አረፍተ ነገር መክፈቻ

መክፈቻ የ ዳታ ጣቢያ

አገባብ:

መክፈቻ የ ፋይል ስም እንደ ሀረግ [ለ ዘዴ] [Access IOMode] [የሚጠበቅ] እንደ [#]የ ፋይል ቁጥር እንደ ኢንቲጀር [እርዝመት = የ ዳታ እርዝመት ማሰናጃ]

ደንቦች:

የ ፋይል ስም: እርስዎ መክፈት ለሚፈልጉት ፋይል መንገድ እና ስም ያስገቡ: እርስዎ ያልነበረ ፋይል ለማንበብ ሙከራ ካደረጉ (ፍቃድ = ለ ንባብ): የ ስህተት መልእክት ይታያል: እርስዎ ያልነበረ ፋይል ላይ ለ መጻፍ ሙከራ ካደረጉ (ፍቃድ = ለ መጻፍ) አዲስ ፋይል ይፈጠራል

ዘዴ: ይህ ቁልፍ ቃል የሚወስነው የ ፋይል ዘዴ ነው: ዋጋ ያላቸው ዋጋዎች: መጨመሪያ (መጨመሪያ ወደ ተከታታይ ፋይል), Binary (ዳታ ጋር መድረስ ይቻላል ባይቶች በ መጠቀም Get እና Put), ማስገቢያ (የ ዳታ ጣቢያ ይከፍታል ለ ንባብ), ውጤት (የ ዳታ ጣቢያ ይከፍታል ለ መጻፊያ), እና በደፈናው (አንፃራዊ ፋይሎች ማረሚያ ነው).

IOMode: ቁልፍ ቃል የ ፍቃድ አይነት የሚገልጽ: ዋጋ ያላቸው ዋጋዎች: ለ ንባብ (ለ ንባብ-ብቻ), መጻፊያ (ለ መጻፊያ-ብቻ), ለ ንባብ: ለ መጻፊያ (ለ ሁለቱም)

የሚጠበቅ: ቁልፍ ቃል የ ደህንነት ሁኔታ የሚገልጽ ፋይሉ ከ ተከፈተ በኋላ: ዋጋ ያላቸው ዋጋዎች: የሚካፈሉት (ፋይሉ በ ሌላ መተግበሪያ ተከፍቶ ይሆናል), እንዳይነበብ መቆለፊያ (ፋይሉ እንዳይነበብ ይጠበቃል), እንዳይጻፍበት መቆለፊያ (ፋይሉ እንዳይጻፍበት ይጠበቃል), መቆለፊያ ንባብ እና መጻፊያ (ፋይሉ ጋር መድረስ አልተቻለም)

የ ፋይል ቁጥር: ማንኛውም የ ኢንቲጀር መግለጫ ከ 0 እስከ 511 ድረስ የሚያሳየው የ ነፃ ዳታ ጣቢያ ቁጥር ነው: እርስዎ ትእዛዝ ማሳለፍ ይችላሉ ከ ዳታ ጣቢያ ፋይል ጋር ለ መድረስ: የ ፋይል ቁጥር የሚወሰነው ወዲያውኑ በ ነፃ ፋይል ተግባር ነው ከ ተከፈተው አረፍተ ነገር በፊት

የ ዳታ እርዝመት ማሰናጃ: በደፈናው ፋይሎች ጋር ለ መድረስ: የ መዝገቦች እርዝመት ማሰናጃ

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ ማሻሻል የሚችሉት የ ተከፈተ ፋይል ይዞታ ብቻ ነው በ መክፈቻ አረፍተ ነገር: እርስዎ የ ተከፈተ ፋይል ለ መክፈት ሙከራ ካደረጉ: የ ስህተት መልእክት ይታያል


ለምሳሌ:

Sub ExampleWorkWithAFile

Dim iNumber As Integer

Dim sLine As String

Dim aFile As String

Dim sMsg As String

    aFile = "c:\data.txt"

    iNumber = Freefile

    Open aFile For Output As #iNumber

    Print #iNumber, "This is a line of text"

    Print #iNumber, "This is another line of text"

    Close #iNumber

    iNumber = Freefile

    Open aFile For Input As iNumber

    While Not eof(iNumber)

        Line Input #iNumber, sLine

        If sLine <>"" Then

            sMsg = sMsg & sLine & chr(13)

        End If

    Wend

    Close #iNumber

    MsgBox sMsg

End Sub