በ ሰንጠረዥ ውስጥ ማስሊያ

የሚቀጥለው የ ስሌት ምሳሌ ነው በ LibreOffice ሰንጠረዥ ውስጥ

  1. ይጫኑ በ ክፍል ውስጥ እና ቁጥር ይጻፉ

  2. ይጫኑ ማስገቢያውን

    መጠቆሚያው ወደ ታች ወደሚቀጥለው ክፍል ይሄዳል

  3. ሌላ ቁጥር ያስገቡ

  4. ይጫኑ የ Tab ቁልፍ

    መጠቆሚያው ወደ ቀኝ ወደሚቀጥለው ክፍል ይሄዳል

  5. ይጻፉ መቀመሪያ: ለምሳሌ =A3 * A4 / 100.

  6. ይጫኑ ማስገቢያውን

    የ መቀመሪያው ውጠት በ ክፍል ውስጥ ይታያል: እርስዎ መቀመሪያ ማረም ይችላሉ በ ማስገቢያው መስመር ላይ በ መቀመሪያ መደርደሪያ ላይ

    እርስዎ መቀመሪያ በሚያርሙ ጊዜ: አዲሱ ውጤት ራሱ በራሱ ይሰላል