ንግግር በ ፕሮግራም ኮድ መክፈቻ

LibreOffice መሰረታዊ መስኮት ንግግር ውስጥ እርስዎ በ ፈጠሩት: የ ንግግር ማረሚያውን መተው ይችላሉ በ መጫን የ ስም tab ላይ በ ክፍል ንግግር መመደቢያ ውስጥ: የ ስም tab ከ መስኮቱ በ ታች በኩል ነው

የሚቀጥለውን ኮድ ያስገቡ ንዑስ ተከታታይ ፕሮግራም የተባለ ንግግር1 ማሳያ በዚህ ምሳሌ ውስጥ: የ ንግግሩን ስም እርስዎ የ ፈጠሩት ነው "ንግግር1":

Sub Dialog1Show

    BasicLibraries.LoadLibrary("Tools")

    oDialog1 = LoadDialog("Standard", "Dialog1")

    oDialog1.Execute()

End Sub

ይህን ሳይጠቀሙ "የ መጫኛ ንግግር" እርስዎ እንደሚከተለው ኮድ መጥራት ይችላሉ:

Sub Dialog1Show

    DialogLibraries.LoadLibrary("Standard")

    oDialog1 = CreateUnoDialog( DialogLibraries.Standard.Dialog1 )

    oDialog1.Execute()

End Sub

ይህን ኮድ ሲያስኬዱ "ንግግር1" ይከፈታል: ንግግሩን ለ መዝጋት ይጫኑ የ መዝጊያ ቁልፍ (x) በ አርእስት መደርደሪያው ላይ