የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ

የ ስራ ቀኖች ይመልሳል በ መጀመሪያ ቀን እና በ መጨረሻ ቀን መካከል ውስጥ ያሉትን: እርስዎ ምርጫዎች መግለጽ ይችላሉ የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች እና የ አመት በአሎች: የ ሳምንቱ መጨረሻ ደንብ (ወይንም ሀረግ) መጠቀም ይችላሉ ለ መግለጽ የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች (ወይንም የ ምንም-ስራ የለም ቀኖች በ እያንዳንዱ ሳምንት ውስጥ). እንዲሁም በ ምርጫ ተጠቃሚው መግለጽ ይችላል የ አመት በአሎች ዝርዝር: የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች እና በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ የ አመት በአሎች አይቆጠሩም እንደ የ ስራ ቀኖች

አገባብ

የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ(መጀመሪያ ቀን: መጨረሻ ቀን: የ ሳምንት መጨረሻ: የ አመት በአሎች)

መጀመሪያ ቀን ስሌቱ የሚጀመርበት ቀን ነው: የ መጀመሪያው ቀን የ ስራ ቀን ከሆነ: ቀኑ በ ስሌቱ ውስጥ ይካተታል

መጨረሻ ቀን ስሌቱ እስከሚፈጸምበት ድረስ ያለው መጨረሻ ቀን ነው: የ መጨረሻው ቀን የ ስራ ቀን ከሆነ በ ስሌቱ ውስጥ ይካተታል

የ ሳምንቱ መጨረሻ በ ምርጫ ደንብ ነው – ቁጥር ወይንም ሀረግ ይጠቀማል ለ መወሰን ቀኖችን የ ሳምንቱን: የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች የሆኑትን እና እንደ የ ስራ ቀን አይወሰዱም: የ ሳምንቱ መጨረሻ የ ሳምንቱ መጨረሻ ቁጥር ነው ወይንም ሀረግ የሚገልጽ የ ሳምንቱ መጨረሻ መቼ እንደሚሆን: የ ሳምንቱ መጨረሻ ቁጥር ዋጋዎች የሚያሳየው የሚቀጥሉትን የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች ነው:

ቁጥር 1 እስከ 7 ለ ሁለት-ቀን የ ሳምንት መጨረሻ እና 11 እስከ 17 ለ አንድ-ቀን የ ሳምንት መጨረሻ

ቁጥር

የ ሳምንት መጨረሻ

1 ወይንም የማይታይ

ቅዳሜ እና እሑድ

2

እሑድ እና ሰኞ

3

ሰኞ እና ማከሰኞ

4

ማክሰኞ እና ረቡዕ

5

ረቡዕ እና ሐሙስ

6

ሐሙስ እና አርብ

7

አርብ እና ቅዳሜ

11

እሑድ ብቻ

12

ሰኞ ብቻ

13

ማክሰኞ ብቻ

14

ራቡዕ ብቻ

15

ሐሙስ ብቻ

16

አርብ ብቻ

17

ቅዳሜ ብቻ


የ ሳምንት መጨረሻ ሀረግ የሚያቀርበው ሌላ መንገድ ነው ለ መግለጽ የ ሳምንቱን ምንም-የ ስራ ቀኖች ያልሆኑ: ይህ ይኖረዋል ሰባት (7) ባህሪዎች – ዜሮዎች (0) ለ ስራ ቀን እና አንድ (1) ምንም-የ ስራ ቀኖች ያልሆኑ: እያንዳንዱ ባህሪ የሚወክለው ቀን ነው በ ሳምንት ውስጥ: ከ ሰኞ በ መጀመር: 1 እና 0 ብቻ ዋጋ ይኖራቸዋል: “1111111” ዋጋ የሌለው ሀረግ ነው: እና መጠቀም የለብዎትም: ለምሳሌ: የ ሳምንት መጨረሻ ሀረግ “0000011” የሚገልጸው ቅዳሜ እና እሑድ ነው እንደ ምንም-የ ስራ ቀኖች ያልሆኑ:

አመት በአል በ ምርጫ የ ቀኖች ዝርዝር ነው የሚቆጠር እንደ ምንም-የ ስራ ቀኖች ያልሆኑ: ዝርዝር ሊሰጥ ይችላል በ ክፍል መጠን ውስጥ:

ለምሳሌ

ምን ያህል የ ስራ ቀኖች ይኖራሉ በ ታሕሳስ 15, 2016 እና ጥር 14, 2017? የ መጀመሪያው ቀን የሚገኘው በ C3 ውስጥ ነው እና መጨረሻው ቀን በ D3. ውስጥ ነውልልል ክፍሎቹ F3 እስከ J3 የያዙት አምስት (5) በአሎችን ለ ገና ልደት እና አዲስ አመት በ ቀን አቀራረብ ውስጥ: ታሕሳስ 24, 2016; ታሕሳስ 25, 2016; ታሕሳስ 26, 2016; ታሕሳስ 31, 2016; እና ጥር 1, 2017.

=የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ(C3;D3;;F3:J3) ይመልሳል 21 የ ስራ ቀኖች ከ ነባር የ ሳምንቱ መጨረሻ ቀኖች ጋር

=የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ(C3;D3;11;F3:J3) ይመልሳል 24 የ ስራ ቀኖች እሑድ ብቻ እንደ የ ሳምንቱ መጨረሻ ጋር

በ አማራጭ: ይጠቀሙ የ ሳምንት መጨረሻ ሀረግ “0000001” ለ መግለጽ እሑድ እንደ ምንም-የ ስራ ቀን አይደለም በየ ሳምንቱ

=የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ(C3;D3;“0000001”;F3:J3) ይመልሳል 24 የ ስራ ቀኖች እሑድ ብቻ እንደ የ ሳምንቱ መጨረሻ ጋር

ተግባር መጠቀም ይችላሉ ያለ ሁለቱ ምርጫ ደንቦች – የ ስራ ቀን እና የ አመት በአሎች – በ መተው:

=የ ኔትዎርክ ቀኖች.አለም አቀፍ(C3;D3) ይመልሳል 22 የ ስራ ቀኖች