የ ምልክት ማድረጊያ አስተዳዳሪ
ይጠቀሙ ወደ ምልክት ማድረጊያ መጨመሪያ ምልክት የ ምልክት ማድረጊያ ለማሰናዳት ለ አሁኑ ገጽ በ እርዳታ ገጽ ላይ ለሚታየው |
እርስዎ ማግኘት ይችላሉ ምልክት ማድረጊያ በ ምልክት ማድረጊያ tab ገጽ ውስጥ
-
ሁለት ጊዜ-በ መጫን ምልክት ማድረጊያውን ወይንም ማስገቢያውን በ መጫን የ ተመደበውን የ እርዳታ ገጽ ይከፍታል: በ ቀኝ-ይጫኑ የ አገባብ ዝርዝር ለ መክፈት
-
የ ምልክት ማድረጊያውን ለማጥፋት የ ማጥፊያ ቁልፍ ይጠቀሙ
የሚከተሉት ትእዛዞች በ አገባብ ዝርዝር ለ ምልክት ውስጥ አሉ
-
ማሳያ - የ ተመረጠውን የ እርዳታ ጉዳይ ማሳያ
-
እንደገና መሰየሚያ - ለ ምልክት ማድረጊያ ሌላ ስም ለ ማስገቢያ ንግግር መክፈቻ
-
ማጥፊያ - የ ተመረጠውን ምልክት ማድረጊያ ማጥፊያ