚ ምክር ማመሳከሪያ ወደ ፊደል ገበታ መቆጣጠሪያ

በ ቅድሚያ የ ተገለጸ ነባር ማስገቢያ የሚገባው በ ነባር መቀላቀያ ምርጫ ሳጥን ውስጥ ነው

የ ማስታወሻ ምልክት

ማስታወሻ የ ዝርዝር ማስገቢያዎች እዚህ የገቡ የሚዋሀዱት ወደ የ ፎርም ከሆነ: ከ ዳታ tab ስር ዝርዝር ይዞታ አይነት ምርጫ "ዋጋ ዝርዝር" ይመረጣል


እርስዎ ካልፈለጉ የ ዝርዝር ማስገቢያዎች እንዲጻፉ ከ ዳታቤዝ ውስጥ ወይንም እንዲተላለፉ ወደ ተቀባይ ዌብ ፎርም ውስጥ: ነገር ግን ዋጋዎችን መመደብ በ ፎርም ውስጥ የማይታዩ: እርስዎ መመደብ ይችላሉ ዝርዝር ማስገቢያዎች ወደ ሌላ ዋጋዎች ውስጥ በ ዋጋ ዝርዝር ውስጥ: ዋጋው የሚወሰነው ከ ዳታ tab. ስር ዝርዝር ይዞታዎች አይነት ይምረጡ ከ ምርጫ "ዋጋ ዝርዝር": እና ከዛ ዋጋዎች ያስገቡ ከ ዝርዝር ይዞታዎች የሚመደቡ ወደ ተመሳሳይ የሚታዩ ዝርዝር ማስገቢያዎች ፎርም ውስጥ: ለ ትክክለኛ ስራ: የ ዋጋ ዝርዝር ደንብ አስፈላጊ ነው

የ ማስታወሻ ምልክት

ለ HTML ሰነዶች: ዝርዝር ማስገቢያ የሚገባው ባጠቃላይ tab ተመሳሳይ ነው ለ HTML tag <OPTION>ማስገቢያ ለ ዋጋ ዝርዝር የሚገባው ከ ዳታ tab ስር ነው ዝርዝር ይዞታው ተመሳሳይ ነው ለ <OPTION VALUE=...> tag.


የ Tab ደንብ

Tab ደንብ ባህሪ የሚወስነው ደንብ መቆጣጠሪያው እንዴት እንደሚያተኩር ነው በ ፎርም ውስጥ: እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ የ Tab ቁልፍ ከ አንድ በላይ መቆጣጠሪያ በያዘ ፎርም ውስጥ: ትኩረቱ ወደሚቀጥለው መቆጣጠሪያ ይንቀሳቀሳል እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ የ Tab ቁልፍ: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ደንቡን ትኩረቱ የሚቀየርበትን በ ማውጫ ውስጥ በ Tab ደንብ ውስጥ

የ ማስታወሻ ምልክት

Tab ደንብ ባህሪ ዝግጁ አይደለም ለ የ ተደበቀ መቆጣጠሪያ እርስዎ ከ ፈለጉ ማሰናዳት ይችላሉ ይህን ባህሪ ለ ምስል ቁልፎች እና ለ ምስል መቆጣጠሪያ: ስለዚህ እርስዎ መምረጥ ይችላሉ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች በ Tab ቁልፍ


ፎርም በሚፈጥሩ ጊዜ: ማውጫ ራሱ በራሱ ይመደባል ለ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ወደ እዚህ ፎርም ውስጥ የሚጨመሩ: እያንዳንዱ የ መቆጣጠሪያ ሜዳ የ ተጨመረው ማውጫ ይመድባል በ መጨመር በ 1. እርስዎ ከ ቀየሩ የ ማውጫ መቆጣጠሪያ: የ ሌሎች መቆጣጠሪያ ማውጫ ራሱ በራሱ ይሻሻላል: አካሎች ትኩረት ውስጥ የማይገቡ (ማስረጊያ ማስቆሚያ = አይ) እንዲሁም ዋጋ ይመድባሉ: ነገር ግን እነዚህ መቆጣጠሪያዎች ይዘለላሉ የ ማስረጊያ ቁልፍ ሲጠቀሙ

እርስዎ በ ቀላሉ መግለጽ ይችላሉ ማውጫዎች ለ ተለያዩ መቆጣጠሪያዎች በ Tab Order ንግግር ውስጥ

የ X ቦታ

መግለጫ የ X ቦታ መቆጣጠሪያ: ለ አንፃራዊ ማስቆሚያ

የ Y ቦታ

መግለጫ የ Y ቦታ መቆጣጠሪያ: ለ አንፃራዊ ማስቆሚያ

የ መሸብለያ ዋጋ አነስተኝ

አነስተኛ ዋጋ ለ መሸብለያ መደርደሪያ መቆጣጠሪያ መወሰኛ

የ መደቡ ቀለም

የ መደብ ቀለም ለ በርካታ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ዝግጁ ነው: እርስዎ ከ ተጫኑ በ መደብ ቀለም ላይ ዝርዝር ይከፈታል እርስዎ ከ ተለያዩ ቀለሞች ውስጥ መምረጥ የሚያስችሎት: የ "መደበኛ" ምርጫ የ ስርአቱን ማሰናጃ ይወስዳል: የሚፈለገው ቀለም ካልተገኘ ይጫኑ የ ... ቁልፍ ቀለም ለ መግለጽ በ ቀለም ንግግር ውስጥ

የ መግቢያ ቃል ባህሪዎች

ተጠቃሚው የ መግቢያ ቃል ካስገባ: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ባህሪዎች የሚታየውን በ ተጠቃሚ የ ተጻፈውን ከማሳየት ይልቅ: በ የ መግቢያ ቃል ባህሪ ማስገቢያ በ ASCII ኮድ የ ተፈለገውን ባህሪ: እርስዎ መጠቀም ይችላሉ ዋጋዎች ከ 0 ጀምሮ እስከ 255 ድረስ

የ ምክር ምልክት

ባህሪዎች እና የ አስኪ ኮዶች መታየት ይችላሉ በ የተለዩ ባህሪዎች ንግግር (ማስገቢያ - የተለዩ ባህሪዎች)


የ ምልክት መጠን

በ ተመረጠው የ መቃኛ መደርደሪያ ማሳያ ላይ ምልክት ትንሽ ወይንም ትልቅ ይሆን እንደሆን መወሰኛ

የ ምልክት ሜዳ

ለ ምልክት መቆጣጠሪያ ምንጭ መወሰኛ የ ምልክት ሜዳ ጽሁፍ ይጠቀማል ከ ዳታቤዝ ሜዳ ስም ይልቅ: ለምሳሌ: በ ማጣሪያ መቃኛ መፈለጊያ ንግግር ውስጥ: እና እንደ አምድ ስም በ ሰንጠረዥ መመልከቻ ውስጥ

አንድ ባህሪ ለ መግለጽ ለ ምልክት እንደ እርዳታ: ስለዚህ ተጠቃሚው መድረስ እንዲችል እዚህ መቆጣጠሪያ ጋር በ መጫን ባህሪዎ ከ ፊደል ገበታ ላይ: ያስገቡ ቲልዴ (~) ባህሪ ምልክት ከ ባህሪው ፊት ለ ፊት

የ ጽሁፍ ቡድን ክፈፍ ብቻ መጠቀም ይቻላል እንደ ምልክት ሜዳ የ ሬዲዮ ቁልፎች ሲጠቀሙ:ይህ ጽሁፍ ይፈጸማል ለ ሁሉም የ ሬዲዮ ቁልፎች ለ ተመሳሳይ ቡድን

እርስዎ ከ ተጫኑ በ ... ቁልፍ ከ ጽሁፍ ሜዳ አጠገብ ያለውን ይታይዎታል የ ምልክት ሜዳ ምርጫ ንግግር: ከ ዝርዝር ውስጥ ምልክት ይምረጡ

ይመርምሩ የ ምንም ስራ የለም ሳጥን ውስጥ: አገናኝ ከ መቆጣጠሪያ እና ከ ሜዳ ምልክት መመደቢያ መካከል ለማስወገድ

የ ምልክት ቀለም

በ መቆጣጠሪያ ውስጥ ለ ምልክቶች ቀለም ማሰናጃ: ለምሳሌ: ቀስቶች በ መሸብለያ መደርደሪያ ውስጥ

የ ረድፍ እርዝመት

በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ውስጥ: ለ ረድፍ እርዝመት ዋጋ ያስገቡ: እርስዎ ከ ፈለጉ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ: ይህን ተከትሎ ዋጋ ያለው የ መለኪያ ክፍል: ለምሳሌ: 2 ሴሚ

የ ሰአት አቀራረብ

እርስዎ መግለጽ ይችላሉ እንዲታይ የሚፈልጉትን የ ጊዜ አቀራረብ

የ ቀን አቀራረብ

በ ቀን ሜዳ እርስዎ መወሰን ይችላሉ የሚፈልጉትን የ ቀን አቀራረብ ንባብ

የ ማስታወሻ ምልክት

ሁሉም የ ሜዳዎች አቀራረብ (ቀን: ሰአት: ገንዘብ: ቁጥር) ራሱ በራሱ ይቀርባል በ ተመረጠው አቀራረብ እርስዎ እንደተዉት: እርስዎ በ ምንም መንገድ ቢያስገቡ


የ ቃላት መጨረሻ

ጽሁፍ ማሳያ ከ አንድ መስመር በላይ እርስዎን ያስችሎታል የ መስመር መጨረሻ መጠቀም በ ጽሁፍ ሳጥን ውስጥ: ስለዚህ እርስዎ ከ አንድ መስመር በላይ ጽሁፍ ማስገባት ይችላሉ: በ አጅ የ መስመር መጨረሻ ለማስገባት: ማስገቢያውን ቁልፍ ይጫኑ

የ ተወሰነ አቀራረብ

እርስዎ አቀራረብ መመርመር ይችላሉ በ መቆጣጠሪያ ሜዳ ውስጥ: በሚቀበል የ አቀራረብ ይዞታዎችን (ቀን: ሰአት: እና ወዘተ): የ አቀራረብ መከልከያ ከ ጀመረ (አዎ): የ ተፈቀደውን ባህሪዎች ብቻ ይቀበላል ለምሳሌ: በ ቀን ሜዳ ውስጥ: ቁጥር ብቻ ወይንም የ ቀን ምልክት ብቻ ይቀበላል: በ እርስዎ የ ፊደል ገበታ የተጻፉ ሁሉም ፊደሎች ይተዋሉ

የ አይጥ ጎማ መሸብለያ

ተጠቃሚ በ አይጥ መጠቆሚያ በሚሸበልል ጊዜ ዋጋው ይቀየር እንደሆን መወሰኛ: በፍጹም: ዋጋውን አትቀይር: ትኩረት በሚደረገበት ጊዜ: (ነባር) ዋጋው ይቀየራል መቆጣጠሪያው ትኩረት ሲያገኝ እና ጎማው በ መቆጣጠሪያው ላይ ሲሆን እና ሲሸበለል: ሁልጊዜ: ዋጋው ይቀየራል መቆጣጠሪያው ትኩረት ሲያገኝ እና ጎማው በ መቆጣጠሪያው ላይ ሲሆን እና ሲሸበለል: የትኛውም መቆጣጠሪያ ላይ ትኩረቱ ቢሆን

የ እርዳታ URL

መወሰኛ የ ቡድን ምልክት በ URL ፊደል የሚያመሳክረው የ እርዳታ ሰነድ እና መጥራት ይቻላል በ እርዳታ መቆጣጠሪያ ሜዳ እርዳታ ለ መቆጣጠሪያ ሜዳ እርዳታ የሚከፍተው ትኩረት ቦታ በ መቆጣጠሪያ ሜዳ እና ተጠቃሚዎች ሲጫኑ ነው F1.

የ እርዳታ ጽሁፍ

የ እርዳታ ጽሁፍ ጠቃሚ ምክር በ መቆጣጠሪያው ላይ ይታይ እንደሆን ምርጫ ማቅረቢያ ጠቃሚ ምክር የሚያሳየው ጽሁፍ በ ተጠቃሚ ዘዴ ውስጥ እርስዎ የ አይጥ መጠቆሚያውን በ መቆጣጠሪያው ላይ ሲያሳርፉ ነው

ለ URL አይነት ቁልፎች የ እርዳታ ጽሁፍ የሚቀርበው እንደ ተስፋፋ ጠቃሚ ምክር ነው: በ URL አድራሻ ፋንታ የ ሚገባው በ URL ስር ነው

የ እርዳታ ጽሁፍ

በ እያንዳንዱ መቆጣጠሪያ ውስጥ እርስዎ መወሰን ይችላሉ ተጨማሪ መረጃ መወሰኛ ወይንም መግለጫ ጽሁፍ ለ መቆጣጠሪያ ሜዳ: ይህ ባህሪ ፕሮግራመሮችን ይረዳል እንዲያስቀምጡ ተጨማሪ መረጃ መጠቀም የሚችሉት በ ፕሮግራም ኮድ ውስጥ: ይህን ሜዳ መጠቀም ይችላሉ: ለምሳሌ: ለ ተለዋዋጮች ወይንም ሌሎች መገምገሚያ ደንቦች

የ ዴሲማል ትክክለኛነት

በ ቁጥር እና ገንዘብ ሜዳዎች መካከል እርስዎ መወሰን ይችላሉ የ ቁጥር አሀዝ የሚታየውን በ ቀኝ በኩል ከ ዴሲማል ነጥብ በኋላ

የ ድንበር ቀለም

መወሰኛ የ ድንበር ቀለም ለ መቆጣጠሪያ የ ድንበር ባህሪ ማሰናጃ "ጠፍጣፋ" እይታ እንዳላቸው

የ ገንዘብ ምልክት

በ ገንዘብ ሜዳ ውስጥ: እርስዎ በቅድሚያ-መግለጽ ይችላሉ ለ ገንዘብ ምልክት ባህሪዎች በማስገባት ወይንም ሀረግ በ ገንዘብ ምልክት ባህሪ ውስጥ

የ ጽሁፍ መስመሮች የሚያልቁት በ

ለ ጽሁፍ ሜዳዎች: ይምረጡ የ መስመር መጨረሻ ኮድ ለ መጠቀም ጽሁፍ በሚጽፉ ጊዜ ወደ ዳታቤዝ አምድ ውስጥ

የ ጽሁፍ አይነት

የ መስመር መጨረሻ እና አቀራረብ በ መቆጣጠሪያ ሜዳ ውስጥ ማስቻያ: እንደ ጽሁፍ ሳጥን ወይንም ምልክት አይነት: በ እጅ የ መስመር መጨረሻ ለማስገባት ይጫኑ የ ማስገቢያ ቁልፍ ይምረጡ "በርካታ-መስመር ከ አቀራረብ ጋር" ለማስገባት የ ጽሁፍ አቀራረብ

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

እርስዎ ከ መረጡ የ ጽሁፍ አይነት "በርካታ-መስመር ከ አቀራረብ ጋር": እርስዎ ማጣመር አይችሉም ይህን መቆጣጠሪያ ከ ዳታቤዝ ሜዳዎች ጋር


የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ መቆጣጠሪያ የ ተሰየመው "በርካታ መስመር ማስገቢያ" ተብሎ ነው ለ ጽሁፍ አምድ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ውስጥ


የሚታይ

በ ቀጥታ ማስተላለፊያ ዘዴ ውስጥ መቆጣጠሪያው ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ: መቆጣጠሪያው ሁሉ ጊዜ ይታያል

ያስታውሱ ይህ ባህሪ መሰናዳቱን ወደ "አዎ" (በ ነባር): ይህ ማለት መቆጣጠሪያው በ መመልከቻው ላይ ይታያል ማለት አይደለም: ተጨማሪ መጠን ይፈጸማል የ መቆጣጠሪያ ተጽእኖ መመልከቻ ሲፈጸም: ለምሳሌ: መቆጣጠሪያ በ ተደበቀ ቦታ የ ተቀመጠ በ መጻፊያ ውስጥ በፍጹም አይታይም: እስከ ቢያንስ ክፍሉ ራሱ እስከሚታይ ድረስ

ባህሪው ከ ተሰናዳ ለ "አይ": ከዛ መቆጣጠሪያው ሁልጊዜ ይደበቃል በ ቀጥታ ዘዴ በሚተላለፍ ጊዜ

አሮጌው OpenOffice.org እትም እስከ 3.1 ይህን ባህሪ ይተወዋል ሰነድ የሚጠቀምበትን በሚያነብበት ጊዜ

የሚታይ መጠን

የ መሸብለያ መደርደሪያ መጠን መወሰኛ በ አውራ ጥፍር ልክ በ "ዋጋ ክፍሎች"ውስጥ: ዋጋ የ ("መሸብለያ ዋጋ ከፍተኛው" መቀነሻ "መሸብለያ ዋጋ ዝቅተኛው") / 2 ውጤቱ በ አውራ ጥፍር ልክ የ መደብ ግማሽ መጠን ይሆናል

ከ ተሰናዳ ለ 0 ከዛ የ አውራ ጥፍር ስፋት እኩል ይሆናል ከ እርዝመት ጋር

የሚጨምር./የሚቀንስ ዋጋ

ክፍተት መወሰኛ ለ መደመሪያ ወይንም ለ መቀነሻ በ እያንዳንዱ ማስጀመሪያ ጊዜ የ ማሽከርከሪያ ቁልፍ መቆጣጠሪያ

ድንበር

በ መቆጣጠሪያ ሜዳ ክፈፍ ባለው: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ድንበር ማሳያ በ ፎርም መጠቀሚያ ላይ በ ድንበር ባህሪዎች ውስጥ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ከ "ያለ ክፈፍ", "3-ዲ መመልከቻ" ወይንም "ጠፍጣፋ" ምርጫዎች

ፊደል

ለ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች የሚታይ ጽሁፍ ወይንም አርእስት ያላቸው: ይምረጡ የ ፊደል ማሳያ እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን: ለ መክፈት የ ፊደል ንግግር ውስጥ: ይጫኑ የ ... ቁልፍ: የ ተመረጠውን ፊደል ተጠቅሞበታል የ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ስሞች እና ዳታ በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ሜዳዎች ውስጥ ለማሳየት