አመት ክፍልፋይ
ውጤቱ የ አመቶች ቁጥር ነው (የ ክፍልፋይ ክፍልም ያካትታል) በ መጀመሪያ ቀን እና መጨረሻ ቀን.መካከል
አገባብ
የ አመት ክፍልፋይ(መጀመሪያ ቀን: መጨረሻ ቀን: መሰረቶች)
መጀመሪያ ቀን እና መጨረሻ ቀን ሁለት የ ቀን ዋጋዎች ናቸው
መሰረት (በ ምርጫ) ከ ዝርዝር ውስጥ የሚመረጥ ምርጫ ነው እና የሚያሳየው አመት እንዴት እንደሚሰላ ነው
መሰረት |
ስሌት |
0 ወይንም አልተገኘም |
በ US ዘዴ (NASD), 12 ወሮች እያንዳንዳቸው 30 ቀኖች አላቸው |
1 |
በ ወሮች ውስጥ ትክክለኛው የ ቀኖች ቁጥር: ትክክለኛው የ ቀኖች ቁጥር በ አመት ውስጥ |
2 |
በ ወሮች ውስጥ ትክክለኛው የ ቀኖች ቁጥር: በ አመት ውስጥ 360 ቀኖች አሉ |
3 |
በ ወር ውስጥ ትክክለኛው የ ቀኖች ቁጥር: በ አመት ውስጥ 365 ቀኖች አሉ |
4 |
በ አውሮፓውያን ዘዴ: 12 ወሮች እያንዳንዳቸው 30 ቀኖች አላቸው |
ለምሳሌ
ምን የ አመት ክፍልፋይ 2008 ይውላል በ 2008-01-01 እና 2008-07-01 መካከል?
=አመት ክፍልፋይ("2008-01-01"; "2008-07-01";0) ይመልሳል 0.50.