የ ቁጥሮች / አቀራረብ
ምድብ
ይምረጡ ምድብ ከ ዝርዝር ውስጥ: እና ከዛ ይምረጡ የ አቀራረብ ዘዴ በ አቀራረብ ሳጥን ውስጥ
ነባር የ ገንዘብ አቀራረብ ለ ክፍሉ የሚወሰነው በ እርስዎ መስሪያ ስርአት አካባቢ ማሰናጃ መሰረት በማድረግ ነው
አቀራረብ
የ ተመረጠው ክፍል(ሎች) ይዞታዎች እንዴት እንዲታይ እንደሚፈልጉ ይምረጡ ለ ተመረጠው ምርጫ ኮዱ የሚታየው በ ኮድ አቀራረብ ሳጥን ውስጥ ነው
የ ገንዘብ ምድብ በ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ
ገንዘብ ይምረጡ እና ከዛ ይሽብልሉ ወደ ላይ በ አቀራረብ ዝርዝር ውስጥ የ ገንዘብ አቀራረብ ምርጫ ለማየት
የ ገንዘብ አቀራረብ ኮድ ይህን ፎርም ይጠቀማል [$xxx-nnn], ይህ xxx የ ገንዘብ ምልክት ነው: እና ይህ nnn የ አገሩ ኮድ ነው: የ ተለዩ የ ባንክ ምልክቶች: እንደ EUR (ለ ኢዩሮ), የ አገር ኮድ አይፈልግም: የ ገንዘብ አቀራረብ ጥገኛ አይደለም እርስዎ ለ መረጡት ቋንቋ በ ቋንቋ ሳጥን ውስጥ
ቋንቋ
ቋንቋ ማሰናጃ ይወስኑ ለተመረጡት ክፍሎች ሜዳዎች በ ቋንቋ ማሰናጃ ወደ ራሱ በራሱ LibreOffice ራሱ በራሱ ይፈጽማል የ ቁጥር አቀራረብ የ ተዛመደውን ከ ስርአት ነባር ቋንቋ ጋር: ይምረጡ ማንኛውንም ቋንቋ ማሰናጃውን ለ መጠገን ለ ተመረጡት ክፍሎች ሜዳዎች
የ ቋንቋ ማሰናጃ ያረጋግጣል የ ቀን እና ገንዘብ አቀራረብ እንዲሁም የ ዴሲማል እና ሺዎች መለያያ እንደ ነበሩ ይቆያሉ: ሰነዱ በማንኛውም መስሪያ ስርአት ቢከፈት የ ተለየ የ ቋንቋ ማሰናጃ ቢጠቀሙም አይቀየርም
የ ምንጭ አቀራረብ
ተመሳሳይ የ ቁጥር አቀራረብ ይጠቀማል እንደ ክፍሎች በ ቻርትስ ውስጥ ዳታ የያዘው
ምርጫዎች
ለ ተመረጠው አቀራረብ ምርጫ መወሰኛ
የ ዴሲማል ቦታዎች
እርስዎ ማሳየት የሚፈልጉትን የ ዴሲማል ቦታዎች ያስገቡ
የ ተካፋይ ቦታዎች
በ ክፍልፋይ አቀራረብ: ያስገቡ የ ቦታዎች ቁጥር ለሚካፈለው እርስዎ ማሳየት ለሚፈልጉት
ቀዳሚ ዜሮዎች
ከ ዴሲማል ነጥብ በፊት ማሳየት የሚፈልጉትን ከፍተኛ የ ዜሮ ቁጥር ያስገቡ
አሉታዊ ቁጥሮች በ ቀይ
የ አሉታዊ ቁጥሮችን ፊደል ወደ ቀይ ቀለም መቀየሪያ
የ ሺዎችን መለያያ ይጠቀሙ
የ ሺዎች መለያያ ማስገቢያ: የ ሺዎች መለያያ እንደ ቋንቋ ማሰናጃዎች አይነት ይለያያል
የ ኤንጂኔር ምልክት
በ ሳይንሳዊ አቀራረብ: የ ኤንጂኔር ምልክት ያረጋግጣል ኤክስፖነንት የ 3. መልቲፕል መሆኑን
የ ኮድ አቀራረብ
የ ቁጥር አቀራረብ ኮድ ለ ተመረጠው አቀራረብ ማሳያ: እርስዎ እንዲሁም ማስገባት ይችላሉ የ አቀራረብ ማስተካከያ የሚቀጥሉት ምርጫዎች ብቻ ዝግጁ ናቸው ለ በተጠቃሚው-ለሚገለጽ የ ቁጥር አቀራረብ
መጨመሪያ
የ ቁጥር አቀራረብ ኮድ መጨመሪያ እርስዎ ያስገቡትን በተጠቃሚ-ለሚገለጽ ምድብ ውስጥ
ማጥፊያ
የ ተመረጠውን የ ቁጥር አቀራረብ ማጥፊያ ለውጡ የሚፈጸመው እንደገና ሲያስጀምሩ ነው LibreOffice.
አስተያየት ማረሚያ
ወደ ተመረጠው የ ቁጥር አቀራረብ አስተያየት መጨመሪያ
የ መስመር ስም
ወደ ተመረጠው የ ቁጥር አቀራረብ አስተያየት ማስገቢያ እና ከዛ ይጫኑ ከዚህ ሳጥን ውጪ