የ ክፍል ይዞታዎች ማረጋገጫ

ለ እያንዳንዱ ክፍል: እርስዎ ዋጋ ያለው ማስገቢያ መግለጽ አለብዎት: ዋጋ የሌለው ማስገቢያ ወደ ክፍል ውስጥ አይቀበልም

የ ማስጠንቀቂያ ምልክት

የ ማረጋገጫ ደንብ አዲስ ዋጋ በሚገባ ጊዜ ይጀምራል: ዋጋ የሌለው ዋጋ ወደ ክፍሉ ውስጥ ገብቶ ከ ነበረ: ወይንም እርስዎ ዋጋ ካስገቡ ወይንም በ መጎተት-እና-በመጣል ወይንም ኮፒ በማድረግ እና በ መለጠፍ በ ክፍሉ ውስጥ ካስገቡ የ ማረጋገጫ ደንብ አይፈጸምም


የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ መምረጥ ይችላሉ መሳሪያዎች - መርማሪ በ ማንኛውም ጊዜ እና ይምረጡ ትእዛዝ ዋጋ የ ሌለው ዳታ ላይ ምልክት ማድረጊያ ለ ማሳየት የትኞቹ ክፍሎች ዋጋ የሌለው ዋጋዎች እንደያዙ


የ ክፍል ይዞታዎች ማረጋገጫ መጠቀሚያ

  1. ይምረጡ ክፍሎች እርስዎ አዲስ ማረጋገጫ ደንብ መግለጽ ለሚፈልጉት

  2. ይምረጡ ዳታ - ማረጋገጫ

  3. መመዘኛ tab ገጽ ውስጥ: ያስገቡ ሁኔታዎችን ለ አዲስ ዋጋዎች ወደ ክፍሎች ውስጥ የሚገቡትን

  4. መፍቀጃ ሜዳ: ይምረጡ ምርጫ

  5. እርስዎ ከ መረጡ የ "ሙሉ ቁጥሮች": ዋጋዎች እንደ "12.5" ያለ አይፈቀድም: ይምረጡ "ቀን" የሚያስችለው የ ቀን መረጃ ማግኘት ነው በ ሁለቱም በ አካባቢ ቀን አቀራረብ እንዲሁም በዚህ ፎርም በ ተከታታይ ቀን በ ተመሳሳይ: የ "ሰአት" ሁኔታ የሚፈቅደው የ ጊዜ ዋጋዎችን እንደ "12:00" ወይንም ተከታታይ የ ጊዜ ቁጥሮችን ነው: "የ ጽሁፍ እርዝመት" ስምምነት ለ ክፍሎች የሚያስችለው ጽሁፍ ብቻ እንዲይዙ ነው

    ይምረጡ "ዝርዝር" ለ ማስገባት ዋጋ ያለው ዝርዝር ማስገቢያ

  6. ይምረጡ የሚቀጥለውን ሁኔታ ከ ዳታ ውስጥ እርስዎ እንደ መረጡት: ተጨማሪ ምርጫዎች ሊመረጡ ይችላሉ

እርስዎ ሁኔታዎችን ከ ወሰኑ በኋላ ለ ክፍል ማረጋገጫ: እርስዎ ሁለቱን tab ገጾች መጠቀም ይችላሉ የ መልእክት ሳጥኖች ለ መፍጠር:

የ ስህተት መልእክት ለማሳየት: ይምረጡ የ ስህተት መልእክት ማሳያ ዋጋ የሌለው ዋጋዎች በሚገቡ ጊዜ

ናሙና ማክሮስ:

Function ExampleValidity(CellValue as String, TableCell as String)
Dim msg as string
msg = "Invalid value: " & "'" & CellValue & "'"
msg = msg & " in table: " & "'" & TableCell & "'"
MsgBox msg ,16,"Error message"
End Function

የ ማስታወሻ ምልክት

ለ ክፍሉ ተግባሩን ከ ቀየሩ በኋላ በ ስህተት ማስጠንቀቂያ tab ገጽ እና ንግግር መዝጊያ በ እሺ: እርስዎ መጀመሪያ ሌላ ክፍል መምረጥ አለብዎት ለውጡ ከ መፈጸሙ በፊት