በ ሰንጠረዥ ውስጥ መፈለጊያ እና መቀየሪያ
በ ሰንጠረዥ ሰነዶች ውስጥ እርስዎ ቃላቶች: መቀመሪያዎች: እና ዘዴዎች ያገኛሉ: እርስዎ መቃኘት ይችላሉ ከ አንዱ ውጤት ወደ ሌላው: ወይንም እርስዎ ሁሉንም ተመሳሳዮች ማድመቅ ይችላሉ በ አንድ ጊዜ: እና ከዛ መፈጸም ይችላሉ አቀራረቡን ወይንም መቀየር የ ክፍሉን ይዞታ በ ሌላ ይዞታ
መፈለጊያ & መተኪያ ንግግር
ክፍሎች ጽሁፍ ወይንም ቁጥሮች መያዝ ይችላሉ በ ቀጥታ የገቡ እንደ የ ጽሁፍ ሰነድ: ነገር ግን እንዲሁም ጽሁፍ ወይንም ቁጥሮች መያዝ ይችላሉ እንደ ውጤት ለ ስሌቶች: ለምሳሌ: ክፍል ከያዘ መቀመሪያ =1+2 ውጤት 3 ያሳያል: እርስዎ መወሰን አለብዎት የሚፈልጉትን ለ 1 የተዛመደውን 2 ወይንም መፈለጊያ 3
መቀመሪያ ወይንም ዋጋዎች ለ ማግኘት
እርስዎ መግለጽ ይችላሉ በ መፈለጊያ & መቀየሪያ ንግግር ውስጥ አንዱን አካሉን መፈለጊያ በ መቀመሪያ ውስጥ ወይንም ውጤቶች ማስሊያ
-
ይምረጡ ማረሚያ - መፈለጊያ & መቀየሪያ የ መፈለጊያ & መቀየሪያ ንግግር ለ መክፈት
-
ይጫኑ ተጨማሪ ምርጫዎች ንግግሩን ለማስፋት
-
ይምረጡ "መቀመሪያ" ወይንም "ዋጋዎች" በ መፈለጊያ በ ዝርዝር ሳጥኖች ውስጥ
በ "መቀመሪያ" እርስዎ ያገኛሉ ሁሉንም የ መቀመሪያ አካሎች
በ "ዋጋዎች" እርስዎ ያገኛሉ ሁሉንም የ ስሌት ውጤቶች
የ ክፍል ይዞታዎች የተለየ አቀራረብ አላቸው: ለምሳሌ: ቁጥሮች እንደ ገንዘብ መቅረብ ይችላሉ: የ ገንዘብ ምልክት እያሳዩ: ለ እርስዎ የ ገንዘብ ምልክት በ ክፍሉ ውስጥ ይታያል: ነገር ግን መፈለግ አይችሉም
ጽሁፍ መፈለጊያ
-
ይምረጡ ማረሚያ - መፈለጊያ & መቀየሪያ ለ መክፈት መፈለጊያ & ንግግር መቀየሪያ
-
የሚፈልጉትን ጽሁፍ ያስገቡ በ መፈለጊያው የ ጽሁፍ ሳጥን ውስጥ
-
አንዱን ይጫኑ ቀጥሎ መፈለጊያ ወይንም ሁሉንም መፈለጊያ
እርስዎ ሲጫኑ ቀጥሎ መፈለጊያ ሰንጠረዥ የሚቀጥለውን ክፍል ይመርጣል እርስዎ የሚፈልጉትን ጽሁፍ የያዘውን: እርስዎ መመልከት እና ማረም ይችላሉ ጽሁፉን: እና ከዛ ይምረጡ ቀጥሎ መፈለጊያ እንደገና ቀጥሎ ወደሚሀኘው ጽሁፍ ያመራል
-
ንግግሩን ከ ዘጉት የ ቁልፍ ጥምረቶችን መጠቀም ይችላሉ (ትእዛዝCtrl+Shift+F) የሚቀጥለውን ጽሁፍ ለማግኘት ንግግሩን ሳይከፍቱ
-
በ ነባር: ሰንጠረዥ ይፈልጋል የ አሁኑን ወረቀት: ይመርምሩ የ ሁሉንም ወረቀቶች ሳጥን ውስጥ በ ሁሉም ወረቀቶች በ ሰነዱ ውስጥ ለ መፈለግ
እርስዎ በ ሚጫኑ ጊዜ ሁሉንም መፈለጊያ ሰንጠረዥ ሁሉንም ክፍሎች ይመርጣል እርስዎ ያስገቡትን ጽሁፍ የያዘውን: እርስዎ አሁን ለምሳሌ ማሰናዳት ይችላሉ ሁሉንም የ ተገኙትን ክፍሎች ማድመቅ: መፈጸም ይችላሉ የ ክፍል ዘዴ ለ ሁሉም በ አንድ ጊዜ
መቃኛው
-
ይምረጡ መመልከቻ - መቃኛ የ መቃኛ መስኮቱን ለ መክፈት
መቃኛ ዋናው መሳሪያ ነው እቃ ለ ማግኛ እና ለ መምረጫ
መቃኛውን ይጠቀሙ እቃዎችን ለ ማስገባት እና ለማገናኘት በ ተመሳሳይ ሰነድ ውስጥ ወይንም ሌሎች ከ ተከፈቱ ሰነዶች ውስጥ