ባጠቃላይ ቃላት መፍቻ

ቃላት መፍቻ የሚገልጸው የ ቴክኒካል ደንቦችን ነው በ ስራ ላይ የሚገጥሞትን በሚሰሩ ጊዜ በ LibreOffice.

የ ቃላት መፍቻ ይጠቀሙ የማያውቁት ደንቦች ካጋጠምዎት በማንኛውም LibreOffice መተግበሪያ ውስጥ

DDE

DDE ማለት "Dynamic Data Exchange," ነው: ቀደም ብሎ የነበረ የ OLE, "እቃዎች ማገናኛ እና ማጣበቂያ" ነው: በ DDE, እቃዎች የሚገናኙት በ ፋይል ማመሳከሪያ ነው: በማጣበቅ አይደለም

እርስዎ መፍጠር ይችላሉ የ DDE አገናኝ የሚቀጥለውን አሰራር በ መጠቀም: ክፍሎች ይምረጡ ከ ሰንጠረዥ ውስጥ: ኮፒ ያድርጉ ወደ ቁራጭ ሰሌዳ ውስጥ እና ይቀይሩ ወደ ሌላ ሰንጠረዥ ውስጥ እና ይምረጡ የ ማረሚያ - የ ተለየ መለጠፊያ ንግግር: ይምረጡ አገናኝ ምርጫ ይዞታዎችን ለ ማስገባት እንደ የ DDE አገናኝ: አገናኙን በሚያስጀምሩ ጊዜ: የገባው ክፍል ቦታ ይነበባል ከ ዋናው ፋይል ውስጥ

IME

IME ማለት Input Method Editor ነው: ይህ ፕሮግራም እርስዎን መጠቀም ያስችሎታል ውስብስብ ባህሪዎችን ለ ማስገባት ምንም-ምእራባዊ ያልሆነ ባህሪ መደበኛ የ ፊደል ገበታ በ መጠቀም

JDBC

እርስዎ መጠቀም ይችላሉ የ Java Database Connectivity (JDBC) API ለ መገናኘት ወደ ዳታቤዝ ከ LibreOffice. JDBC drivers የ ተጻፉት በ Java programming language እና ነፃ መድረክ ነው

ODBC

Open Database Connectivity (ODBC) መደበኛ አሰራር ነው መተግበሪያዎች የ ዳታቤዝ ስርአት ጋር የሚደርስበት: የ ጥያቄ ቋንቋ የ ተጠቀሙት በ Structured Query Language (SQL) በ LibreOffice እርስዎ መወሰን ይችላሉ ለ እያንዳንዱ ዳታቤዝ: ይጠቀሙ እንደሆን ለ SQL ትእዛዞች ጥያቄዎች ማስኬጃ: በ አማራጭ እርስዎ መጠቀም ይችላሉ አንዱን በ አንዱ ላይ እርዳታ ለ መግለጽ የ እርስዎን ጥያቄ በ አይጥ ቁልፍ በ መጫን እና ራሱ በራሱ እንዲተረጉም ወደ SQL በ LibreOffice.

OLE

Object Linking and Embedding (OLE) እቃዎችን ማገናኘት ይቻላል ወደ ታለመው ሰነድ ውስጥ: ወይንም ይጣበቃል: ማጣበቂያ የ እቃውን ኮፒ ይለጥፋል እና ዝርዝር የ ፕሮግራም ምንጩን ወደ ታለመው ሰነድ ውስጥ ያስገባል: እርስዎ እቃውን ማረም ከ ፈለጉ: በ ቀላሉ የ ፕሮግራም ምንጩን ያስጀምሩ በ እቃው ላይ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ

OpenGL

OpenGL የሚወክለው የ 3ዲ ንድፍ ቋንቋ ነው: በ መጀመሪያ የ ተፈጠረው በ SGI (Silicon Graphics Inc). ሁለት ቋንቋ በ መደበኛ የሚጠቀሙት: Microsoft OpenGL, የ ተፈጠረው ለ መጠቀም ነው በ Windows NT, እና Cosmo OpenGL የ ተፈጠረው በ SGI. የ ኋለኛው የሚወክለው ነፃ የ ንድፍ ቋንቋ ነው ለ ሁሉም መድረክ: እና ሁሉም አይነት ኮምፒዩተሮች: መጠቀም ይችላሉ በ ኮምፒዩተሮች ላይ የ ተለየ የ 3-ዲ ንድፎች ለማይደግፍ ጠንካራ አካል

PNG

Portable Network Graphics (PNG) የ ንድፍ ፋይል አቀራረብ ነው: ፋይሎቹ የሚታመቁት በ ተመረጠ ማመቂያ ዘዴ ነው: እና ተቃራኒ ነው ለ JPG አቀራረብ: PNG ፋይሎች ሁልጊዜ የሚታመቁት ያለ ምንም መረጃ መጥፋት ነው

RTF

Rich Text Format (RTF) የ ፋይል አቀራረብ ነው የ ተፈጠረው የ ጽሁፍ ፋይሎች ለ መቀያየር ነው: የ ተለየ ገጽታ አቀራረብ ይቀየራል ወደ ሊነበብ ወደሚችል መረጃ ጽሁፍ በ ቀጥታ: ከ ሌሎች ፋይሎች አቀራረብ ጋር ሲነፃፀር ይህ አንፃራዊ ትልቅ ፋይሎች ይፈጥራል

SQL

Structured Query Language (SQL) ቋንቋ ነው ለ ዳታቤዝ ጥያቄዎች መጠቀሚያ በ LibreOffice እርስዎ ጥያቄዎች መፍጠር ይችላሉ በ አንዱ በ SQL ወይንም የ አይጥ መጠቆሚያውን በ መጠቀም

SQL ዳታቤዝ / SQL ሰርቨር

የ SQL database: የ ዳታቤዝ ስርአት ነው የሚያቀርበውም የ SQL ገጽታ ነው: የ SQL ዳታቤዞች ብዙ ጊዜ የሚጠቅመው ለ ደንበኞች/ሰርቨር ኔትዎርኮች ነው: የ ተለያዩ ደንበኞች ሰርቨሩ ጋር እንዲደርሱ ነው (ለምሳሌ: የ SQL ሰርቨር) ስለዚህ ይባላሉ የ SQL ሰርቨር ዳታቤዞች: ወይንም የ SQL ሰርቨሮች በ አጭሩ

በ LibreOffice: ውስጥ እርስዎ ማዋሀድ ይችላሉ የ ውጪ SQL ዳታቤዞች: እነዚህ የሚገኙት በ እርስዎ ሀርድ ዲስክ ውስጥ እንዲሁም ኔትዎርኮች ውስጥ ነው: እዚህ ጋር መድረስ የሚቻለው በ ODBC, JDBC, ወይንም የ native driver ሲዋሀድ ነው ወደ LibreOffice

መስኮቶች እና ብቸኛ መስመር

ብቸኛ እና ወላጅ የሌላቸው ታሪካዊ የ ህትመት ደንቦች ናቸው: ለ ብዙ አመታት ሲሰራባቸው የኖረ: ብቸኛ የሚያመለክተው አጭር መስመር ነው በ አንቀጽ መጨረሻ ላይ: ሰነዱ በሚታተም ጊዜ ብቻውን በሚቀጥለው ገጽ ላይ ይታያል: ወላጅ ከሌላቸው ጋር ሲነፃፀር: የ አንቀጽ የ መጀመሪያው መስመር ነው: ሰነዱ በሚታተም ጊዜ ብቻውን ከ ታች በኩል ይታያል: በ LibreOffice ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ: እርስዎ ራሱ በራሱ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎችን እንዲከለክል ማድረግ ይችላሉ በሚፈልጉት የ አንቀጽ ዘዴ: ይህን በሚያደርጉ ጊዜ እርስዎ መወሰን ይችላሉ አነስተኛውን የ መስመሮች መጠን በ አንድ ላይ በ ገጽ ውስጥ የሚሆኑትን

ማሳረፊያ

አንዳንድ መስኮቶች በ LibreOffice ለምሳሌ በ ዘዴዎች እና አቀራረብ መስኮት ውስጥ እና በ መቃኛ ውስጥ "ተንቀሳቃሽ" መስኮቶች ናቸው: እርስዎ ማንቀሳቀስ ይችላሉ እነዚህን መስኮቶች: እንደገና-መመጠን ወይንም ወደ ጠረዝ በኩል ማንቀሳቀስ ይችላሉ: በ እያንዳንዱ ጠርዝ ላይ እርስዎ በርካታ መስኮቶች በላዩ ላይ ማድረግ ይችላሉ ወይንም ከ እያንዳንዱ አጠገብ ለ አጠገብ እና ከዛ በ ማንቀሳቀስ የ ድንበር መስመሮች: እርስዎ መቀየር ይችላሉ የ መስኮቶችን አንፃራዊ መጠን

ለ ማባረር እና እንደገና-ለ ማሳረፍ ተጭነው ይያዙ የ ቁልፍ: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ባዶ ቦታ ላይ በ መስኮቱ ውስጥ: በ ዘዴዎች መስኮት ውስጥ: እርስዎ እንዲሁም ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ግራጫ ክፍል መስኮት ውስጥ ከ ምልክቱ አጠገብ: ተጭነው ይያዙ የ ቁልፍ

ማሳረፊያ (በራሱ መደበቂያ)

በ ማንኛውም የ መስኮት ጠርዝ ላይ ሌላ መስኮት ያረፈበት ለ እርስዎ ቁልፍ ይታያል ይህ እርስዎን የሚያስችለው መስኮቱን ማሳየት ወይንም መደበቅ ነው

ማስቀመጫ አንፃራዊ እና ፍጹም

በ ተለያዩ ንግግሮች ውስጥ (ለምሳሌ: መሳሪያዎች - በራሱ ጽሁፍ) እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ፋይሎችን ማስቀመጥ በ አንፃራዊ ወይንም በ ፍጹም

እርስዎ ከ መረጡ አንፃራዊ ማስቀመጫ: ማመሳከሪያ ወደ የ ተጣበቁ ንድፎች ወይንም ሌሎች እቃዎች በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ: በ ፋይል ስርአት ውስጥ በ አንፃራዊ ቦታ አካባቢ ይቀመጣል: ምናልባት ምንም አያስፈልግ ሊሆን ይችላል የ ተመሳከረው ዳይሬክቶሪ አካል የ ተመዘገበበት: ፋይሎቹ ይገኛሉ የትም አካባቢ ቢሆኑ: ማመሳከሪያው ተመሳሳይ አካል ወይንም መጠን እስከሆነ ድረስ: ይህ አስፈላጊ የሚሆነው እርስዎ ሰነዱን ዝግጁ ማድረግ ከፈለጉ ነው ለ ሌሎች ኮምፒዩተሮች የ ተለየ የ ዳይሬክቶሪ አካል ላላቸው: ወይንም አካል: የ መጠን ስሞች ላላቸው: እርስዎ በ አንፃራዊ መንገድ እንዲያስቀምጡ ይመከራሉ: እርስዎ መፍጠር ከ ፈለጉ የ ዳይሬክቶሪ አካል በ ኢንተርኔት ሰርቨር ላይ

እርስዎ ከ መረጡ ፍጹም ማስቀመጫ: ሁሉም የ ሌሎች ፋይሎች ማመሳከሪያዎች እንደ ፍጹም ይገለጻሉ: በ አካሉ አንጻር መሰረት: መጠን ወይንም root ዳይሬክቶሪ: ይህ ጥቅሙ ሰነዱ ማመሳከሪያ የያዘውን ማንቀሳቀስ ይቻላል ወደ ሌሎች ዳይሬክቶሪዎች ወይንም ፎልደሮች ውስጥ: እና ማመሳከሪያው ዋጋ እንዳለው ሆኖ ይቀራል

ማዞሪያ ቁልፍ

  1. በ ፎርም መቆጣጠሪያ: ማሽከርከሪያ ቁልፍ ንብረት ነው ለ ሂሳብ ሜዳ: የ ገንዘብ ሜዳ: የ ቀን ሜዳ: ወይንም የ ሰአት ሜዳ: ንብረቱ የ "ማሽከርከሪያ ቁልፍ" ካስቻሉ ሜዳው ያሳያል ጥንድ ምልክቶች ከ ቀስቶች መጠቆሚያ ጋር ወደ ተቃራኒ አቅጣጫዎች: በ ቁመት ወይንም በ አግድም

  2. በ Basic IDE, ማሽከርከሪያ ቁልፍ ስም ነው ለ ቁጥር ሜዳ ከ ሁለት ቀስት ምልክቶች ጋር የሚጠቀሙበት

እርስዎ መጻፍ ይችላሉ የ ቁጥር ዋጋ ወደ ሜዳ ውስጥ ከ ማዞሪያ ቁልፍ አጠገብ ባለው: ወይንም ይምረጡ ዋጋ በ ቀስት ወደ-ላይ ወይንም ቀስት ወደ-ታች ምልክቶችን ማዞሪያ ቁልፍ: በ ፊደል ገበታ ላይ ይጫኑ ገጽ ወደ ላይ እና ገጽ ወደ ታች ቁልፎችን: ከፍተኛ እና አነስተኛ ዋጋዎችን ለማሰናዳት

ከ ማሽከርከሪያ ቁልፍ አጠገብ ያለው ሜዳ የ ቁጥር ዋጋዎች የሚገልጽ ከሆነ እርስዎ መግለጽ ይችላሉ የ መለኪያ ክፍል ለምሳሌ: 1 ሴሚ ወይንም 5 ሚሚ: 12 ነጥብ ወይንም 2".

ቀዳሚ ቁልፍ

ቀዳሚ ቁልፍ የሚያገለግለው እንደ የተለየ መለያ ነው ለ ዳታቤዝ ሜዳዎች: የተለየ መለያ ለ ዳታቤዝ ሜዳዎች የሚጠቅመው ለ ተዛማጅ ዳታቤዝ ነው: በ ሌሎች ሰንጠረዥ ውስጥ ዳታ ጋር ለ መድረስ ነው: ማመሳከሪያ ከ ተፈጠረ ወደ ቀዳሚ ቁልፍ ከ ሌላ ሰንጠረዥ ውስጥ: ይህ የሚወሰደው እንደ እንግዳ ቁልፍ ነው

በ LibreOffice, እርስዎ ይግለጹ ቀዳሚ ቁልፍ በ ንድፍ ውስጥ: በ መምረጥ ተገቢውን ትእዛዝ ከ አገባብ ዝርዝር ከ ረድፍ ራስጌ ውስጥ: ለ ተመረጠው ሜዳ

በ ቀጥታ እና የ ዘዴዎች አቀራረብ

እርስዎ ያለ ዘዴዎች ሰነድ ካቀረቡ እንደ: "በ ቀጥታ" አቀራረብ: ይህ ማለት ጽሁፍ ማሻሻል ወይንም ሌሎች እቃዎች: እንደ ክፈፎች ወይንም ሰንጠረዦች: በ ቀጥታ በ ተለያዩ መለያዎች መፈጸም ነው: አቀራረብ የሚፈጸመው ለ ተመረጠው ቦታ እና ለ ሁሉም ለውጦች ለየብቻ መፈጸም አለበት: ዘዴዎች በ ሌላ አነጋገር: በ ጽሁፍ ላይ በ ቀጥታ አይፈጸሙም: ነገር ግን ይገለጻሉ በ ዘዴዎች እና አቀራረብ መስኮት ውስጥ እና ይፈጸማሉ: አንዱ ጥቅም እርስዎ ዘዴዎችን በሚቀይሩ ጊዜ: ዘዴው የ ተፈጸመበት ሁሉም አካል በ ሰነድ ውስጥ በ ተመሳሳይ ጊዜ ይሻሻላል

ማስወገድ ይችላሉ በቀጥታ አቀራረብ ከ እርስዎ ሰነዶች ውስጥ በመምረጥ ጠቅላላ ጽሁፉን በ አቋራጭ ቁልፎች +A እና ከዛ ይምረጡ አቀራረብ - በቀጥታ አቀራረብ ማጽጃ

በ እውነት-መመዝገቢያ

በ እውነት-መመዝገቢያ የ አጻጻፍ ደንብ ነው የሚጠቅመው ለ ማተሚያ ነው: ይህ ደንብ የሚመራው ወደ ተስማሚ ህትመት ለ መስመሮች በሚታተምበት ቦታ ላይ በ መጽሀፉ ፊት እና ኋላ ገጽ ላይ በትክክል እንዲታተም ነው: የ ጋዜጣ ገጾች እና የ መጽሄት ገጾች: በ እውነት-መመዝገቢያ ገጽታ እነዚህን ገጾች ለማንበብ ቀላል ያደርጋቸዋል: ግራጫ ጥላ እንዳያንጸባርቅ በ መከልከል: በ ጽሁፉ መሰመር ውስጥ: በ እውነት-መመዝገቢያ ደንብ እንዲሁም መስመሮችን ያመሳክራል በ አጓዳኝ የ ጽሁፍ አምዶች ውስጥ እኩል እርዝመት እንዳላቸው

እርስዎ አንቀጽ በሚገልጹ ጊዜ: የ አንቀጽ ዘዴ: ወይንም የ ገጽ ዘዴ እንደ በ እውነት-መመዝገቢያ: የ መሰረት መስመር የ ተጎዳው ባህሪ ይሰለፋል በ ቁመት ገጽ መጋጠሚያ ላይ: የ ፊደል መጠን ምንም ያህል ቢሆን ወይንም ንድፎች ቢገኙም: እርስዎ ከ ፈለጉ መወሰን ይችላሉ የ መጋጠሚያ ማሰናጃ ለዚህ መጋጠሚያ እንደ የ ገጽ ዘዴ ባህሪ

በ ፊደል መሀል ክፍተት

Kerning ማለት በ ፊደሎች መካከል ያለውን ክፍተት መጨመሪያ ወይንም መቀነሻ ነው ለማሻሻል የሚታየውን የ ጽሁፉን አቀራረብ ለማሳመር

በ ፊደል መሀል ክፍተት ማስተካከያ ሰንጠረዥ የያዘው መረጃ የትኞቹ ጥንድ ፊደሎች በርካታ ክፍተት እንደሚፈልጉ ነው: እነዚህ ሰንጠረዦች ባጠቃላይ የ ፊደል አካል ናቸው

አስኪ

አሕፃሮተ ቃል ለ American Standard Code for Information Interchange. ASCII ባህሪ ማሰናጃ ነው ፊደሎች ለማሳያ በ ግል ኮምፒዩተር ላይ: የያዛቸው 128 ባህሪዎች ናቸው: በውስጡ ፊደሎች እና ቁጥሮች ስርአተ ነጥብ እና ምልክቶች ይዟል: የ ተስፋፋ የ ASCII ባህሪ ማሰናጃ እስከ 256 ባህሪዎች መያዝ ይችላል: ለ እያንዳንዱ ባህሪ የ ተለየ ቁጥር ተመድቧል: እና ተመሳክሯል እንደ ASCII Code.

በ HTML ገጾች ውስጥ ባህሪዎች ብቻ የ 7 Bit ASCII ባህሪ ማሰናጃ ይታያል: ሌሎች ባህሪዎች እንደ German umlauts, ይለያሉ በ ተለየ ኮድ: እርስዎ ማስገባት ይችላሉ የ ተስፋፋ የ ASCII ኮድ ባህሪዎች: የ LibreOffice መላኪያ ማጣሪያ አስፈላጊ መቀየሪያ ይፈጽማል

አቀራረብ

አቀራረብ የሚመራው ወደ የሚታዩ የ ጽሁፍ እቅድ ነው በሚጠቀሙ ጊዜ ቃላት-ማቀናበሪያ ወይንም DTP ፕሮግራም: ይህ የ ወረቀት አቀራረብ መግለጽ: የ ገጽ ድንበር: ፊደሎች: የ ፊደል ውጤቶች: እንዲሁም ማስረጊያ እና ክፍተቶች ያካትታል: እርስዎ ጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ በ ቀጥታ ወይንም በ ዘዴዎች በቀረበው በ LibreOffice.

አገናኝ

አገናኝ ትእዛዝ የሚገኘው በ ማረሚያ ዝርዝር ውስጥ ነው: ይህን ትእዛዝ ማስጀመር የሚቻለው በ አሁኑ ሰነድ ውስጥ አንድ አገናኝ ሲኖር ነው: እርስዎ ስእል በሚያስገቡ ጊዜ: ለምሳሌ: እርስዎ ስእሉን በ ቀጥታ ወደ ሰነድ ውስጥ ወይንም ስእሉን እንደ አገናኝ ማስገባት ይችላሉ

እቃ ወደ ሰነድ ውስጥ በ ቀጥታ በሚገባ ጊዜ: የ ሰነዱ መጠን ይጨምራል በ (ቢያንስ) በ እቃው ባይት መጠን: እርስዎ ሰነዱን ማስቀመጥ እና መክፈት ይችላሉ በ ሌላ ኮምፒዩተር ውስጥ: እና ያስገቡት እቃ በ ሰነዱ ውስጥ በ ተመሳሳይ ቦታ ያገኙታል

እርስዎ እቃ ካስገቡ እንደ አገናኝ: ለ ፋይሉ ስም ብቻ ማመሳከሪያ ይገባል: የ ፋይሉ መጠን ለ ሰነዱ ይጨምራል በ መንገድ እና በ ፋይል ማመሳከሪያ ውስጥ: እርስዎ የ እርስዎን ሰነድ በሌላ ኮምፒዩተር ውስጥ ከ ከፈቱ: ነገር ግን: የ ተገናኘው ፋይል በ ተመሳሳይ ቦታ ውስጥ መገኘት አለበት እቃውን ለማየት በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ

ይጠቀሙ ማረሚያ - አገናኞች የትኞቹ ፋይሎች እንደ አገናኝ እንደገቡ: አስፈላጊ ከሆነ አገናኞቹን ማስወገድ ይቻላል: ይህ አገናኞቹን ይሰብራል እና እቃዎቹን በቀጥታ ያስገባል

እቃ

እቃ የ መመልከቻው አካል ነው ዳታ የያዘ: ወደ መተግበሪያ ዳታ ሊመራ ይችላል: እንደ ጽሁፍ ወይንም ንድፎች የመሰሉ

እቃዎች ነፃ ናቸው እያንዳንዳቸው ላይ ተፅእኖ አይፈጥሩም: ማንኛውም እቃ ዳታ የያዘ ለ ተወሰነ ትእዛዝ መመደብ ይቻላል: ለምስሌ: የ ንድፍ እቃ ትእዛዝ አለው ለ ምስል ማረሚያ እና ሰንጠረዥ የ ስሌቶች ትእዛዝ የያዘ

ውስብስብ የ ጽሁፍ እቅድ (CTL)

ቋንቋዎች በ ውስብስብ የ ጽሁፍ እቅድ የሚጻፉ ትንሽ ወይንም ሁሉም የሚከተሉት ገጽታዎች ይኖራቸዋል:

አሁን LibreOffice ይደግፋል ሂንዲ: ታዪ: ሂብሩ: እና አረብኛ እንደ CTL ቋንቋዎች

ያስችሉ CTL ድጋፍን በመጠቀም - ቋንቋ ማሰናጃ - ቋንቋዎች

ዝርዝር አገባብ

የ እቃውን አገባብ ዝርዝር ለማስጀመር በ መጀመሪያ እቃውን ይጫኑ በ የ አይጥ ቁልፍ ለመምረጥ እና ከዛ አንዳንድ የ አገባብ ዝርዝር መጥራት ይቻላል እቃው ባይመረጥም እንኳን: የ አገባብ ዝርዝር በ ሁሉም ቦታ ይገኛሉ በ LibreOffice.

የ ቁጥር ስርአት

የ ቁጥር ስርአት የሚወሰነው በ ቁጥር ባህሪዎች ነው ዝግጁ በሆኑ ቁጥሮች ለ መወከል: የ ዴሲማል ስርአት: ለምሳሌ አስር ቁጥሮች መሰረት ያደረገ ነው በ (0..9), የ ባይነሪ ስርአት መሰረት ያደረገው ሁለት ቁጥር ነው በ 0 እና 1, የ ሄክሳ ዴሲማል ስርአት መሰረት ያደረገው በ 16 ባህሪዎች ነው (0...9 እና A...F).

የ ቤዤ እቃ

የ ተፈጠረው በ ፋረንሳይ የ ሂሳብ አዋቂ Pierre Bézier, ነው የ ቤዤ ክብ በ ሂሳብ የሚገለጽ ክብ ነው: የሚጠቅመው ለ ሁለት-አቅጣጫ ንድፎች መተግበሪያ ነው: ክብ የሚገለጸው በ አራት ነጥቦች ነው: መነሻው ቦታ እና መጨረሻው ቦታ: እና ሁለት የ ተለያዩ የ መሀከል ነጥቦች አለው: የ ቤዤ እቃዎች ማሻሻል ይችላሉ ነጥቦችን በ አይጥ መጠቆሚያው በማንቀሳቀስ

የ ተዛመደ ዳታቤዝ

ተዛማጅ ዳታቤዝ የ ዳታ እቃዎች ስብስብ ነው የ ተደራጀ እንደ ስብስብ በ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚገለጽ: እርስዎ ዳታ መድረስ የሚችሉበት ወይንም እንደገና የሚዘጋጅበት በ ተለያየ መንገድ: የ ዳታቤዝ ሰንጠረዦችን እንደገና ሳያዘጋጁ

A relational database management system (RDBMS) ፕሮግራም ነው እርስዎን መፍጠር ያስችሎታል: ማሻሻል: እና ማስተዳደር ተዛማጅ ዳታቤዝ: የ RDBMS ይወስዳል የ Structured Query Language (SQL) አረፍተ ነገር ተጠቃሚ ያስገባውን ወይንም የ መተግበሪያ ፕሮግራም የያዘውን እና ይፈጥራል: ያሻሽላል ወይንም ወደ ዳታቤዝ ጋር መድረስ ያስችላል

ጥሩ ምሳሌ ለ ተዛማጅ ዳታቤዙ ሲይዝ ነው ደንበኛ: ግዢ: እና የ ፋክቱር ሰንጠረዥ: በ ፋክቱር ሰንጠረዥ ውስጥ ትክክለኛ ደንበኛ የለም: ወይንም የ ግዢ ዳታ: ነገር ግን ሰንጠረዡ ማመሳከሪያዎች ይዟል ከ ተዛማጅ አገናኝ ጋራ: ወይንም ተዛማጅ ከ ደንበኛ አንጻር እና የ ግዢ ሰንጠረዥ ሜዳዎች: (ለምሳሌ: የ ደንበኛ መለያ ሜዳ ከ ደንበኛ ሰንጠረዥ ውስጥ).