ፊደል ማረሚያ እና ሰዋሰው

ሰነድ ወይንም አሁን የ ተመረጠውን የ ፊደል ስህተት መመርመሪያ: የ ሰዋሰው መመርመሪያ ተጨማሪ ተገጥሞ ከሆነ: የ ሰዋሰው ስህተት ይመረመራል

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ መሳሪያዎች - ፊደል ማረሚያ

F7 ቁልፍ

መደበኛ መደርደሪያ ላይ ይጫኑ

ምልክት

ፊደል ማረሚያ


ፊደል እና ሰዋሰው በማረም ላይ

የ ፊደል ማረሚያ የሚጀምረው መጠቆሚያው አሁን ካለበት ቦታ ጀምሮ ነው: እና ይቀጥላል እስከ መጨረሻው ድረስ ወይንም እስከ ምርጫው ድረስ: እርስዎ ከዛ መምረጥ ይችላሉ ለ መቀጠል ፊደል ማረሙን ከ ሰነዱ መጀመሪያ ጀምሮ

ፊደል ማረሚያ የሚያየው የ ተሳሳቱ ፊደሎችን ነው: እና ለ እርስዎ ምርጫዎችን ያቀርባል እና የማይታወቅ ቃል ወደ መዝገበ ቃላት ውስጥ መጨመሪያ ምርጫ ያቀርባል: የ መጀመሪያው የ ተሳሳተ ፊደል ሲገኝ የ ፊደል ማረሚያ ንግግር ይከፈታል

የ ሰዋሰው መመርመሪያ ተጨማሪ ተገጥሞ ከሆነ: ንግግሩ ይጠራል ፊደል እና ሰዋሰው ማረሚያ የ ፊደል ስህተት ከስሩ በ ቀይ ቀለም ይሰመርበታል: የ ሰዋሰው ስህተት ከስሩ በ ሰማያዊ ቀለም ይሰመርበታል: ንግግሩ በ መጀመሪያ ሁሉንም የ ፊደል ስህተቶችን ያቀርባል እና ከዛ በኋላ ሁሉንም የ ሰዋሰው ስህተቶች በሙሉ ያቀርባል

ማስቻያ ሰዋሰው መመርመሪያ በ መጀመሪያ ሁሉንም የ ፊደል ስህተቶች ላይ እንዲሰራ እና ከዛ በኋላ ሁሉንም የ ሰዋሰው ስህተቶች ላይ እንዲሰራ

ዳይሬክቶሪ ውስጥ የለም

አረፍተ ነገር ማስያ የ ተሳሳተውን ቃል በማድመቅ: ቃሉን ያርሙ: ወይንም አረፍተ ነገሩን: ወይንም ይጫኑ ከ ታች በኩል በ ጽሁፍ ሳጥን ውስጥ ካለው ምርጫ ውስጥ

አስተያየቶች

ለ ተሳሳተው ቃል መቀየሪያ የሚሆን ዝርዝር ያቀርባል: እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን ቃል ይምረጡ: እና ከዛ ይጫኑ ማረሚያ ወይንም ሁሉንም ማረሚያ

የ ጽሁፍ ቋንቋ

ቋንቋ ይወስኑ ፊደል ማረሚያ ለ መጠቀም

የ ቋንቋ ማስገቢያ ምልክት ማድረጊያ አለው ከ ፊት ለ ፊት ፊደል ማረሚያው ከተመረጠ

ምርጫዎች

ንግግር መክፈቻ: እርስዎ የሚመርጡበት በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ መዝገበ ቃላት: እና ማሰናጃ ደንቦች ለ ፊደል ማረሚያ

መዝገበ ቃላት ማረሚያ

ያልታወቀውን ቃል በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ መዝገበ ቃላት ውስጥ መጨመሪያ

አንድ ጊዜ መተው

ያልታወቀውን ቃል ይዘል እና ፊደል ማረም ይቀጥላል

የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ ምልክት የዚህ ቁልፍ ይቀየራል ወደ ይቀጥሉ እርስዎ ፊደል ማረሚያውን ክፍት ከተዉት እና ወደ እርስዎ ሰነድ ከ ተመለሱ: ፊደል ማረሙን ለ መቀጠል ከ አሁኑ ቦታ መጠቆሚያው ካለበት ጀምሮ: ይጫኑ ይቀጥሉ


ሁሉንም መተው

ሁሉንም ሁኔታዎች እና ያልታወቀውን ቃል ይዘላል እስከ መጨረሻው LibreOffice ድረስ እና ፊደል ማረም ይቀጥላል

ማረሚያ

የ ማይታወቀውን ቃል በ አሁኑ ሀሳብ መቀየሪያ: እርስዎ በትክክል ያልተጻፈ ቃል ከ ቀየሩ: ጠቅላላ አረፍተ ነገሩ ይቀየራል

ሁሉንም ማረሚያ

ሁሉንም ሁኔታዎች መቀየሪያ ያልተወቀውን ቃል በ አሁኑ ሀሳብ ውስጥ

መተው

ይጫኑ ለ መተው የ መጨረሻውን ለውጥ በ አሁኑ አረፍተ ነገር ውስጥ: ይጫኑ እንደገና ለ መተው ቀደም ያለውን ለውጥ ለ መተው በ ተመሳሳይ አረፍተ ነገር ውስጥ