LibreOffice የመሳያ ገጽታዎች
LibreOffice መሳያ እርስዎን መፍጠር ያስችሎታል ቀላል እና ውስብስብ ስእሎች እና በተለመደ በርካታ የ ምስል አቀራረብ መላክ ያስችሎታል: እርስዎ እንዲሁም ማስገባት ይችላሉ ሰንጠረዦች: ቻርትስ: መቀመሪያ እና ሌሎች የተፈጠሩ በ LibreOffice ፕሮግራሞች ወደ እርስዎ መሳያዎች ውስጥ
የ Vector ንድፎች
LibreOffice መሳያ የ አቅጣጫ ንድፎች መፍጠር ያስችሎታል መስመሮች እና ክቦች በ ሂሳባዊ አቅጣጫ የተገለጹ በ መጠቀም: አቅጣጫዎች መስሮች ይገልጻሉ: ኤሊፕሶች እና ፖሊጎኖች እንደ ጂዮሜትሪ ቅርጻቹ ይለያያል
3ዲ እቃዎች መፍጠሪያ
እርስዎ መፍጠር ይችላሉ የ 3ዲ እቃዎች እንደ ኪዩብስ: ስፌርስ: እና ሲሊንደሮች በ LibreOffice መሳያ እና የ እቃውን ብርሃን ምንጭ በማሻሻል
መጋጠሚያዎች እና መቁረጫ መስመሮች
መጋጠሚያ እና መቁረጫ የሚያቀርቡት ጠቃሚ የ መመልከቻ እርዳታ እርስዎ በ መሳያ ውስጥ እቃዎችን በ ትክክል እንዲያሰልፉ ነው: እርስዎ እንዲሁም መምረጥ ይችላሉ እቃዎችን መቁረጥ በ መጋጠሚያ መስመር ላይ: እና በ መቁረጫ መስመር ላይ: ወይንም በ ሌላ እቃ ጠርዝ ላይ
እቃዎችን ማገናኛ ግንኙነታቸውን ለማሳያ
እርስዎ እቃዎችን ማገናኘት ይችላሉ በ LibreOffice መሳያ በ ተለዩ መስመሮች "አገናኞች" በሚባሉ: በ እቃዎች መካከል ግንኙነታቸውን ለማሳየት: አገናኞች መገጠሚያ ነጥቦችን ያያይዛሉ በ መሳያ እቃዎች ውስጥ እና የ ተያያዙት እቃዎች ሲወገዱ እንደ ነበሩ ይቆያሉ: አገናኞች ጠቃሚ ናቸው ለ ድርጅት ቻርትስ እና ቴክኒካል ንድፎችን ለ መፍጠር
አቅጣጫ ማሳያ
ቴክኒካል ንድፎች ብዙ ጊዜ የሚያሳዩት በ መሳያ ውስጥ የ እቃዎችን አቅጣጫ ነው: በ LibreOffice መሳያ: እርስዎ የ አቅጣጫን መስመር መጠቀም ይችላሉ ለ ማስላት እና ቀጥተኛ አቅጣጫ ለማሳየት
አዳራሽ
አዳራሽ የ ያዛቸው ምስሎች፡ እንቅስቃሴዎች፡ ድምፆች እና ሌሎች እቃዎችን ለማስገቢያ እና በ እርስዎ ስእል ውስጥ ለመጠቀሚያ ነው እንዲሁም የሌሎችን LibreOffice programs.
የንድፍ ፋይል አቀራረብ
LibreOffice መሳያ በርካታ የንድፍ ፋይሎች መላክ ያስችላል ለምሳሌ እንደ BMP, GIF, JPG, እና PNG.