በክፍሎች ውስጥ በተጠቃሚው የሚወሰኑ ድንበሮች

ለ ተመረጡት ክፍሎች የ ተለያዩ አይነት መስመሮች መጠቀም ይችላሉ

  1. ክፍል ወይንም በርካታ ክፍሎች ይምረጡ

  2. ይምረጡ አቀራረብ - ክፍሎች

  3. ከ ንግግሩ ውስጥ ይጫኑ ድንበሮች tab.

  4. ይምረጡ መጠቀም የሚፈልጉትን የ ድንበር ምርጫ እና ይጫኑ እሺ

ከ ምርጫዎች በ መስመር ማዘጋጃ ቦታ ለ በርካታ ድንበር ዘዴዎች መፈጸሚያ መጠቀም ይችላሉ

ክፍሎች መምረጫ

እንደ ክፍሉ ምርጫ ቦታው የተለያየ መልክ ይኖረዋል

ምርጫዎች

የ መስመር ማዘጋጃ ቦታ

አንድ ክፍል

ድንበሮች ከ አንድ ክፍል ጋር ተመርጧል

ክፍሎች በ አምድ ውስጥ

ድንበሮች ከ አምድ ጋር ተመርጧል

ክፍሎች በ ረድፍ ውስጥ

ድንበሮች ከ ረድፍ ጋር ተመርጧል

ጠቅላላ ክፍሎች 2x2 ወይንም ተጨማሪ

ንበሮች የተከለከለ ተመርጧል


የ ማስታወሻ ምልክት

ድንበሮችን በበርካታ ምርጫዎች ውስጥ መፈጸም አይችሉም


ነባር ማሰናጃዎች

ይጫኑ አንዱን ነባር ምልክት በርካታ ድንበሮችን ለማሰናዳት ወይንም እንደ ነበር ለመመለስ

ለምሳሌ

ይምረጡ በግምት ባለ 8x8 ክፍሎች እና ይምረጡ አቀራረብ - ክፍሎች - ድንበሮች

ነባር ምልክት የ ረድፍ ድንበሮች tab ገጽ

አሁን እርስዎ ይቀጥሉ መመልከት የትኛው መስመር በሌላው ምልክት እንደሚሰናዳ ወይንም እንደሚወገድ አሁን ለ እርስዎ ይታያል

በተጠቃሚው የሚወሰኑ ማሰናጃዎች

ተጠቃሚው የሚወሰን ቦታ: ይጫኑ እያንዳንዱን መስመር ለማዘጋጀት ወይንም ለማስወገድ: ቅድመ እይታው የሚያሳው መስመሮችን በ ሶስት የተለያያ ሁኔታ ነው

በ ተከታታይ ይጫኑ በ ጠርዙ ወይንም በ ድንበሩ ላይ ለ መቀያየር ሶስቱን የተለያዩ ሁኔታዎች

የ መስመር አይነቶች

ምስል

ትርጉም

ጥቁር መስመር

ሙሉ መስመር በ ተጠቃሚው የሚወሰን ድንበር

የ ጥቁር መስመር ማሰናጃ ለ ተመሳሳይ መስመር ለ ተመረጡት ክፍሎች: መስመሩ የሚታየው በ ነጠብጣብ መስመር ነው እርስዎ ሲመርጡ የ 0.05 ነጥብ መስመር ዘዴ: ድርብ መስመሮች የሚታዩት እርስዎ የ ድርብ መስመር ዘዴ ሲመርጡ ነው

ግራጫ መስመር

ግራጫ መስመር በ ተጠቃሚው የሚወሰን ድንበር

ግራጫ መስመር ይታያል: ተመሳሳይ መስመር ለ ክፍሉ ሲመረጥ አይቀየርም: በዚህ ቦታ ላይ ምንም መስመር አይሰናዳም ወይንም አይወገድም

ነጭ መስመር

ነጭ መስመር በ ተጠቃሚው የሚወሰን ድንበር

ነጭ መስመር ይታያል: ተመሳሳይ መስመር ለ ክፍሉ ሲመረጥ ይወገዳል


ለምሳሌ

ነጠላ ክፍል ይምረጡ እና ከዛ ይምረጡ አቀራረብ - ክፍሎች - ድንበሮች

ይጫኑ የታችኛውን ጠርዝ ለማሰናዳት ቀጭን መስመር እንደ ዝቅተኛ ድንበር: ሁሉም ሌሎች መስመሮች ከ ክፍሉ ውስጥ ይወገዳሉ

ቀጭን የ ታች ድንበር ማሰናጃ

ይምረጡ ወፍራም የ መስመር ዘዴ እና ይጫኑ የታችኛውን ጠርዝ: ይህ ወፍራም መስመር እንደ ዝቅተኛ ድንበር ያሰናዳል

ወፍራም መስመር እንደ ድንበር ማሰናጃ

ይጫኑ ሁለተኛውን ነባር ምልክት ከ ግራ በኩል አራቱንም ድንበሮች ለማሰናዳት: ከዚያ በተከታታይ ይጫኑ በ ታችኛው ጠርዝ ላይ ነጭ መስመር እስከሚታይ ድረስ: ይህ የ ታችኛውን ድንበር ያስወግደዋል

የ ታችኛውን ድንበር ማስወገጃ

እርስዎ መቀላቀል ይችላሉ በርካታ የ መስመር አይነቶች እና ዘዴዎች: የ መጨረሻው ምስል የሚያሳየው ወፍራም ድንበሮች እንዴት እንደሚያሰናዱ ነው (ወፍራም ጥቁር መስመሮች) ማንኛውም ሰያፍ መስመሮች በ ክፍሉ ውስጥ ምንም አይነኩም (ግራጫ መስመሮች)

ለ ክፍል ድንበሮች የ ረቀቀ ምሳሌ