ማነፃፀሪያ ተግባር

የ ማነፃፀሪያ አንቀሳቃሽ ሁለት መግለጫዎችን ያወዳድራል: ውጤቱ የሚመለሰው በ ቡልያን መግለጫ ነው ማነፃፀሪያውን በሚወስነው እውነት (-1) ወይንም ሀሰት (0).

አገባብ:

ውጤት = መግለጫ1 { = | < | > | <= | >= } መግለጫ2

ደንቦች:

ውጤት: የ ቡልያን መግለጫ የሚወስነው በ ማነፃፀር (እውነት ወይንም ሀሰት)

መግለጫ1, መግለጫ2: እርስዎ ማወዳደር የሚፈልጉት ማንኛውም የ ቁጥር ዋጋዎች ሀረግ

የ ማነፃፀሪያ አንቀሳቃሾች

= : እኩል ነው ከ

< : ያንሳል ከ

> : ይበልጣል ከ

<= : ያንሳል ወይም አኩል ይሆናል ከ

>= : ይበልጣል ወይንም እኩል ይሆናል ከ

<> : እኩል አይሆንም ከ

ለምሳሌ:

Sub ExampleUnequal

Dim sFile As String

Dim sRoot As String ' Root directory for file in and output

    sRoot = "c:\"

    sFile = Dir$( sRoot ,22)

    If sFile <> "" Then

        Do

            MsgBox sFile

            sFile = Dir$

        Loop Until sFile = ""

    End If

End Sub