የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ መጠቀሚያ

የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ አዲስ ማሳያ ዘዴ ነው ለ ትእዛዝ ምልክቶች በፍጥነት ለ መጠቀም

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

ይህ ገጽታ ለ ሙከረ ነው እና ስህተቶች ወይንም ያልተጠበቁ ውጤቶች ሊፈጥር ይችላል: ለማንኛውም ማስቻል ከፈለጉ ይምረጡ - LibreOffice - የረቀቀ እና ይምረጡ የ ሙከራ ገጽታ ማስቻያ ሳጥን ውስጥ ምልክት ያድርጉ


በ ነባር: LibreOffice ትእዛዞች በ ቡድን ይሆናሉ በ ዝርዝር ውስጥ እና የ እቃ መደርደሪያ በ ምልክቶች ይሞላል

የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ የሚያሳየው የ ተለየ መንገድ ነው ለማደራጀት መቆጣጠሪያዎችን እና ምልክቶችን ከ ቀጥታ ረድፎች እና ምልክቶች ስብስብ: የሚያሳየው የ ቡድኖች ስብስብ ለ ትእዛዝ ይዞታዎች ነው

በ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ላይ: ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙት ትእዛዞች በ ቡድን ውስጥ ተዘጋጅተዋል: በፍጥነት ለ መድረስ ያስችሎታል: ረጅም ዝርዝር ከ መቃኘት ይልቅ: እና የ እቃ መደርደሪያ ትእዛዝ ምልክቶች ከ መፈለግ ያድናል

የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ዝግጁ ነው ለ መጻፊያ: ሰንጠረዥ: እና ማስደነቂያ: የ ተጠቃሚ ገጽታ አሁን በርካታ ዝግጁ እቅዶች አሉት: ሁለት ማስገቢያዎች በ መመልከቻ ዝርዝር መቆጣጠሪያ በ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ውስጥ: የ እቃ መደርደሪያ እቅድ እና የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ.

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ዝርዝር መመልከቻ - እቃ መደርደሪያ እቅድ - የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ


የ ተጠቃሚ ገጽታ እቅዶች

የ እቃ መደርደሪያ እቅድ ማስገቢያ ይገልጻል የትኛው የ ተጠቃሚ ገጽታ አካላቶች እንደሚታዩ: ዝግጁ የሆኑት እቅዶች እነዚህ ናቸው:

ተጠቃሚ በሚያስጀምር ጊዜ ተጨማር እቃ መደርደሪያዎች: በ ተጠቃሚው ገጽታ ውስጥ ይቀመጣሉ: ስለዚህ በሚመለሱ ጊዜ የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ዘዴ: ሁሉንም የ ተሰናዱ የ በፊቱን እቃ መደርደሪያዎች ያሳያል

ዝግጁ የ ማስታወሻ ደብተር እቃ መደርደሪያ ዘዴዎች

የ ማስታወሻ ምልክት

በ ምልክት ዘዴ ውስጥ የ ዝርዝር ማሳያ ይደበቃል በ ነባር: ዝርዝር መደርደሪያውን ለማሳየት: ይምረጡ “≡” ምልክት ከ ላይ-በ ግራ ቦታ በኩል በ መስኮት ውስጥ እና ይምረጡ ዝርዝር መደርደሪያ


የ ምክር ምልክት

የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ምልክቶች ማስተካከል ይቻላል በ መሳሪያዎች - ምርጫዎች - LibreOffice - መመልከቻ - የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ


የ ማስታወሻ ምልክት

የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ማስተካከል አይቻልም


የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

የ አሁኑ መፈጸሚያ (LibreOffice 6.1) የ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ የ ተለመደ ነው ለ መጻፊያ: ሰንጠረዥ: እና ለ ማስደነቂያ ክፍሎች: ማንኛውም ለውጦች በ ማስታወሻ ደብተር መደርደሪያ ላይ የሚያደርጉት ተጽእኖ ይፈጥራል በሌሎች ክፍሎች ውስጥ