የተለዩ ባህሪዎች ለ ሜዳ አቀራረብ

አቀራረብ: እርስዎ ማሰናዳት ይችላሉ የ አቀራረብ ባህሪ በ መጫን የ ... ቁልፍ ውስጥ በ አቀራረብ መስመር ከ ባህሪዎች: የ ሜዳ አቀራረብ ንግግር ውስጥ የ ቁጥር አቀራረብ ንግግር ይታያል

የ ሜዳ አቀራረብ የ ተገናኘ ከሆነ ከ ጽሁፍ ሜዳ ዳታቤዝ ጋር: በዚህ ሜዳ ውስጥ የሚገቡ እንደ ጽሁፍ ይወሰዳሉ: የ ሜዳ አቀራረብ የ ተገናኘ ከሆነ ከ ጽሁፍ ሜዳ ዳታቤዝ ጋር እና የሚታይ ከሆነ እንደ ቁጥር: በዚህ ሜዳ ውስጥ የሚገቡ እንደ ቁጥር ይወሰዳሉ: ቀን እና ሰአት የሚያዙት እንደ ውስጣዊ ቁጥር ነው

አነስተኛ ዋጋ እና ከፍተኛ ዋጋ : እርስዎ ማስገባት ይችላሉ አነስተኛ እና ከፍተኛ የ ቁጥር ዋጋዎች ሜዳ አቀራረብ: አነስተኛ እና ከፍተኛ ዋጋ የሚወስነው የ ነበረውን ዳታ ውጤት ነው (ለምሳሌ: አነስተኛ. ዋጋ 5, ነው: የተገናኘው ዳታቤዝ ሜዳ የያዘው ኢንቲጀር ዋጋ 3. ነው: ውጤቱ 5, ነው: ነገር ግን ዋጋው በ ዳታቤዝ ውስጥ አልተሻሻለም) እና ማስገቢያው ለ አዲስ ዳታ (ለምሳሌ: ከፍተኛ. ዋጋ 10 ነው እና እርስዎ ካስገቡ 20. ማስገቢያው ይታረማል እና10 ይጻፋል ከ ዳታቤዝ ውስጥ). ሜዳዎቹ ካልተሞሉ በ አነስተኛ ዋጋ እና ከፍተኛ ዋጋ ምንም መጠን አይፈጸምም: ለ ሜዳዎች አቀራረብ ከ ዳታቤዝ ጽሁፍ ሜዳ ጋር ለ ተገናኙ: እነዚህ ሁለት ዋጋዎች እና የ ነባር ዋጋ መፈጸም አይቻልም

ነባር ዋጋ: ይህ ዋጋ የተሰናዳው ለ አዲስ መዝገቦች እንደ ነባር ነው