LibreOffice የ መጻፊያ ገጽታዎች

LibreOffice መጻፊያ የ ጽሁፍ ሰነዶች እና ንድፎች መፍጠር ያስችሎታል: እንዲሁም ንድፎች: ሰንጠረዥ: ወይንም ቻርትስ: እርስዎ ሰነዶቹን በሚፈልጉት አቀራረብ ማስቀመጥ ይችላሉ: እንዲሁም በ መደበኛ የ OpenDocument format (ODF), Microsoft Word .doc format, ወይንም HTML. እና በ ቀላሉ ሰነዶችን ማስተላለፍ ይችላሉ ወደ Portable Document Format (PDF).

በ መጻፍ ላይ

LibreOffice መጻፊያ መሰረታዊ ሰነዶችን መፍጠር ያስችሎታል: ለምሳሌ እንደ ማስታወሻ ፋክሶች ደብዳቤዎች: ማመልከቻዎች እና ሰነዶችን ማዋሀጃ እንዲሁም ረጅም እና ውስብስብ ወይንም በርካታ-ክፍል ያላቸው ሰነዶች ማመሳከሪያዎች: ማመሳከሪያ ሰንጠረዦች እና ማውጫዎች መፍጠር ያስችሎታል

LibreOffice መጻፊያ ብዙ ጠቃሚ ገጻታዎች ይዟል እንደ ፊደል ማረሚያ : የ ተመሳሳይ : በራሱ አራሚ : እና ጭረት እና የተለያዩ ቴምፕሌቶች መፍጠሪያ አዋቂ ይዟል

ንድፍ እና ግንባታ

LibreOffice ለ ሰነዶች እቅድ ሰፊ የተለያያ ምርጫዎችን ያቀርባል: ይጠቀሙ የ ዘዴዎች መስኮት ለ መፍጠር ለ መንደፍ እና የ አንቀጽ ዘዴዎችን ለማሻሻል: እያንዳንዱን ባህሪዎች: ክፈፎቸ እና ገጾች: በ ተጨማሪ: መቃኛ ይረዳዎታል በ ፍጥነት በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ለ መዘዋወር: የ እርስዎን ሰነድ በ እቅድ መመልከቻ ለ ማየት: እንዲሁም በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ያስገቡዋቸውን እቃዎች መቆጣጠር ያስችሎታል

እንዲሁም መፍጠር ይችላሉ የተለያዩ ማውጫዎች እና ሰንጠረዦች በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ: አካሎችን እና የ ማውጫ አቀራረብ እና ሰንጠረዦችን እንደ እርስዎ ፍላጎት መግለጽ ይችላሉ: Live hyperlinks እና ምልክት ማድረጊያዎች እንዲሁም በ ቀጥታ መዝለል ያስችሎታል ወደ ተመሳሳይ እቃዎች እና ጽሁፎች

የ ዴስክቶፕ ማተሚያ LibreOffice መጻፊያ

LibreOffice መጻፊያ የ ተለያዩ የ ዴስክቶፕ ማተሚያዎችን እና መሳያ መሳሪያዎችን ይዟል: እርስዎን ለመርዳት የ ባለሞያ ሰነዶችን እንዲፈጥሩ ለማስቻል: እንደ መግለጫ ጽሁፍ: የ ዜና ደብዳቤዎች እና ግብዣዎች የመሳሰሉ: የ እርስዎን ሰነድ ወደ በርካታ-አምድ እቅድ አቀራረብ መቀየር ይችላሉ የ ጽሁፍ ክፈፎች , ንድፎች : ሰንጠረዦች እና ሌሎችንም እቃዎች

ስሌቶች

የ ጽሁፍ ሰነድ LibreOffice አብሮት የተዋሀደ የ ማስሊያ ተግባር አለው: የተወሳሰቡ ስሌቶችን መፈጸም የሚያስችሎት ወይንም ሎጂካል አገናኝ:. እርስዎ በ ቀላሉ መፍጠር ይችላሉ ሰንጠረዥ በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ስሌቶችን ለመፈጸም

ስእሎች መፍጠሪያ

የ LibreOffice መጻፊያ መሳያ መሳሪያዎች እንደ ስእሎች፡ ንድፎች፡ መግለጫዎች እና ሌሎች አይነት ስእሎች በ ቀጥታ ወደ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ መፍጠር ያስችሎታል

ንድፎችን ማስገቢያ

ስእል ማስገባት ይችላሉ በ ተለያየ አቀራረብ ወደ ጽሁፍ ሰነድ: እንዲሁም ንድፎችን እንደ JPG ወይንም GIF አቀራረብ: በ ተጨማሪም በ አዳራሽ የተለያዩ የ ቁራጭ ስእሎች ስብስብ ንድፍ እና የ ፊደል ስራ አዳራሽ አስደናቂ የ ፊደል ስራ ውጤቶች ይፈጥራል

ተለዋዋጭ የ መተግበሪያ ገጽታዎች

ይህ የ ፕሮግራም ገጽታ የተዘጋጀው እርስዎ እንደሚፈልጉት እንዲያሰናዱት ተደርጎ ነው: ምልክቶችን ማስተካከል ይችላሉ እና ዝርዝሮችን: የ ተለያዩ የ ፕሮግራም መስኮቶችን ቦታ መቀየር ይችላሉ: እንደ ዘዴዎች እና አቀራረብ መስኮት ወይንም መቃኛውን እንደ ተንሳፋፊ መስኮቶች በ ማንኛውም ቦታ በ መስኮቱ ውስጥ ማድረግ ይችላሉ: እርስዎ ማሳረፊያ አንዳንድ መስኮቶችን በ መስሪያ ቦታ ጠርዝ በኩል ማድረግ ይችላሉ

መጎተቻ & መጣያ

መጎተቻ -እና-መጣያ ገጽታ የሚያስችለው በ ጽሁፍ ሰነዶችን በ ፍጥነት እና በ ቅልጥፍና መስራት እንዲችሉ ነው LibreOffice: ለምሳሌ እቃዎችን መጎተት-እና-መጣል ይችላሉ እንደ ንድፍ ያሉ ከ አዳራሽ ውስጥ: ከ አንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በሚሰሩበት ሰነድ ውስጥ ወይንም በ ተከፈቱ LibreOffice ሰነዶች ውስጥ

የ እርዳታ ተግባሮች

መጠቀም ይችላሉ የ እርዳታ ስርአቱን እንደ ሙሉ ማመሳከሪያ ለ LibreOffice መተግበሪያዎች እንዲሁም መመሪያዎች ለ ቀላል እና ለ ውስብስብ ስራዎች